ቪዢን 20/20 የብረሃኑ ነጋ ቀመር። የትምህርት ንግድ ሚኒስቴር ለምን በትውልድ ላይ የቁማር ፖለቲካ ይጫወታል?
አባቱ ቀማኛ፤ ልጁ ደበኛና ቀማኛ ሊባል የሚገባው የዘመናችን እኔ ብቻ አዋቂ የእሥሥት በሃሪን የተላበስው ሚኒስቴሪ ኦቦ ብራኑ ነጋ ይባላል። በአፄ ሐይለሥላሤ ዘመን በንጉሰ ነገሥቱ ፈቃድ እና በ አቋቋሙት የፋይናስ የብድርና የቁጠባ መስክ አባቱ አቶ ነጋ ቦንጋ ነገዴ እና ከበርቴ ሆነው፤ ዘመናቸው የቀና፤ ዘሮቻቸው ጠግበው ውለው አደረው፤ ዘምነው አከትመዋል። ልጃቸው ወይም ሁለቱ ልጆቻቸው በሞት ከተልየችው እህቱ ጋር የግራ ዘመም አቀንቃኞች ሆነው፤ የደሃውን፤ ያልተማረውን፤ እድሉ እንደነሱ ያልስመረልተን የድሃ ልጅን በተረት ተረት የፈርንጅ ርዕዮት የጥይት እራት አድረገውት፤ የዘመናች እና የትውልድ ነቀዝ የሆነብን የአቶ ነጋ ቦነጋ ወንድ ልጃቸው ከማዕተ ግራዘመም እልቂት ተርፎ የመጪውን ትውልድ እድል በቂም በቀል ተነሳሽንት ይኸው አደባባይ እየቆመረበት ይገኛል።
አንድ ሃገር የትመህርት ዘርፍ ነድፋ፤ መተዳደሪያ መርሆዎችን አንፃ፤ ኢንተረናሸናል ህግጋትን አከብራ፤ ትውለዷን የምታንፅበት ፖሊሲን በሚኒስቴር መዋቅር ደረጃ አቋቁማ ይህ መንግቴ ዘመናዊ እና አለማቀፋዊ መንግስት ማሟላት ያለባቸውን ግዴታዎች አሟልቼ ያለምንም ህፍረት ሃገረ መንግስት ንኝ ብላ ከቆመችበት ዘመን ጀምሮ እንዲህ ህዝቧ እና መጪው ትውልዷ ተዋርዶ እና ተወንጅሎ አያውቅም። የተባበሩት መንግስታት ዩኒቨርሳል መብት ብለው በህግ የተቀረጹ ‘የሰው ለጆች መሰርታዊ መብት ብለው’ ካስቀመቱት ሀግጋቶች እነዱ ‘ነፃ ዩኒቨርሳል የትመህርት መብትና እድልን ለዜጎች ያለምንም አድሎ ማቅረብ ነው።
Article 26
- Everyone has the right to education. Education shall be free, at least in the elementary and fundamental stages. Elementary education shall be compulsory. Technical and professional education shall be made generally available and higher education shall be equally accessible to all on the basis of merit.
- Education shall be directed to the full development of the human personality and to the strengthening of respect for human rights and fundamental freedoms. It shall promote understanding, tolerance and friendship among all nations, racial or religious groups, and shall further the activities of the United Nations for the maintenance of peace.
- Parents have a prior right to choose the kind of education that shall be given to their children.
ምንጭ፡ https://www.un.org/sites/un2.un.org/files/2021/03/udhr.pdf
እንደ ኢትዮጰያ ያሉ አቅመ ደካማ ሀገሮች፤ በተባበሩት መንግስታት በትምህርት አሰጣጥ ሂደታቸው ይደጎማሉ። በጎ አድራጊ ድረጅቶች፤ ግለሰቦች እና ግብረ ሠናይ ድርጅቶች የህዝቡን እና የግለሰቦችን የመማር መብት በነዋይ በጥናታዊ ምርምሮች ለተማሪውም ላስተማሪውም ይደጉማሉ፤አስፈላጊውን አቅርቦት ይለግሳሉ አልፈው ተርፍው በቅጥትኛ ተሳታፊነት መሃል ገብተው ያሳልጣሉ። የትምህረት ተደራሽነት እንዲስፋፋ መንግስት በግብር ሰብሳቢነት፤ በሕዝብ የትቋቋሙ መሃበራዊ ድረጅቶች፤ የሃይማኖት ተቋሞች እና ግለሰቦች በተነሳሸነት እውቀትን ለማዳረስ የበኩላቸውን ድርሻ ይወጣሉ እየተውጡም ይገኛሉ። ይሄ ሁሉ መረባረብ ባለበት ፈተናውን ሳይፈትኑ በፊት መላተማሪወን ተማሪ ቤቶቹን ቤትስቡን በፍርደ ገምድል አስተሳሰብ አስቀድሞ በመፈረጅ 97 በመቶ ተማሪ ፈተናውን ያላለፈው ተማሪው ‘ሌባ’ ‘ኮራጅ’ እና ‘መረን የሰደደ ልቅ ትውልድ’ ስለሆነ ነው ብሎ ባደባባይ እጁን ኪሱ ውስጥ ከቶ ማላከክ ከሚኒስቴር ቀርቶ ስብእናና አእምሮ ካለው ተራ ግለሰብ አየጠበቅም። ኦቦ ብርሀኑ ነጋ ግን በወር 10ሺህ ዶላር በ UNDP እየተከፈለው በሚነኪስቴር እነት ቁነጮ የሚመራው መንግሰታዊ መዋቅር ተመሪውን ወንጀለኛ አድረጎ በመፈረጅ በወታደርና በፓሊስ እንደ ወንጀለኞች አስጨንቆ ልጆቻችንን በጭንቀት እንዲፈተኑ ማድረጉ በህግ መጠየቅ ይገባዋል የሚሉ ድምፆች እየመጡ ነው። ውጤቱም ውድቀት እና ለ12 አመት ተኮትኩቶ ያደገን ትውልድ እንደቆሻሻ መድፋት ነው። መፍትሄ ብለው ያቀርቡትም ንግድን ማሳልጫ እና ሌባ ኮራጅ ያሉትን ትውልድ እንደሎተሪ ድግመህ ሞክር ማልፍህን ግን ዋስትና አንሰጥህም የሚሉ ስትራቴጂዎች ናቸው ብለው ይሚያምኑም ትንትነዋል።
ብርሃኑ ነጋ መንግስት እሰከ መዋቅሩ ተጠያቂ ነን ብሏል። ስለዚህም እርሱ እንዳለው መጠየቅ መከሰስ እና መወገዝ አለበን። አንደኛው ክስ ለምንድን ነው ለፈተናው ጊዜ ያንን ሁሉ ነዋይና ሎጂስቲክ አፍሰህ ተማሪዎቹ ‘ሌቦች’ አስተማሪዎቹ እና የትምህርት ገበታው ‘ብቃት የሌላቸው’ ናቸው በማለት ስም በማጠፋት በማንቋሸሽ ትውለድን ቤተሰብን ለማክሰር አዲስ ሴራ የሸረብከው?? ተብሎ በሕግ መጠየቅ አለበት። የመንግስት መገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም የተማሪዎች ‘ወንጀለኛ ናቸው’ ‘ኮራጅ ትውልድ ብሎ በጅምላ መፈረጁ የትውልድ እና የዘር ማጥፋት ወንጀልነቱን የመላክታል።
የትምህርት ተቋማቱ አሜኔታ እንዳይጣልባቸው የተስራው ሴራ በህግ መመርምር አለበት። የልጆቹን አምኖ የስጣቸው ተማሪ ቤቶችን ‘የሌባና ይኮራጅ መፍብርኪያ ናቸው’ ልጆቻቹህ ሌቦች አስትማሪዎቹ ሌቦች ተማሪ ቤቶቹ የሌባና መሰብሰቢያ ስልሆኖ እኔ አፍሼ በፖሊስ አስፍራርቼ እፍትናለው ይሚልውን መብት ላንድ በሽብር ተጠርጥሮ የተፈረድበት ፍርደኛ ግለሰብ በመንግስት መዋቅ አታኮ ሕዝብ እና አገር ላይ በቀሉን እንዲውጣ ማን ፈቀደለት?? 3 በመቶው አልፏል የተቀረው እንደገና ነዋዩን በግሉ አፍሶ “ዩንቨርስቲ ማቴሪያል” ከሆነ እድሉን ይሞክር ማለቱ ትምከህቱን እና ማን አለብኝነቱን ያሳያል።
ብርሃኑ ነጋ በሽበርተኛነት የከሰሰ ፍርደነኛ ነው። የከተማ ነውጥን አስነስተሃል ተብሎ ተከሶ በምሕረት የተለቀቀ ፍርደኛም ነው። በልቡ ሃገረ ኢትዮጵያ ላይ ቂም አላሳደረም እንዳይባል በኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት ከለላ ሰጪነት በግብፅ መንግስት ነዋይ ድጎማ ሕዝባዊ አመጽን አስነስቶ አገርን አፍርሶ ለመስራት ሲታገል መክረሙ የአደባባይ ሚስጢር ነው። ተማሪን እንደመንግስት ያለምንም ፍትሃዊ ሂደት ወንጀለኛ ነህ በሎ እንደ ወንጀለኞች አጉሮ ለፈተና አፍሶ ወስዶ መፈተን ከዛም ፈተናውን 97 በመቶው ወድቃቹሃል ብሎ ማወጁ የቅን አሳቢነት ሳይሆን የመሰሪ እና የደበኛነት መገለጫ ነው። እንደገና ከፍላቹህ ተፈተኑ አሊያም ገደል ግቡ እናንተ ሌቦች! ቤተሰቦቻቹህ ሌቦች! አሰተማሪዎቻቹህ ሌቦች! ብሎ subliminal መንግሰት ላይ አምጽ! ገልበጠው! አትታዘዝልት! ተገንጠል! እምቢተኝነትህን አሳይ! ብሎ ሲያወጅ ስለምን ይሄ ወንጅለኛ በሃገር ህልውና ላይ በትውልድ እጣፈንታ ላይ ምነው ቀዘነ ብሎ አንድም የጠየቀ የለም። ሚኒስቴር ትብዪዎቹ ጠቀላዩን ጨምሮ ዲግሪያችውን ብጥቀር ገብያ ግዝትው ነው እንዲህ ያበጡብን በለው እርሱ ያፈራቸው ሚዲያዎች ሲንግሩን ከርምዋል። እንግዲያውስ ልክ ትማሪዎቻችን ብአድባባይ ሌባ ኮራጅ ትብለው ታፍሰው እንደትፍተኑት ብርሃኑን ጨምሮ ጠቀላዩን ሚኒስቴር እነ ዶክተር እንቶኒዎች ታፍሰው ይ12ኛ ክፍል ማልፊያ ይፈተኑ!! እስኪ ወንድ ይጠይቅ!! በርግጠኝነት አያልፉም!! ይህ ሆነ አልሆን በህግ አይጠይቅም ማለተ ግን አይደለም።ህዝቡ ይሄንን ሁሉ አንጡራ ሃብቱን አፍሶ ላስትማራቸው ልጆቹ ለመብቱ አይነሳምም ማለትም አይደል። የነሳል ብርሃኑ ነጋን ተባባሪዎቹን ለህግ ያቀርባል። እርሱ ፈርጆ ያመጣውንን መራራ ፅዋ እራሱ ይቀምሳታል። ተጀመረ።
ልማንኛውም ክዚህ ሥር ያለውን ጋዜጠኛ ምግልጫውን ይመልከ
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ላይ የትምህርት ሚኒስቴር የሰጠው ሙሉ መግለጫ
ሌላው በጠቅላዩ መሪነት ልጆቻችሁን የሚያስትምሩት እኒህ አይንቱ ውዳቄዎች ናቸው ይሚል ዘግባ ከስር ይመልክቱ። ፍጅቱ መዋቅራዊ መሆኑን አመላካች ነው።
እንግዲህ እውንታዎቹ በ አህዝ ምን ይመስላሉ? የገዢው መደብ ተማሪዎች ሁሉም አልፈው ባልዲግሪ ይሆናሉ እንደቤተስቦቻቸው አጭብርብረው ይሚል ይመስላል።
እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፦
– በሀገሪቱ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች በ1 ሺህ 161 መደበኛ ትምህርት ቤቶች አንድም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ብሔራዊ ፈተና አላለፈም።
– የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ካስፈተኑ 2 ሺህ 959 የመደበኛ ትምህርት ቤቶች መካከል ነው 1 ሺህ 161 የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪዎችን እንዳላሰለፉ የታወቀው።
– ከአጠቃላይ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 798 ትምህርት ቤቶች ቢያንስ አንድ ተማሪ አሳልፈዋል።
– 7 ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች በሙሉ ያሳለፉ ሲሆን እነዚህም ትምህርት ቤቶች ፦
👉 ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ ቤት፣
👉 ኦዳ አዳሪ ልዩ ት/ቤት ፣
👉 ባህርዳር ስቴም ት/ቤት ፣
👉 ወላይታ ሊቃ ት/ቤት፤
👉 የጎንደር ማህበረሰብ አቀፍ ት/ቤት እና ከግል ትምህርት ቤት ደግሞ ለባዊ ት/ቤት ናቸው።
ምንጭ፦ WMCC
ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አሰራር ለመከተል ማቀዱን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።
በዚህም መሰረት ከግማሽ በላይ ያመጡት 30 ሺህ ገደማዎቹ ተማሪዎች በሚቀጥለው ዓመት በቀጥታ ወደ ዩኒቨርስቲ ገብተው የአንደኛ ዓመት ተማሪ ይሆናሉ።
ቀሪዎቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም መሰረት በማድረግ፤ የተሻለ ያመጡት ተመርጠው ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ እንደሚደረግ አስረድተዋል።
ይሁንና እነዚህ ተማሪዎች በቀጥታ የዩኒቨርስቲ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንደማይሆኑ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠቁመዋል።
ተማሪዎቹ ” የደከሙባቸው ትምህርቶችን ” ለአንድ ዓመት በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በግላቸው እየከፈሉ እየተማሩ ከቆዩ በኋላ፤ በዓመቱ መጨረሻ ፈተና ወስደው ካለፉ በዩኒቨርስቲዎች የአንደኛ ዓመት ተማሪ ሆነው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር እንድዘገበው፦
– በሀገር ደረጃ የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት በተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 ፤ 666 ሲሆን በማህበራዊ ሳንይንስ ከ600 ፤ 524 ሆኖ ተመዝግቧል።
– በፆታ በተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 ፤ ወንድ 666 ሴት 650 ፤ በማህበራዊ ሳይንስ ከ600 ወንድ 516 ፤ ሴት 524
– በአጠቃላይ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ በማህበራዊ ሳይንስ ከ500 እና በላይ ያስመዘገቡ 10 ተማሪዎች፤
– በአጠቃላይ በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 እና በላይ ያስመዘገቡ 263 ተማሪዎች ናቸው።
ትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በሰጡት መግለጫ ምን ምን ጉዳዮችን አነሱ ?
– በ2014 የትምህርት ዘመን ለፈተና የተመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በጠቅላላ 985 ሺህ 354 ተማሪዎች ሲሆኑ ለፈተና የቀረቡት 92 ነጥብ 2 % 908 ሺህ 256 ተማሪዎቹ ሲሆኑ 77 ሺህ 98 ተማሪዎች ፈተና አልወሰዱም።
– በደንብ ጥሰት ፣ለመኮራረጅ በመፈለግ እና በሌሎች ምክንያቶች 50 ሺህ 170 ተማሪዎች ሳይፈተኑ ቀርተዋል።
– በ2014 የትምህርት ዘመን 899 ሺህ 520 ተማሪዎች ተፈትነዋል ።
– በፆታ ማዕከልነት የአማካይ ውጤት በወንዶች 30 ነጥብ 2 እንዲሁም ሴቶች 28 ነጥብ 09 % አማካይ ውጤት አስመዝግበዋል።
– በትምህርት ዘርፍ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከማህበራዊ ሳይንስ በተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን የተፈጥሮ ሳይንስ 31 ነጥብ 63 ከመቶ እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ 27 ነጥብ 79 ከመቶ በአማካኝ አስመዝግበዋል።
– በክልል ደረጃ ይህየ ነው የሚባል የውጤት ልዩነት የሌለ ሲሆን አዲስ አበባ ፣ ሐረሪ እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል።
– ከተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወንድ ከ 700፤ 666 ያስመዘገበ ሲሆን 650 ሴት ተማሪ አስመዝግባለች ።
– በማህበራዊ ሳይንስ ከ600 ወንድ 524 አስመዝግቧል።
– ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር እውቅና እና ሽልማት ይሰጣቸዋል።
ሃገረ ኢትዮጵያ ተረካቢ ትውልድ አይውጣብሽ የሚል ዘመን የደረስን ይመስላል። ሙስና ሕጋዊ! ያንድ የዘር ሃረግ እየጥሩ ዘሩን ማጥፋት! ማሳደድ! ፓለቲካ ቁማር በላንው! ደግሞ እንዳይንሳ አከርካሪውን መታንው ብሎ አድባባይ መፎከር ተማሪን አሰልፎ የሄን የጥላቻ ዘምር፤ ፈትና ሲድርስ አንተ ሌባ ትውልድ አዲሡን ግብር ሳትከፍል ወደ ፊት አታሰልፋት ብሎ ይሚዛበት የፖለቲካ ትርኪምርኪ ወዮለት ግፉ ሞልቶ የፈሰሰ እለት።