የሾላ ገበያ እሳት ከ50ሚሊዎን ብር በላይ ጉዳት አደረሰ።
Read Time:40 Second
” በእሳት አደጋው 50 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ውድሟል “
የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ፤ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ሾላ ገበያ በደረሰ የእሳት አደጋ 50 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ገልጿል።
ኮሚሽኑ አደጋው ትናንት ሌሊት 10 ሰዓት አካባቢ መድረሱን አመልክቷል።በገበያ ማዕከሉ ከሚገኙ 1 ሺ 600 ሱቆች ውስጥ 84 የሚሆኑት ላይ የእሳት አደጋው የደረሰ ሲሆን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አደጋውን ለመቆጣጠር ባደረጉት ጥረት 1 ሺህ 516 የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ማትረፍ (500 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት) መቻሉን ገልጿል።
ኮሚሽኑ በሰጠው መረጃ እነወደገለዠው አደጋውን ለመቆጣጠር 12 የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች እና 95 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተሰማርተው ነበር።አደጋውን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር 4 ሰዓት 28 ደቂቃ ወስዷል።
– በአደጋው እስካሁን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። የአደጋ መንስኤ እየተጣራ ነው።የሾላ የገበያ ማዕከል በከተማ ደረጃ ለእሳት አደጋ ተጋላጭ ተብለው ከተለዩ የገበያ ማዕከላት ውስጥ አንዱ ነው።