ሊቀ እጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ እና ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ምእመናን በሐዋሳ በመገኘት አጽናንተዋል፤ ሀዘናቸውንም ገልጸዋል።
Read Time:36 Second
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ እና ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በትናንትናው ዕለት በጸጥታ ኃይሎች በተወሰደው እርምጃ የተጎዱ ምእመናንን ጎብኙ።
የሻሸመኔ ኦርቶዶክሳውያን በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሰረት የሕገ ወጡን ቡድን ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አናስገባም በማለት ቅጽራቸውን ሲጠብቁ ቢውሉም ለሕገ ወጡ ቡድን ከለላ የሰጠው የጸጥታ ኃይል በንጹሃን ላይ እርምጃ መውሰዱ ይታወቃል።
በዚህም ሰማዕትነትን የተቀበሉ ምእመናን እንዳሉ ሁሉ በርካቶች ከፍታኛ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሐዋሳ የተለያዩ ሆስፒታሎች ተወስደዋል።
እስካሁን ባለን መረጃም በሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል 6፣ በያኔት ሆስፒታል፣ በአላቲዮን ሆስፒታል 8 ምእመናን ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛሉ።
የሲዳማ፣ ጌዲዮ፣ አማሮ፣ ቡርጂና ምዕራብ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ እጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ እና ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የጆርጂያና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እነዚህን ምእመናን በሐዋሳ በመገኘት አጽናንተዋል፤ ሀዘናቸውንም ገልጸዋል።
ምንጭ -የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት