” መንግስት በኢንተርኔት ግንኙነት ላይ የጣለውን ገደብ ያንሳ ” – የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ም/ቤት

0
0 0
Read Time:51 Second

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት መንግሥት በኢንተርኔት ግንኙት ላይ የጣለው ገደብ ሚዲያዎች ስራቸውን በአግባቡ ለህዝቡ ተደራሽ  እንዳያደርጉ እንቅፋት እየፈጠረ በመሆኑ ገደቡ እንዲነሳ መጠየቁን ለቲክቫህ በላከው መግለጫ አሳውቋል፡፡

ከሰሞኑን መንግስት በአንዳንድ የኢንተርኔት የግንኙነት መተግበሪያዎች ላይ የጣለው ገደብ መገናኛ ብዙሃን መረጃ የማሰባሰብ፤ የማደራጀትና ተደራሽ የማድረግ ላይ ተግዳሮት ከመፍጠሩ ባሻገር የሰበሰቡትን መረጃ በሀገርና በውጭ ሀገር ለሚገኙ ተደራሲያን ኢንተርኔትን እንደ ዋነኛ የመረጃ ማሰራጫ የሚጠቀሙ መገናኛ ብዙሃን ስራቸውን በአግባቡ ለመከወን መቸገራቸውን በመግለጫው ተመላክቷል።

በመሆኑም ሰሞኑን  በሀገሪቱ ከተፈጠረው ኃይማኖታዊ አለመግባባቶች ጋር በተያያዘ የችግሩን ስፋትና ክብደት ከግምት በማስገባት ሊቀለበስ የማይችል አደጋን ምክንያት በማድረግ ካልሆነ በስተቀር ሕግን መሰረት በማድረግ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ላይ መንግስት ገደብ ሊያደርግ እንደማይገባ ምክር ቤቱ እንደሚያምን አሳውቋል።

ከዚህ አንፃር በአንዳንድ የኢንትርኔት መረጃ ማስተላለፊያ መተግበሪያዎች ላይ የተጣለው ገደብ ሶስት ሳምንታትን ያስቆጠረ ከመሆኑም በላይ ገደቡ የተደረገበትን ምክንያት የሚመለከተው መንግስታዊ አካል የሰጠው ግልጽ  ማብራሪያ ባለመኖሩ የጠቅላላ ህዝቡን መረጃ የማግኘትና የማሰራጨት መብት ላይ ገደብ ለመጣል የሚያበቃ አማራጭ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ም/ቤት ገልጿል።

ም/ቤቱ ገደቡ እንዲነሳ በይፋ ጥሪ አቅርቧል።

#NB. በማህበራዊ መገናኛዎች (ቴሌግራም፣ ፌስቡክ፣ ዩትዩብ…) ላይ ገደብ ከተጣለ ዛሬ 24ኛ ቀን ሆኗል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *