አቶ ታየ ደንደዓ:- ሴተኛ አዳሪ በሚሊዮን የገዛ ቡድን ዛሬ በህግ ማስከበር ስም የደሃ ቤት እና ቤተ እምነት ማፍረስ ተገቢ አይደለም!!

0
1 0
Read Time:56 Second

“የቱለማን መሬት ሸጦ ሴተኛ አዳሪ በሚሊዮን የገዛ ቡድን ዛሬ በህግ ማስከበር ስም የደሃ ቤት እና ቤተ እምነት ማፍረስ ተገቢ አይደለም!!” አቶ ታየ ደንደዓ

አቶ ታዬ ደንደዓ በአዲስ አበባ ዙሪያ ሸገር ከተማ የሚፈርሱ ቤቶች እና ቤተ እምነቶችን ተከትሎ የፃፉት እንደሚከተለው ወደ አማርኛ ተተርጉሟል እንድታነቡት እንጋብዛለን!!

ቱለማዎች መፈናቀላቸው እውነት ነው። ቱለማን አፈናቅሎ ለማኝ እና ስደተኛ ያደረጋቸው ማነው? ሌላ ሃይል ቢኖርም አብዛኛውን ቱለማን ከቤታቸው ያፈናቀለው ሌቦቹ ናቸው። ባለፉት አምስት ዓመታት በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ከተሞች የሆነውን ሀገር ያውቃል። በገበሬ ስም የአዲስ አበባን መሬት የዘረፈው ማነው? የአዲስ አበባን መሬት ቸብችቦ ሴተኛ አዳሪ በጨረታ የገዛው በሚሊየን ቲፕ የሰጠው ማነው? የሌባው ቡድን ነው።

ቀን ቀን የቱለማን ደሃ የሚያስለቅሰው፣ ማታ ውስኪ ቤት የሚጨፈረው፣ ይቅር የማይባል ወንጀል እየፈፀሙ ዛሬ ደግሞ የቱለማ ጠበቃ መሆን። በቱለማነት ተከልለው የራስን ወንጀል መደበቅ አይቻልም። ለቱለማ ብለን መስጂድ አፈረስን ማለት ምን ማለት ነው! የመስጂድ ማፍረስን ከቱለማ ጋር ማገናኘት ለግጭት መቀስቀሻ ነው።

ህግን ማክበር ትክክል ነው። የቤተ እምነት ግንባታ ጨምሮ ሁሉም ነገር በሕግና በሥርዓት መከናወን አለበት። ህገ ወጥ ግንባታን መከልከል ጉልበትና ሃብት ሳይባክን ነው መሆን ያለበት። የራስን መሬት ሸጦ፣ ቤት ሲሰራ ዝም ብሎ መብራትና ውሃ አስገብቶ፣ ከፍተኛ የሀገር ሀብት ከፈሰሰበት በኋላ በህግ ማስከበር ስም የደሃ ቤት እና ቤተ እምነት ማፍረስ ተገቢ አይደለም።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *