በዎላይታዞንየድጋሜሕዝበውሳኔምርጫ (ሪፈረንደም) ድምፅአሰጣጥ እየተካሄደ ነው።

0
0 0
Read Time:52 Second

ሰኔ 12 ቀን 2015 / በዎላይታ ዞን የድጋሜ ሕዝበ ውሳኔ ምርጫ (ሪፈረንደም) ድምፅ አሰጣጥ እየተከነወነ ነው።

– የመራጮች ምዝገባ እና የድምፅ መስጠት ሂደት በአንድ ቀን የሚደረግ ይሆናል።

– የቀረቡት ሁለት አማራጮች ናቸው። እነሱም ፦

ነጭ እርግብ ፦ የ6ቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ዎላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና የ5ቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ደራሼ) በአንድ የጋራ ክልል መደራጀትን #እንደግፋለሁ።

ጎጆ ቤት ፦ የ6ቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ዎላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና የ5ቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ደራሼ) በአንድ የጋራ ክልል መደራጀትን #አልደግፍም።

– ድምፅ መስጠት የሚጀመረው ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ነው።

– በ1,812 የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ድምፅ ይሰጣል ፤ ለዚህም ዝግጅት ተደርጓል።

– ከአዲስ አበባ 5,215 ፤ ከዎላይታ ዞን 3,845 ተመልምለው በቦርዱ የሰለጠኑ አስፈፃሚዎች በምድብ ጣቢያዎቻቸው ላይ ይገኛሉ።

– ከነገ ድምፅ የመስጫ ቀን ጋር በተያያዘ በዞኑ በሚገኙ የፌዴራል እና የክልል መንግስታዊ ተቋማት ስራ አይኖርም።

– ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑና የግል ተቋማት #ዝግ ሆነው ይውላሉ።

– የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ሆስፒታሎችን ጨምሮ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት …ወ. ዘ. ተ) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ ማከናወን ይችላሉ። እንዲዘጉ አይገደዱም።

– የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ ይቀጥላል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *