በመቅደላ ጦርነት ወደ እንግሊዝ የተሰረቁ የቅድስት ድንግል ማርያም ወቅዱስ ገብርኤል ጽላት ተመለሰ።

0
0 0
Read Time:52 Second

በመቅደላ ጦርነት ወደ እንግሊዝ ተወስዶ የነበረው የቅድስት ድንግል ማርያም ወቅዱስ ገብርኤል ጽላት ለኢትዮጵያ ተመለሰ።

በ1860 ዓ.ም በመቅደላ ጦርነት ወደ እንግሊዝ ተወስዶ የነበረው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ወቅዱስ ገብርኤል ጽላት በትላንትናው ዕለት መስከረም 10 ቀን 2016 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ተመልሷል።

በትናንትናው ዕለት በእንግሊዝ ለንደን በተካሄደ የርክክብ ስነ ሥርዓት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፣ ከኢትዮጲያ ኢምባሲ ተወካዮች እንዲሁም ቅርሶቹን በማስመለስ ትልቅ ድርሻ የነበራቸው የሼሄራዛድ ፋውንዴሽን ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በኢትዮጲያ የታሪክና ባሕል ተመራማሪነታቸው የሚታወቁት ዶ/ር አሉላ ፓንክረስት እነዚህ በጦርነት ወቅት የተዘረፉ ቅርሶች እንዲመለሱ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ተገልጿል።

የፊታችን እሑድ መስከረም 13/2016 ዓ.ም በርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለጽላቱ የክብር አቀባበልና ወደ ኢትዮጲያም ሽኝት እንደሚደረግለት ታውቋል።

እ.አ.አ በ2020 በለንደን የተመሠረተውና በእንግሊዝ ያሉ የኢትዮጵያ ቅርሶችን ለማስመለስ በርካታ ሥራዎችን የሠራው የሼሄራዛድ ፋውንዴሽን መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ጣሂር ሻህ እነዚህን የመሰሉ ሃይማኖታዊ እና ባሕላዊ ቅርሶች ከተዘረፉ በኋላ መመለስ የተሰበረውን ለመጠገን የቆየን ቁስል ለመፈወስ አቅም እንዳላቸው ተናግረዋል።

ለቀጣይ የትብብር ሥራዎችም መሠረት ናቸው ያሉት ጣሂር ሻህ ያለንን አክብሮት ማሳያም ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ከታቦተ ሕጉ በተጨማሪ ሌሎች ቅርሶችም መመለሳቸው ታውቋል።

Source: ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *