ከመቅደላ አንባ የተዘረፈው የታቦተ ሕግ ርክክብ እና ታሪካዊ መንፈሳዊ ገጠመኝ

0
0 0
Read Time:4 Minute, 29 Second

ትላንት መስከረም ፲፩ ቀን 2016 ዓ.ም (21/09/2023) ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ሕልፈተ ሕይዎት በኋላ ብዙ የተዘረፉ እጅግ በጣም ውድ የሀገር ቅርስና የሃይማኖት መገለጫ ንዋያተ ቅድሳት መካከል የተወሰኑ ታቦታተ ሕግ እርክክብ እንደተረገ ወይም እንደ ሚደረግ የደረሰንን መረጃ ዋቢ አደርን ከመግለጽ በተጨማሪ በጉዳዩ ላይ ቅርብ ክትትል እንደምናደርግ መጠቆማችን እናስታውሳለን።

በዚሁም መሠረት አንድ በኢትዮጵያ ታሪካዊ ወቅታዊ፣ፓለቲካዊና ሃይማኖታዊ ንቁ ተሳትፎ ባለው #የኢትዮጵያ #ትሪቢውን ዋና አዘጋጅ ወንድም እንዳለ (Endex) እንደዚሁም በእንግሊዝ ሀገር ኗሪነቱ የሆነ የተዘረፉ ቅርሶችን በግል ገንዘቡ እየገዛ በማሰባሰብ እና በኢትዩጵያ ታርካዊና ፓለቲካዊ ጉዳይ ላይ ቀናኢነት ካለው ከአቶ አለባቸው ደሳለኝ ጋር በመሆን እርክክብ ይደርግበታል ወደተባለው የእንግሊዝ ታሪካዊ ቦታ አቅንተን ነበር።

ይሁን እንጅ የምሽቱን የርክክብ ትዕይንቱ በማቀናጀት የሚሠሩት እንግሊዛዊት ውይዘሮ፤ እርክክቡ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲፈጸም፤ የምዲያ ሰዎችም እንዳይገቡ ከመንግሥት መመሪያ የተሰጠበት፤ መግባት ያለባቸውም ኢንባሲው በዝርዘር ያስመዘገባቸው እና የአለባበስ መስፈርቱን ያሟሉ ሰዎች ብቻ መሆናቸውን ስለገለጹልን ይኸን ተላልፎ ለመግባት አለወደድንም።

ይሁንና ጉዳዩን በቅርብ መከታተል የወዴታ ግዴታ መሆኑን ከመረዳት ጋር የደርስንበትን ተጨባጭ ሁኔታ ለሕዝብ ማካፈል ተገቢ በመሆኑ ከመገንዘብ አኳያ የሁኔታውን ጭብጥ እና የምሽቱ ትዕይንት ምን ይመስል እንደነበር እንደሚከተለው ለማቅረብ እንወዳለን።

የታቦታተ ሕጉ እርክክብ ቀን ላይ ከለንደን ደብረ ጽዩን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በተወከሉ ቀሳውስት ኃላፊነት ቀደም ብሎ እንደተፈጸመ የታወቀ ሲሆን ታቦታቱም የቀድሥት ደንግል ማርያም እና የቅዱስ ገብርኤል ታቦተ ሕግ በአንድነት የያዘ ጥንታዊነቱን በሚገባ የሚገልጽ አሁን ዘመን ሊገኝ በማይችል ክቡር የማዕድን ቅርጽን የተላበሰ እንደሆነ አስቀደመን ለመረዳት ችለናል።

በምሽቱ የርክክብ ትዕይንት ብቻውን በተመለከተ በቦታው ከታደሙት ካህናት መካከል የታወቁት የተክሌ አቋቋም ወይም የደብረታቦሬ አቋቋም አባት የሚባሉት የአለቃ ተክሌ ገብረ ሃና ሦስተኛ የቀለም ልጅ እና ጎንደር ደብረታቦር የአለቃ ቀለመወርቅ ይማም ተማሪ የሆኑት የክሌ አቋቋም ኢትባሀል ተጠያቂና መምህር የሆኑትን ሊቀጠበብት ዓለማየሁ ደስታን አነጋግረናል።

ከሊጠበብቱ እንደ ተረዳነው አንድ በረጅም ጊዜ በእንግሊዝ ፓርላመንት ውስጥ ተሳትፎ የነበራቸው አሁንም በሓውስ ኦፍ ሎርድስ ውስጥ የሚያገለግሉ እድሜ ጠገብ የሆኑ ጥቁር እንግሊዛዊ እንደተገኙና ታሪካዊ ዳራውን አስቀደሙ ከመረዳት እና በዘረፋው ከመቆጨት መንፈስ በሚመስልና ገሳጭነት በላው ኃይለ ቃል ስሜት ንግግር ማድረጋቸውንና በተለይም በኢትዮጳያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልዩ የእምነት መገለጫ የሆነው ታቦተ ሕግ ተዘርፎ በአልባሌ ሁኔታ ለረጀም ጊዜ እንዲቀመጥ ማድረግ አግባብነት የሌው መሆኑን ወቀሳ አዘል የአደማጭን እዘነ ልቡና የሳበ ጠንከር ያለ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ለመረዳት ተችሏል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ እንደሆኑ የተገለጸው የታወቁት የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪ ሊቅ ፐሮፈሰር ፓንክረስት ልጅ ዶክተር አሉላ ፓንክረስት፤ የቅርሶቹን መዘረፍ ኢሕጋዊነት አስመልክቶ በጥንታዊ ፎቶ ግራፍ በተደገፈ ማስረጃነት ታሪካዊ ክስተተቱን ከታሪካዊ ጭብጡ ጋር በማገናዘብ አጭር ንግግር ማደረጋቸውን ታውቋል።

በእንግሊዝ የኢትዮጵያ ኢንባሲ አንባሳደር ተፈሪ መለስ፤ በእንግሊዝ ሀገር በጎ ፈቃድ የተዘረፉ ቅርሶችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመልሱ በማድረግ ደረጃ በእንግሊዝ መንግሥት የሚደረገውን ትብብር በማመስገን አጭር ዲፕሎማሲያዊ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ተረድተናል።

በምሽቱ የርክክብ ትዕይንት በኢንባሲው በኩል የስም ዘርዘራቸው የተላለፈ የተወሰነ ቁጥር ያላቸውን ኢትዮጵያውንያን የተገኙ መሆናቸው ሲታወቅ፤ ጉዳዩ በሚዲያም ሆነ በኢትዮጵያዊ ማኅበረሰቡ በስፋት እንዳይታወቅ ምክክር የተደረገበና በምስጢር መልክ እንደተያዘ ለመገንዘብ ችለናል።

ታቦታተ ሕጉ፤ በኣውሮፓ ለመጀምሪያ ጊዜ በቀዳማዊ ኃይልሥላሴ ፈቃድ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ ቡራኬ የዛሬ ሃምሳ ዓመት ክተመሠረተችው የር ዕሰ አድባራት ለንደን ደብረጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መንበረ ክብር በአደራ መቀመጡን ታውቋል።

በአደራ የሚቆየው ለሦስት ቀናት ብቻ መሆኑንና እሁድ ወደ ሀገር ቤት ይመለሳል የሚል መልዕክት የተሠራጨ ቢውጣም፤ ሁኔታ ጥናት ያለው፤ የወቅቱን የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ፤ በመዋቅርና በመርሐ ግብር የተደገፈ ተገቢው ምክርክር የተደረገበት ጉዳይ ነው ብሎ ለመናገር የሚያስደፍር አይደለም የሚል ጠቃሚ ትችት እየተንጸባረቀ ነው። ያምሆነ ይህ አሁንም ጉዳዩን በቀርብ እየተከታተልን ለሕዝባችን ይፋ ማድረግ ይጠበቅብናል።

በምሽቱ ላይ በሚያምር ሁኔታ ከቅንደ የተሠሩና በብር የተጠረዙ ሁለት የአፄ ቴዎድሮስ ዘመንም ሆነ ከዚያ በፊት የነገሥታቱና የመሣፍንቱ የክብር መጠጫ ዋንጫዎች ለዕይታ የቀረቡ ሲሆን እነዚህ ዋንጫዎች የርክክቡ አካል ስለመሆናቸውና ወደ ኢትዮጵያ ስለመመለሳቸው ጉዳይ የታወቀ ነገር የለም።

ይህን ጽሑፍ ከማጠናቀቃችን በፊት በዚህ ታቦተ ሕግ ርክክብና አቀማመጥ ላይ የተሰማኝን ታርካዊ ገጠመኝ ከመረዳት ወይም ከማስተዋል ጋር ያደረብኝ መንፈሳዊ ትሩፋት ለማካፈል ወደድኩኝ።

ይህ የተዘረፈው ኢትዮጵያዊ የቀድሥት ደንግል ማርያም እና የቅዱስ ገብርኤል ታቦተ ሕግ በአፄ ቴተዎደሮስ ዘመነ ንግሥና #የመጨረሻው ይሕዎት ዘመን ወይም ምደራዊ እስትንፋስ ላይ #ለመጀመሪያ ጊዜ ከሁለት መቶ ዓመት በፊት ባህር አቋርጦ መጥቶ በኢንግላንድ ወይም የመላእክት ምደር ተብላ በምትታወቀው ሀገር መቆየቱ እንደ ተጠበቀ ሆኖ፤ እንደገና በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ #የመጨረሻው የንግሥና ዘመን ለሐዋርያዊ አገልግሎት #ለመጀመሪያ ጊዜ በተመሠረተችው የደብረ ጽዩን ቅድስት ማርያም ታቦት ሕግ ጋር በአንድ መንበር በአንድ ከርሰ ሐመር ማደራቸው እጅግ አስደማሚ እረቂቅ መንፈሳዊ ክስተት ትልቅ መለዕክት ያለው መሆኑን እንድናስተውል አድርጎናል።

በተጨማሪም አሁን ደብረ ጽዮን ቅደስት ማርያም ያለችበትን ሕንጻ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ኤርትራውያን ጨምሮ ባደረጉት መንፈሳዊ አንድነት እና ትብብር አስተዋጽዖ የተገዛ ከመሆኑም በላይ፤ ይህ ታሪካዊ ሕንጻ ተጀምሮ የተጠናቀቀው በአፄ ቴዎድሮስ ንጉሥነ ነገሥት #የመጭረሻ ዘመን ከመሆኑም በተጨማሪ፤ ለረጅም ዘመናት በኢንግላንድ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሥር #የቅዱስ #ፊሊጶስ ቤተ ክርስቲያን ሆኖ ያገለገለ ነው።

ቅዱስ #ፊሊጶስ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ የንግሥት ሕደኬ የንብረት አዛዥ የነብረውን ኢየሩሳሌም ደርሶ ሲመለስ ከከመንገድ ላይ በመንፈስ ቅዱስ ተእዛዝ ተገናኝተው ቅዱስ ፊሊጵስ የክርስቶስን አምላክነት ከብሉይ ኪዳን መጽሐፍ እያጣቀሰ ለጃንደረባው ሰብኮና አሳምኖ ያጠመቀው የመጀምሪያው ክርስቲያን ያደረገው አዱስ ሐዋርያ ነው። [የሐዋርያት ሥራ 8፤26] ያንብቡ።

ከዚህ ጋር በተጓዳኝ ለንደን ደብረ ጽዮንን ቤተ ክርስቲያንን ያለምንም ክፍያ በነፃ አቋቋም በአብነት መምርነት የሚያገለግሉት፤ዲያቆናትን እና ቅሳውስትን የሚያስተምህሩት ቅን፤ ትጉህ ፤ጥንቁቅ መንፈሳዊ ባለሙያ ሊቀ ጠበብት #ዓለማየሁ ደስታ፤ በአፄ ቴዎድሮስ ልጅ ስም በተማራኪው ለዑል #ዓለማየው ስም የሚጠሩ ከመሆኑም በላይ፤እትብታቸው የተቀበረው ጎጃም ቢሆንም ከሕፃንነት እደሜያቸው ጀምሮ ተውህቦ ቀለም የተባለውን የተክሌ አቋቋም ትምህርትን በመማር ጥርሳቸውን ነቅለው ያደጉት በመንፈሳዊ ትምህርት ከሊቃውንት የተወለዱት ጎንደር ደብረታቦር ሲሆን፤የተዘረፉት ታቦተ ሕግም፤የቀደመ መንበረ ክበራቸው ጎንደር እንደሆነ መጠራጠር የማይቻል መሆኑን ማሳየት እንወዳለን። ሆኖም ታቦታተ ሕጉ ወደ ኢትዮጵያ ቢመለሱም ወደዚሁ ወደ ቀደመ መንበረ ክብራቸው ጎንደር መሄድ እንዳለባቸው ማሰሰባንች ይቀጥላል።

ሌላው ታቦታተ ሕጉ ያረፈበት የርዕሰ አደባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ በሚያስደንቅ ሁኔታ ገዳማዊ ገጽታ የሚታይበትና የንግሥት መንግድ Queens avenue #ንግሥት የሚለውን “ወትቀውም ንግሥት በየማንከ …” ከሚለው ቃለ እግዚአብሔር ጋር በማገናዘብ የቅድስት ደንግል ስያሜ በተሰጠው መንገድ፤ እንደዙሁም የቅዱስ ፊሊጵስ መንገድ St. Philip Road የመጀመሪያውን ኢትዮጵያዊ ክርስቲያን ባጠመቀው ሐዋርያ ስም በሚጠራው መስቀለኛ አራት ማዕዘን ባለው ቦታ ላይ የታነጸ ግርማ ሞገስ የተላበሰ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን መሆኑን ታሪካዊ ገጠምኑን በምንፈሳዊ ሕሊና አገናዝቦ መረዳት ግድ ነው።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *