1 0
Read Time:1 Minute, 6 Second

“የፋኖ ትግል የመጨረሻ ግብ የፖለቲካ ስልጣን መያዝ ይሆናል ማለት ነው።”

ፋኖ ሻለቃ አንተነህ

ሻለቃ አንተነህ የፋኖ አማራ Fano Amhara የምኒሊክ ብርጌድ አዛዥ በዐማራ ሕዝባዊ ግንባር ጥላ ስር ፣ በጎንደር ዙሪያ፣ በአርማጭሆና ወልቃይት ጠገዴ የሚንቀሳቀሱ ሻለቃዎችና ብርጌዶች አስተባባሪ ነው።

ሻለቃ አንተነህ የህልውና ትግሉ ከአንደኛ ደረጃ አልፎ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ተሸጋግሯል:-አንደኛ ደረጃ:- በየክፍለሃገራት የሚደረጉ የተናጠል ትግሎች ነበሩ፣ሁለተኛ ደረጃ :- ደግሞ ክፍላተ ሃገራት በቅንጅት የሚያደርጉት ትግል ነው።

ሶስተኛው ደረጃ :- ህዝቡ ሙሉ በሙሉ ትግሉን የሚቀላቀልበት ፣ በሌሎች ክልሎች ያሉ ዐማራዎችና ሌሎች ብሄሮች የሚቀላቀሉበት ምናልባትም የመጨረሻው ደረጃ ሊሆን ይችላል ሲሉ ለዐማራ ብሮድካስቲን ሴንተር (ABC) አስተላልፋል።

ከዚህ በፊት በታሪክ አባቶቻችን አገራቸውን ከጠላት ከተከላከሉ በኋላ ህጋዊ ለሆነው ለንጉሳዊ ቤተሰቦች እስረክበው ይመለሱ ነበር ። በአሁኑ ግዜ ግን የህልውና ትግል ስለሆን ፣ የዐማራ ህዝብ ዋስትና ባላገኘበትና ስልጣን ተረካቢ በሌለበት ሁኔታ ፋኖ ጦርነቱን አሸንፎ ስልጣንን ለማንም አስረክቦ የሚመለስበት ሁኔታ አይኖርም።

ስለዚህ የፋኖ ትግል የመጨረሻ ግብ የፖለቲካ ስልጣን መያዝ ይሆናል ማለት ነው። ከዚህ በፊት ለምሳሌ 2008 ላይ የዐማራ ትግል የተጨናገፈው በፖለቲካ ስልጣን መታገዝ ባለመቻሉ ነው ብለን እናምናለን።

አሁን ግን በታላቁ እስክንድር የሚመራው ሕዝባዊ ግንባር ይኼን ክፍተት ይሞላል ብለን ስለምናምን፣ በውጪ ያሉ የግንባሩ ተወካዮች ላይም እምነት ስለአለን፣ በአራቱም ግዛቶች ያሉ የተለያዩ የፋኖ ግንባር መሪዎች የትግላችን ግዜ እንዳይረዝምና ሂደቱም እንዳይወሳሰብ ስለሚያግዘን በእስክንድር ነጋ በሚመራው ሕዝባዊ ግንባር ጥላ ስር እንዲሰባሰቡ ጥሪ እናደርጋለን።

ሻለቃ አንተነህ (የምኒሊክ ብርጌድ አዛዥ )
በዐማራ ሕዝባዊ ግምባር ጥላ ስር ፣ በጎንደር ዙሪያ፣ በአርማጭሆና ወልቃይት ጠገዴ መተማ የሚንቀሳቀሱ ሻለቃዎች ብርጌዶች አስተባባሪ።
“አርበኝነት የማንነታችን አርማ ነው”

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *