በፋሺስታዊው የኦሮሙማው ጸረ አማራ ቡድን የዘር ማጥፋት ጦርነት ታውጆበት ያለን ሕዝብ ድምጽ እንሁን።

0
1 0
Read Time:1 Minute, 47 Second
የሎንዶን ፋኖዎች የፋሺስቱን ምስለኔ ሲያጋልጡ። የርሱም ምላሽ እናትህን ል…

በፋሺስታዊው የኦሮሙማው ጸረ አማራ ቡድን የዘር ማጥፋት ጦርነት ታውጆበት ያለን ሕዝብ ድምጽ ትሆኑ ዘንድ በዲሲና አካባቢው ላላችሁ የአማራ ማሕበራት የተላለፈ ጥሪ!!!

* ወንድወሰን ተክሉ*

፨ የባንክ የስልክ የመብራት አገልግሎት የታገደውን የአማራን ሕዝብ ሁኔታን ድምጽ በመሆን ለአለም ታሳውቁ

ዛሬ አማራው በፋሺስታዊው የኦሮሙማው ቡድን Under Siege የሆነ ሕዝብ ነው። በአየር በምድር የብስ ከተቀረው ዓለም ተገልሎ የባንክ የስልክ የመብራት እና የሕክምና አገልግሎት ታግዶበት በዓየር በድሮን እየተጨፈጨፈ ያለ ሕዝብ ነው።

የድሮን ጭፍጨፋው ከአራቱ አማራ ክፍላተሀገራት ውጪም በወለጋ በሚኖሩ አማራዊያን ላይ በተለይም በምስራቅ ወለጋ እያዘበ በርካታ ንጹሃንን በመጨፍጨፍ ላይ ይገኛል።

በተጨማሪም በፋሺስታዊው የኦሮሙማው እሬቻ ዝግጅት በደብረዘይት በመላው ክልል 4 በሚኖሩ ከ15 ሚሊዮን በላይ አማራዊያን ላይ ጭፍጨፋ ይፈጸም ዘንድ የአማራን ፋኖ ካላወገዛችሁ የአማራን መሪዎች እነ ታላቁን እስክንድር ነጋን አርበኛ ዘመነ ካሴን ካላወገዛችሁ እሳቱ በእያንዳንዳችሁ ቤት ይገባል በማለት የጭፍጨፋ አዋጅ ማወጁ ይታወቃል።

ይህንን ዓይነቱን ዓይን ያወጣን አረመኔያዊና ፋሺስታዊ ዘመቻን በሀገር ውስጥ ያለው ጀግናው ሕዝባችን ባለው አቅም ሁሉ የሞት ሽረት ፍልሚያ እያደረገ እንዳለ ይታወቃል። ይህንን ፋሺስታዊን ጸረ አማራ ዘመቻን ሕዝባችን ባለው አቅሙ እየታገለው ባለበት ሁኔታ እኛ በዳያስፖራ ያለን በተለይም በአሜሪካን ዲሲና አካባቢው ያለን አማሮች ድምጽ በመሆን ነገዳዊ ግዴታችንን መወጣት ያለብን መሆኑ ግልጽና ለጥያቄ የሚበቃ አይደለም።

ስለሆነም በአሜሪካን ዲሲና አካባቢው ለአማራው የምንቆረቆር ነን ብላችሁ በአማራ ስም ተደራጅታችሁ ያላችሁ ማህበራት በርካታ ብትሆኑም እስካሁኑ ሰዓት ድረስ በዚህ ጉዳይ ላይ አጀንዳችሁ በማድረግ ስትንቀሳቀሱ ስላልታየ ድምጽ መሆን በሚገባችሁ ሰዓት ስለምን ዝም አላችሁ በሚል መጠይቅ ይህንን ጥሪ ሳስተላልፍ ከዚህ በፊት ድምጽ በመሆን ሰልፍ አድርጋችሁ አታውቁም በሚል እሳቤ ሳይሆን አሁን በዚህን ሰዓት ድምጽ መሆን የሚገባ ስለሆነ ለማሳሰብ በሚል ነው።

፨ የዲሲ የጋራ ግብረ ኋይና በዲሲና አካባቢዋ ያሉ አማራ ማሕበራት ከወንድሞቻችሁ የእንግሊዝ አማራ ፋኖ ተጋድሎ ተሞክሮ ውሰዱ

በትናንትናው እለት በሀገረ እንግሊዝ ለንደን በሚኖሩ የአማራ ፋኖ በለንደን ታላቅ ትግል የፋሺስቱን ኦሮሙማን ኢንቨስትመንት ኮንፍረንስ ላይ ተገኝተው ማስተጔጎላቸውን መዘገቤ ይታወቃል። እነዚህ የለንደን አማራ ፋኖዎች ባለፈው ወር መስከረም ላይ በኤምባሲው የተደገሰን ድግስ ላይ ተገኝተው አማራ እየታረደ ሰላም ነው ብሎ መጨፈር አይቻልም ብለው ማስቆማቸውንም መገለጹ ይታወቃል።

ስለዚህ በአሜሪካን ዲሲ ይህንን ዓይነቱን ሰልፍና ትግል በማዘጋጀት የሚታወቀው የዲሲ የጋራ ግብረ ኋይል እና እንዲሁም በዲሲና አካባቢዋ ያላችሁ የአማራ ማሕበራት ከወንድሞቻችሁ የለንደን አማራ ፋኖዎች ተጋድሎ ልምድ በመውሰድ በዲሲ ተመሳሳይ የሆነ ትግል ማድረግ ያለባችሁ አሁን ዛሬ ሕዝባችን Under Siege ባለበት ሰዓት ነውና ትግሉን ታቀጣጥሉት ዘንድ ለማስታወስ እወዳለሁ።

Under Siege ያለን ሕዝብ እኛ ድምጽ ካልሆንለት ማን ድምጽ ይሆንለታል???

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *