18ኛው የብሄር ብሄርሰቦች ቀን በዓል ላይ የፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የስላቅ ንግርር ሲፈተሽ‼️
በጦርነት ላይ ያለውን የአማራን ህዝብ አሁናዊ ሁኔታን ቅንጣት ባልጠቀሰበት ደረጃ ተከበረ በተባለው 18ኛው የብሄር ብሄርሰቦች ቀን በዓል ላይ የፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የስላቅ ንግርር ሲፈተሽ‼️
* ወንድወሰን ተክሉ*
🛑 በብሄር ብሄረሰቦች በዓል መድረክ ነገዳዊ ህልውና እውቅና ያልተሰጠው የአማራ ህዝብ፤-
በየዓመቱ ህዳር 29 ቀን የሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ዘንድሮ ለ 18ኛ ግዜ በሶማሌ ክልል ጅጅጋ ተከብራል ተብሎ ሲለፈፍ እየሰማን ነው፡፡ በዚህ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ተብሎ በተሰየመው በዓል ተብዬ መዝጊያ መድረክ ላይ የክብር እንግዳ በመሆን 17 ደቂቃ የፈጀ ንግግር ያደረገቺው ፕሬዚዳንት ሳህለወርው ዘውዴ በጦርነት ላይ ስላለው የአማራ ህዝብ ቅንጣት ሳትተነፍስ ዙሪያ ጥምጥም የሚሽከረከር ንግግር አድርጋ ከመድረኩ ወርዳለች፡፡
ሆኖም ፕሬዚዳንታ 17 ደቂቃ በፈጀ ንግግሯ ተሳስታ እንኳን የአማራ ህዝብ ያለበትን የጦርነት ገጽታን ሳትጠቅስ በተለመደው የአድርባይነት አቌም አዳፍና ያለፈቺው ሆኖ ሳለ አንዳንድ ጥራዝ ነጠቅ ቫይረስ ያጠቃቸው shallow minded ካድሬ ሚዲያዎች ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘወዴ በመጨረሻ ላይ አፈረጡት እያሉ ሲዘግቡ ማየት ተችሏል፡፡
🛑 17 ደቂቃ የፈጀው የፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ንግግር በአጭር ወፍ በረር ቅኝት ሲቃኝ፤
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በጅጅጋ ተገኝንታ ባደረገቺው 17 ደቂቃ በፈጀ ንግግራ ውስጥ ለሰከንድም ያህል አማራና የአማራ ህዝብ ሁኔታ በግልጽ ተጠቅሶ አልተገለጸም፡፡ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ስላለው የድሮን ጭፍጨፋ፤ የንጹሀን እልቂት፤ የአማራ አርሶ አደር ሰብል መውደም የእምነት ተቌማት ኢላማ ተደርገው መደብደብና በአጠቃላይ በአማራ ህዝብ ላይ በታወጀው ማንነት ተኮር ጦርነት ህዝባችን በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ስር ያለ ህዝብ ሆኖ ሳለ በፕሬዚዳንታ ንግግር አንድም ቦታ አልተጠቀሰም፡፡
እለቱ የኢትዮጲያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀን ነው ተብሎ ከተገለጸበት አገላለጽ አንጻር በህብ ብዛቱ ፤ በቆዳ ስፋቱና ለፌዴራሉ መንግስት በሚያስገባው ግብር ከኢትዮጲያ አንደኛ በሆነው የአማራ ክልል በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ስር ያለና በጦርነት ስር ያለ ህዝብና ክልል ሆኖ ሳለ የሀገሪቱ ርእሰ ብሄር በሆነቺው ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ 17 ደቂቃ የፈጀ ንግግር ውስጥ የአማራ ህዝብ፤የአማራ ክልል፤ በአማራ ላይ የታወጀው አስቸኳይ ግዜ አዋጅና በአማራ ህዝብ ላይ የታወጀን ጦርነት ቅንጣት ሳትጠቅስ በአንጻሩም ስለ ኢትዮጲያ አደጋ ላይ ናት ዓይነት ቃል ደጋግማ ስትናገር ያለችበትን ሀገር የማታውቅ አሊያም ያለችበትን ሀገር ችግር የምትደብቅ አድርጔታል፡፡
በእርግጥ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ቃላትን እየተረጎሙ ፕሬዚዳንታ ስለ አማራ ጦርነት ስለአማራ መጨፍጨፍ ስለአቢይ መራሹ ኦህዴድ እንዲህ እያለች ተናግራለች እያሉ እራሳቸውን ማስደሰት ለሚሹ ደናቁርቶችና ተከፋይ ካድሬዎች በሚሆን ደረጃ 17ቱንም ደቂቃ ችግሮችን በመናገር ስለኢትዮጲያዊነት በመስበክ፤ ስለሰብ ዓዊ መብት መከበር ወዘተ ዓይነት ይዘት ባላቸው ሁኔታ በመናገር ጨርሳዋለች ብሎ መግለጽ በሚያስችል ደረጃ የገለጸች ብትሆንም አንድም ግዜ ቢሆን አማራ ብላ ህዝባችንን ያለበትን ሁኔታ ስትገልጽ አልተሰማችም፡፡
ከፕሬዚዳንቷ ንግግር ውስጥ ብሄርተኝነት እየጠነከረ እየገዘፈና ኢትዮጲያዊነት ደግሞ በአንጻሩ እያነሰ እየኮሰመነ ያለበትን ሁኔታን በመግለጽ ከፍ ከፍ ማድረግ የሚገባን ኢትዮጲያን እና ኢትዮጲያዊነትን እንጂ ብሄርተኝነትን አይደለም በማለት ያስተላለፈቺውን ስላቅ ሥሰማ እጅግ የተማረች ቢሮክራት የምትባለዋ ፕሬዚዳንት ሳህልወርቅ ዘውዴ እድሜዋን በሙሉ የሰራችበትን ህገመንግስት የማታውቅ ሰው ናትን ወይንስ ይህን ያህል የወረደ ማስመሰልን ስራ የተካነችበት ስብእና ነው ብዬ እንድጠይቅ ነው ያደረገኝ፡፡
ጎበዝ አንድ የስነ መንግስትን 101 ሀ ሁ ማወቅ የሚገባን ነገር ሀገራት ሁሉ መንግስታት አላቸው፡፡ መንግስታት ሁሉ ደግሞ ያንን ሀገር የሚመሩበት ተራማጅ ህገ መንግስት ሆነ ኃላ ቀር ከፋፋይ ሆነ አቀራራቢ ብቻ የፈለገውን ዓይነት ቢሆንም ህገ መንግስት አላቸው፡፡ መንግስታት ሀገርን የሚመሩት በሉት የሚገዙት በየሀገራቱ ባለው ህገ መንግስት ነው፡፡ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በርእሰብሄርነት የምታገለግለው መንግስት የሚመራበት ህገ መንግስት አለው፡፡ ይህ ህገ መንግስት ነው በህግ ደረጃ ዛሬ ፕሬዚዳንት ሳህልወርቅ ዘውዴ ብሄርተኝነትን እየገዘፈ ኢትዮጲያዊነትን እየኮሰመነ እና እያነሰ የመጣው እና ኢትዮጲያን እና ኢትዮጲያዊነትን ከፍ አድርጉ እያለች የተናገረቺውን ጉዳይ የፈጠረው ህገመንግስቱ ነው እንጂ ዛሬ ስልጣን ላይ ያለው ገዢ ቡድን አይደለም፡፡ ስለዚህ ብሄርተኝነት ከኢትዮጲያዊነት ይበልጥ ከፍ ብሎና ጎልቶ እንዲታወቅ በህገመንግስቱ ላይ ተጽፎ መቀመጡን የሚያውቅ ሰው – ያውም የትምህርት እጥረት የለበትም የሚባል ሰው እንደ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ዓይነት ማለቴ ነው ድንገት ከእንቅልፋ እንደባነነ ሰው ብድግ ብሎ ጫፍ በረገጠ ብሄርተኝነት ሀገር እያነሰ ብሄርና ብሄርተኝነት እያደገና እየገዘፈ ስለመጣ ኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነትን እባካችሁ ከፍ አድርጉ ብሎ ቢናገር ለአፍ ያህል ካልሆነ በስተቀር ለሰላሳ ዓመት የሰራችበትን እና የተሾመችበትን ህገመንግስትን የማታውቅ ያስብላል፡፡
ጎበዝ ዛሬ ባለንበት ሁኔታ አንዳችንም በማይፈጸሙ ጣፋጭ ቃላቶች ሽንገላ መሸንገል የምንፈልግ አይደለንም ብዬ ነው የምረዳው፡፡ ዛሬ የአማራ ህዝብም ሆነ የተቀረው ኢትዮጲያዊ ዜጋ ሊፈጸሙ የማይችሉ ጣፋጭ ቃላቶችን መስማት የማይፈልግበት ወቅትና ሁኔታ ላይ ነው ያለው፡፡ የአማራ ህዝብ የህልውና አደጋ ምንጭ ይህ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ደፍራ ልትጠቅሰው ያልሞከረቺው ህገመንግስትና ህገመንግስቱ የፈጠራቸው የጥፋት ሀይሎች ማለትም ኦህዴድ/ብ ዓዴን መራሹ የኦሮሙማው ብልጽግና መሆኑን እና ይህ ቡድን የነገደ አማራን ህዝብ ህልውናን ብቻ ሳይሆን ፈራ ተባ እያለች በዙሪያ ጥምጥም አገላለጽ ፕሬዚዳንታ አደጋ ላይ ወቅድቌል ለማለት የሞከረቺውን ኢትዮጲያዊነትንም ጭምር አደጋ ላይ የጣለ መሆኑን ሁሉም አረጋግጦ ያወቀበት ወቅት ላይ ነው የምንገኘው፡፡
ይህ ሆኖ ሳለ ብሄርተኝነትን አግዝፎና አሳድጎ ኢትዮጲያን እና ኢትዮጲይዝዊነትን አኮስምኖ እያጠፋ ያለው ፕሬዚዳንት የሆነችበት ህገመንግስትና ህገመንግስቱ የፈጠረው የጥፋት ሀይል ሆኖ ሳለ ከዚሁ ስርዓት ጋር ሆኖ በፕሬዚዳንትነት ስልጣንና ማእረግ ስርዓቱን አገልጋይ የሆነ ሰው የችግሮቹን ምንጭና ባለቤት ሳትጠቅስ ስለጦርነት ጎጂነት ስለጫፍ የረገጠ ብሄርተኝነት አደጋ ስለ ኢትዮጲያ እኩል የሁላችንነትና ወዘተ ዓይነት የተቃረነ ንግግር ማድረግ ከስላቅነት የዘለለ አይሆንም፡፡
ፕሬዚዳንቷ ስለድርቅ ስለርሃብ፤ ስለመፈናቀል፤ስለሴቶች መደፈር፤ስለእርሰበርስ ጦርነት፤ስለገዘፈ ብሄርተኝነትና ወዘተ ችግሮች ስትናገር ፈጽሞ አንድም ተጠያቂ የሚሆንን ሀይል ድርጅት ወይም ግለሰብ ስም አልጠቀሰችም፡፡
ፕሬዚዳንታ ስለ የሀሳብ ልዩነት ጠላትነት አይደለም፤ የሀሳብ ልዩነት መበረታታትና መከበር ያለበት ነው ብላ ስትናገር-፤ ዘርና ሀይማኖት ሰውን የምናጠቃበት አይደለም፤ በሀሳብ ልዩነት ብላ ስትናገር በሀሳብ ልይነትና በነገዳዊ ማንነታቸው ብቻ ተለይተው ስለታጎሩት የፖለቲካ እስረኞችና ጦርነት ተክፍቶበት በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ስር ስላለው የአማራ ህዝብ ትንፍሽ ያለቺው ነገር የለም፡፡ ፕሬዚዳንቷ የምታገለግለውንም መንግስት ገዢ ድርጅት ኦህዴድ፤ ብዓዴን፤ ወይም ለነጻነት የሚታገሉትን ታጋይ ሀይሎች ፋኖን እና መስል ድርጅቶችን ፈጽሞ ሳትጠቅስ፤ አፍራሽ የሆኑ የምትላቸውን የመንግስት ፖሊሲና አፈጻጸምን እና ከሁሉም በላይ ባለፈው ዓመት ስለተካሄደው የሰላም ስምምነት ስትገልጽ በአንጻሩም ዛሬ በጦርነት ስር ስላለው ህዝብና አካባቢ ትንፍሽ ብላ ሳትገልጽ እንዲሁ በደፈናው ሾላ በድፍኑ ዓይነት በሆነ አገላለጿ በሚንቀጠቀጥ ድምጽ የተድፈነፈኑ ችግሮችን በገደምዳሜ አነብንባ መድረኩን ለቃለች፡፡
ባለፈው ወር ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለጉብኝነት ወደ አሜሪካን በተጔዘችበት ወቅት ፋሺስታዊውን የኦሮሙማን ስርዓት በመክዳት የፖለቲካ ጥገኝነት ጠየቀች የሚል ያልተረጋገጠ ዜና ሲሰራጭ ይህ ጸሀፊ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ዳግማዊ ዳዊት ዮሀንስ ? ወይንስ ዳግማዊ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በሚል ርእስ ስር በጻፈው መጣጥፍ የቀድሞው አፈጉባኤ ዳዊት ዮሀንስ በ1989 ክረምት ወደ አሜሪካን ተጉዞ በነበረበት ወቅት ኢህ አዴግን ክዶ ጥገኝነት ጠይቌል የሚል ዜና መሰራጨቱን በመግለጽ ዳዊት ዮሀንስ ግን ከ45 ቀን ቆይታ በሀላ ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሰ ሁሉ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅም ትመለሳለች ብሎ እንደጻፈ ፕሬዚዳንታ ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ስር ዓቱን በታማኝነት እያገለገለች ያለች መሆናን ማወቅ ይገባል በማለት ጽሁፌን አቌጫለሁ፡፡አበቃሁ፡፡
Editor’s note : Views in the article do not necessarily reflect the views of Ethiopiantribune.com