ሜክሲኮ ዋቢ ሸበሌ አካባቢ የሚገኘው ሎምባርደያ ሲፈርስ የመጽሀፍ ሻጩ ህይወት አለፈ
Read Time:35 Second
ሜክሲኮ ዋቢ ሸበሌ አካባቢ የሚገኘው ሎምባርደያ ሲፈርስ የመጽሀፍ ሻጩ ህይወት አለፈ
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ያለ ምክንያት መሞትስ ??
ወንድሜ በሰላም ያገናኝን ያልከኝ ለዚህ ነው? መፀሀፍ ማንበብ መሸጥ ከልጅነት ጀምሮ የኖርክበት ሞትህ መፀሀፍ ተሸክሞ ሆነ?
ጌትነት ወንድሜ በቅርስነት የተመዘገበው ሎምባርደያ ምሽት ሲፈርስ በመጋዘን ተከራይተው ያስቀመጡትን መፀሀፍ በማውጣት ላይ ሳሉ አፍራሽ ግብረ ሀይሉ በላያቸው ላይ ቤቱን ደረመሱት።
ወንድሜ ጌትነት ከነያዘው መፀሀፍ ጀርባው ላይ የቤቱ ክምር ዲንጋይ ወደቀበት።
ጌትነት አሮጌ መፀሀፍ እየሸጠ የሚተዳደር የአንድ ሴት ልጅ አባት ነው። እስፓይናል ኮርዱ ሙሉ በሙሉ ነው የደቀቀው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ገባ አልተሳካም ወንድሜ ገና ገና መኖር ሰይጀምር ተቀጠፈ።
ቅርሱም ሎምባርደያ ፈረሰ
ወንድሜም ተቀጠፈ ?
ማነው አላፊነት የሚወስደው ማነው ?
የድሃ እንባ ይጮሃል ፈጣሪ ፍርዱን ብቻ ስጥ
ስርአት ቀብሩ ሐሙስ ጥር 02/2016 በደብረዘይት (ቢሾፍቱ )
ይፈፀማል
Via ቴዲ ባጫ