“200 ሚሊዮን ብር ጉቦ እንድንከፍል ተጠይቀናል!” ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ

0
0 0
Read Time:1 Minute, 13 Second

የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ መሰደዳቸውን ገለፁ።

የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ መሰደዳቸውን ገለፁ። ዛሬ ሰኔ 15/2016 ዓም ከአሜሪካ ሆነው በሰጡት መግለጫ የተለያዩ ጫና ሲደርስብን ነበር በተለይ የድርጅቱ አካውንት መታገዱን ይፋ ካደረግን በኋላ የተለያዩ ወንጀሎችን እኔ ላይ በመለጠፍ እኔን ለማሳሰር ጥረት ሲደረግ ቆይቷል ብሏል።

በህገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውር ትሳተፋለህ፣ ፋኖን ትደግፋለህ እና በርካታ ክሶች እንደቀረበባቸው ገልጿል።

በተለይ 200 ሚሊዮን ብር ጉቦ ከከፈልን የባንክ አካውንታችን እግዱ እንደሚነሳልን ተጠይቀን ፍቃደኛ ስላልሆንን ትታሰራለህ ተብያለሁ ሲሉ ዶ/ር ፍሰሃ ገልጿል። ስለዚህ የእኔን ደህንነት ለማረጋገጥ የመጀመሪያ እርምጃ ከሀገር መውጣት ስለሆነ ወደ አሜሪካ ተሰድጃለሁ ብለዋል።

ፍትህ እስኪገኝ ሁሉንም አማራጭ እንጠቀማለን ተስፋ አንቆርጥም ይህ ሁሉ እኛ ላይ ሲደርስ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ያውቃሉ ብዬ አላስብም ብለዋል። ስለዚህ ጠቅላይ ሚንስትሩ ጣልቃ ገብተው በመጀመሪያ ደረጃ እኔ ሀገሬ ገብቼ እንድሰራ እና ለድርጅቱ የሰላም ዋስትና እንዲሰጡኝ እጠይቃለሁ ከእሳቸው ውጪ ማንንም አላምንም ብለዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩን ለማግኘት ሶስት አመት ሙሉ ጠይቀናል እሳቸውን ማግኘት አልቻልም፣ እሳቸው ወደ እኛ መጥተው ሊያነጋግሩን ይገባ ነበር ከተበደልን በኋላ ዝም ሊሉን አይገባም ነበር የ1600 ሰራተኞች ደሞዝ መክፈል አንችልም ጾሙን ማደር የለበትም ሲሉ ዶ/ር ፍሰሃ ቅሬታቸውን ገልጿል።

በሰላም መስራት ነው የምንፈልገው፣ ከማንም ጋር መጣላት አንፈልግም የእኛ መርህ ኑ አብረን እንስራ ነው የተፈጠረው በሰላም ይፈታ ብለዋል። በቀጣይ በሽምግልና ችግሩ እንዲፈታ እናደርጋለን እንዲሁም የአሜሪካ ኤምባሲ ጣልቃ ገብቶ ከመንግስት ጋር መነጋገር የሚቻልበት አማራጭ እንደሚፈልጉ ተናግሯል።

ባለ አክሲዮኖች ተረጋጉ እስከመጨረሻው ድረስ እንታገላለን ፍትህ እንድናገኝ ሁሉም ድምፅ ማሰማት እንደሚገባው መልዕክት አስተላልፏል።

በመላው አለም የሚገኙ ዜጎች በፍቃደኝነት በውጪ ሀገር በተከፈተ አካውንት ድጋፍ እንዲያደርጉ የችግር ጊዜ አብራችሁን እንድትቆሙ ብለዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *