” ሳይሞከር የከሸፈው መፈንቅለ መግስት በኢትዮጵያ “

ከአለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ለንደን)
እንደምን አላችሁልኝ ወዳጆቼ ! !
ወታደራዊ ኢንፎርማቸውን እስክ ክንዳቸው ድረስ ጠቅልለዉ ግራ እጅችውን ጭብጥው እያወዛወዙ
” አብዮታዊት እናት ሐገር ወይንም ሞት ! “
በማለት ለአስራ ሰባት አመት ኢትዮጵያን የመሩት አብዮተኛው ሌ/ኮሎኔር (ፕሬዝዳት ) መንግስቱ ሐይለማሪያም በአንድ ወሳኝ ወቅት ኢትዮጵያና ህዝቧን እሳት ላይ ጥደው ቤተሰቦቻችውን ይዘው
አገር ጥለው እብስ ጥርግ አሉ: :
ኢትዮጵያም በትግራይ ወያኔወች እጅ ወደቀች : :
ጊዝው 1983 ዓ/ም መሆኑን ታሪክ መዝግቦታል
እናም ፕሬዝዳንት መንግስቱ ሐይለማሪያም
ምእራባውያን መንግስታት ኮሚኒስቱ አምባገነን በማለት ከሚጠርቸው ሮበርት ሙጋቤ አገር የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበው
ቀሪ ህይወታቸውን ዚምባብዌ ውስጥ እየኖሩ ይህው 84ኛ አመት የልደት በአላቸውን በቅርቡ አክብረው ውለዋል : :
ወዳጆቼ. ለዛሬው ብዕርሬን ያስጭብጥኝ ጉዳይ ስለ ቀድምው ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃይለማሪያም የስልጣንና የስደት ህይወት ልነግራችሁ ፈልጌ አይደለም: :
በቅርቡ በሌ/ኮሎኔር. በላይነህ ታዬ ተፅፎ ለህትመት የበቃው ” ዝሆኑን በሴራ ” የተሰኜውን መፅሐፍ በደራሲው ተፈርሞ በውድ ጏደኛዬ በኩል በፖስታ ሲደርሰኝ ከኮሎኔር በላይነህ ታዬ
ጋር የነበርንን ወድጅነት ትዝታዬን ቀሰቀስብኝ ::
እናም መፅሐፉን አንብቤ ስጨርስ የግል ምልከታዬን አጋራችሁ አለሁ ::
እስከዚው ትዝታን በፌስቡክ ላጫውታችሁ: :
ከመፅሀፉ ደራሲ ሌ/ኮሎኔር በላይነህ ታዬ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቅነው በቀይ ኮኮብ
ዘመቻ በ1974 ዓ/ም አስመራ ነው : :
ዝርዝሩን ለጊዝው ላቆየው : :
ኮሎኔር በላይነህ ታዬ በእድሜም በወታደራዊ ማአረግም ይበልጠኛል: : ነገር ግን በላይነህ በስልጣኑ የሚኮፈስና የበታቾቹን የሚንቅ ሰው ባለመሆኑ አብዛኛው ወጣት መኮነኖችና፣ የበታች ሹሞች ፣ ወታደርች ፣ ጭምር በአክብርት ይወዱታል: :
በታሪክ አጋጣሚ ከነዚህ ወዳጆቹ ውስጥ አንዱ ነበርኩ : : እሱ ሌ/ኮሎኔር ..እኔ ደግሞ መቶ አለቃ : :
በመጨረሻም ሁሉም ነገር .. አልፎ
ሁለታችንም የምንሰራው አድስ አበባ
አራት ኪሎ በሚገኜው ህንፃ ውስጥ በመሆኑ እንደገና ተመልሰን ተገናኜን : :
አንድ ቀን ጧት ወደ ቢሮዬ ልገባ ደረጃው ወጥቼ ስጨርስ ፣ ነፍሱን ይማረውና ከታዋቂው ጋዜጠኛ መፅሐፈ ሲራክ ጋር መተላልፊያ ኮሪደሩ ላይ ተገናኜን: :
ቢሯችን ፊት ለፊት ትይዩ ስለነበር የሆነ ነገር ከሱ መውስድ ስፈልግ. በነፃንት እንደልቤ ገብቼ እወጣለሁ: :
የዚያን እለት ጧት ስንገንኝ ሰላምታ ከተለዋወጥን በዃላ እጄን ይዞ ልነግርህ የምፈልግው ጉዳይ አለ በማለት ወደ ቢሮው አብረን ገብተን በሩን ከውስጥ ቆለፈው : :
ከዚህ በፊት መፀሐፈ ሲራክን የሚክል መረጃን አፈንፍኖ የሚያድን ብዙ ልምድ ያለው በሳልና አንባቢ ጋዜጠኛ አላጋጠመኝም ነበር : :
እኔም. በጋዝጠኝንት የምስራው ጦር ሐይሎች ሬድዮ ፕሮግራም ውስጥ በመሆኑ መፅሐፈ ሲራክን የመሰሉ በሳል ጋዜጠኞ የልብ፣ወዳጅ አድርጎ ልምዱን መማር ያስደስተኝ፣ስለነበረ ከስራ በዃላም ጎራ ወደሚልባት ማምሻ ቤት አልፎ አልፎ እየተገናኜን ብዙ የህይወት ተሞክሮዎቹን አጫውቶኛል : :
ዛሬ ግን መረጃውን ከመንገሩ በፊት ከወትሮው ለየት ባለ ሁኔታ በማስጠንቀቂያ እንዲህ ሲል ጀመረ : :
አንድ ጥብቅ መረጃ ልነግርህ ወስኛ አለሁ አለኝ::
ጅሮወቼ ቆሙ :: ምንድ ነው አልኩት?
እንደምታውቀው የከሸፈው የግንቦት ስምንቱ መፈንቅለ መንግስት ጄኔራሎች መወሰን አቅቷቸው መከላከያ ሚ/ር ውስጥ ተሰብስበው የእሳት እራት ለምን እንደሆኑ ታውቃለህ? በማለት ጠይቆ ንግግሩን ቀጠለ : :
አንድ መፈንቅለ መንግስት ሲዘጋጅ መሟላት የሚገባውን ቅድመ ዝግጅትና ጥንቃቄ አላደረጉለትም ::
ስልጣናቸውን ብቻ ተመክተው የሚደርሳቸውን መረጃ በአግባቡ መጠቀም ስላልቻልና በሚሰጡት የዘገየ ውስኔ ተበሉ : :
አሁንም ተመሳስይ ነገር እንደገና ሊደገም ነው
አለኝ : : የታቀደው ሁለተኛው መፈንቅለ መንግስት ቀድሞ ጭምጭምትው መሰማቱ ያሳሰበው ይመስላል: :
ምን ተፈጠረ ሌላ ኩኔታ ሊኪያሒያድ ነው ?
ስል ጠየኩት?:: መፅሐፈ ቀጠለ
ወዳጄ ” ይህንን መረጃ አሳልፈህ ለሰው ብትናገር በሕይወትህ እንደፈረድክ ቁጠረው አለኝ ::
በዚህ ጊዜ ደነገጥኩ ! !
መቼም ወሬውን ሰምቼ ዝም እንደማልል ያውቃል የነብር ጅራት ከያዙ አይለቁ ሆኖብኝ ክትትሌን በሚስጥር ቀጠልኩ : : ብዙ ስልኮች ወደ ተለያዩ ቦታወች ደወልኩ: : ብዙ የማውቃቸውን ወታደራዊ መኮንኖች ለማነጋገር ሞከርኩ ነገር ግን መፃፉም ዝም ቄሱም ዝም ሆነብኝ : : የእነትናን ጠባሳ ያዬ በእሳት አይጫወትም ይባል የለ : :
አንድ ቀን ምሳ ስአት ላይ መኪና መንገድ ሳቋርጥ ሌ/ኮሎኔር በላይነህ ታዬና ኮሎኔር ቦረና ወርዶፋን አብረው ምሳ ለመብላት ሲሔዱ አገኜዃቸው: :
የእግዚአብሔር ሰላምታ አቅርቤ አብሪያቸው ተቀለቀልኩ. :: ነፍሱን ይማረውና ኮሎኔር ቦረናም
ቢሆን ይወደኛል : :
እየተጭዋወትን አንድ ላይ ምሳ ተመግበን ስንጭርስ
ከኮሎኔር በላይንህ ታዬ ጋር አልፎ አልፎ አብረን የምናመሽበት ቤት ከስራ በዃላ እንድንገናኝ
ተቀጣጥረን ተለያየን ::
ኮሎኔር በላይነህ ታዬ የሚገርም ሰብዕና ያለው ሰው ነው :: ከማምናቸውና ከማደንቃቸው ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ውስጥ አንዱ በመሆኑ ስንገናኝ ጋዜጠኛ መፀሐፈ ሲራክ የነገረኝን መረጃ በሚስጥር ላካፍለው ወስኛለሁ ::
ይህንን ድፍረት ያገኜሁት ብዙ ጊዜ የማይመስለኝን ነገር ስቃወምና እውንቱን ስናገር
በሚገጥመኝ የማይመቹ የስራ አታካሮዎች ላይ በሚደርስቡኝ ተፅዕኖወች እንደ ሻለቃ ክፍሌ አቦቸርና እንደ ኮሎኔር በላይነህ ታዬ የመሳሰሉ ተቆርቋርወች ባይኖሩኝ፣ኑሮ ብዙ የስቃይ አመታቶችን አሳልፍ ነበር ::
ለዚህ ነው ይህንን ጉዳይ ብንግረው በላይነህ አሳልፎ አይሰጠኝም የሚል እምነት ያደረብኝ ::
እናም ተገናኝተን ቢራችንን እየተጎነጨን ደስ ብሎን አመሸን : :
ልንሰነባበት ጥቂት ጊዜ ሲቀሩን ” ያበጠው ይፈንዳ ” በማለት የሰማሁትን እንዲህ በማለት
አጫወትኩት: :
በላይነህ ምን ያህል እንደማከብርህና እንደምወድህ ታውቃለህ ስለው ?
በሚገባ ነው እንጂ በማለት አረጋገጠልኝ: :
ይህንን ሚስጥር የነገረኝ፣ሠው እንዲህ በማለት አስጠንቅቆኛል : :
” መረጃውን ለሌላ ሰው አስልፍህ ብትናገር በሕይወትህ እንደፈረድክ ቁጠር
ብሎኛል አልኩት :: የጄኔራሎቹን መፈንቅለ መንግስት እያስብኩ : :
መልስ ስይሰጥ ዝም ብሎ አዳመጠኝ ::
” በቅርቡ በወጣት መኮንኖች የተቀነባበረ መፈንቅለ መንግስት ሊያደርጉ ታስቧል የሚል መረጃ ደርሶኛል አልኩት ::
ኮሎኔር በላይነህ ፊቱ ሲለዋወጥ ትዝ ይለኛል: :
ሁኔታውን ቀለል አርጎ ለማለፍ አስቦ ነበር : :
ነገር ግን መረጃውን የሚሰማው ከሌላ ሶስተኛ ወገን ሳይሆን በወቅቱ ፣ከብዙ ታዋቂ የኪነጥብ ሰወች. …ከብዙ ጋዜጠኞች … ከከፍተኛ ባለስልጣኖች ጋር እንደምግናኝ ጠንቅቆ የሚውቀኝ አለባቸው ነኝ: :
ምንም እንኳን አለቃዬ ቢሆን ዝም ብሎ መረጃውን አጣጥሎ ሊያልፈው እንደማይፈልግ ገምቻለሁ : : በዚህ ላይ የሰለጠነ መርማሪ ፖሊስ መኮነን ፣ እንደነበረም አትርሱ: :
ብቻ ጥቂት ፀጥታ በሁለታችንም መካከል ሰፈነ : :
በላይነህ ሐሳቦቹን ሰብስቦ በተርጋጋ ሰሜት ማነው መረጃውን የነገረህ በማለት ጠየቀኝ ?
እኔም እስከ አሁን ድረስ ቃሌን ጠብቄ መረጃውን ማን እንደነገረኝ ሳልነግረው አመታት ተቆጥረው አልፈዋል ::
እሱም ካልንገርከኝ ብሎ አላስቸግርኝም ::
ምክኒያቱም ጋዜጠኛ መፀሐፈ ሲራክ ከብዙ ባለስልጣኖች ጋር እንደማይግባባ ያጫውተኝ ስለነበረ በምንም ምክኒያት አሳልፌ ልሰጠው አልፈልግም ::
በመጨረሻ እራሱ ኮሎኔር በላይነህ አመነልኝ: :
ሌላ መፈንቅለ መንግስቱ ሊደረግ እንደታሰበና አመራር ከሚሰጡት ወታደራዊ መኮን
ኖች ውስጥ አንዱ እሱ እንደሆነ በዝርዝር አጫወተኝ : :
አሁን ገና በጣም ደነገጥኩ: :
ባልገመትኩትና ባልጥበኩት ሁኔታ ትክክለኛውን መረጃው እንዳገኜሁ ሳረጋግጥ ..በሌላ በኩል ደግሞ ጋዜጠኛ መፀሐፈ ሲራክ የፈራው ነገር ደረሰ : :
በግራ ጎኑ የተቀባበለ ኮልት ሽጉጥ የታጠቅን የጦር መኮነን ባለማወቅ መንግስት ለመገልበጥ እያሴረ መሆኑን ተከታትዬ የደረስኩበት በመምስል ፊት ለፊት
በድፍረት ቁሜ ስነግረው ምን ሊፈጠር እንደሚችል ገምቱና !!
እናንተስ በኔ ቦታ ብትሆኑ ውሳኒያችሁ ምንድ ነው ?
አሁን ሁሉም ነገር ግልፅ ሆኗል ::
ከዚህ በዃላ የኔ ጉዳይ ያአለቀለት መሰለኝ: :
የፈሰ ውሀ አይታፈስም …. ::
ነገሩን መልሼ እንደማላስተካክለው አውቃለሁ
የእጆቹን እንቅስቃሴ እየተጠባበኩ
ታዲያ ለምን አልነገርከኝም በማለት በድፍረት ጠየኩት ? ኮሎኔር በላይነህ ከአቀራረቤ ጀምሮ
በተንኮል እየተፈታተንኩት እንዳልህነ ገብቶታል : :
ለስለስ ብሎ ንግግሩን ቀጠለ ::
” በመጨረሻ መስማትህ አይቀርም ብዬ ነው አለኝ በፈገግታ ::
ምናልባት ዜናውን የምትሰራው አንተ ሳትሆን ትቀራህ በማለት :: በቀልድ ሊያረጋጋኝ ሞከረ ::
ሳላስበው ሳቄ መጣ ፣….ጭራሽ ዜናውን ! ስለው ሁለታችንም የሚገርም ሳቅ ተሳስቀን ተሰነባበትን : :
እውነቱን ለመናገር ለሊቱን ሙሉ ብዙ ነገሮች በአዕምሮዬ እየተመላለሱ አልጋዬ ውስጥ ስገላበጥ እንቅልፍ ሳይወስደኝ ነጋ : :
አሁን በላሁበት እድሜ ሁኜ ሳስበው የነገሮቹ ሁሉ መገጣጠም ለራሴ መልሶ ይገርመኛል ::
ሌላ ስው ቢሆን ምን አይነት እርምጃ ሊወስድብኝ እንደሚችል መገመት አልቸገርም : :
ሳስበው ግን ኮሎኔር በላይነህ ታዬ በምርጫ የተፈተነበት ስአት ይመስኛልኝል ::
እኔም አሳልፌ እንደማልሰጠው ተማምኖ ምንም የከፋ እርምጃ ሳወስድ ሁሉም በነበር. አልፎ ፍቅርቻንና ወንድማማችነታችን ፀንቶ አሁንም ድረስ ትዝታ ሆኖ አብሮን ይኖራል : :
ለመጨረሻ ጊዜ የተለያየ ነው ከጦላይ የተሀድሶ እስር ቤት አምልጨ ለንደን ስገባ አድራሻየን ከሐገር ፍቅር ጏደኞቼ ወስዶ እንዲህ በማለት ፃፈልኝ: :
” አለባቸው ደሳለኝ ከቶ የአንተን ነገር ከየት እንደምጀምር ግራ ገብቶኛል ::
ከጦላይ አምልጠህ አዲስ አበባ መግብትህ ሲገርመኝ ጭራሽ ሜዲትራንያን ባህር
አቋርጠህ ለንደን ገባህ? ሲል ይድነቃል : :
ከ30 አመት በዃላ በለውጡ ሰሞን ተመልሼ ሐገሬ መግባቴን በቴሌቪዥን ተከታትሎ በሰወች አማካኝነት አፈላልጎ ተገናኜን : :
ስለዚህ ወደፊት ” ዝሆኑን በሴራ” በሚለው መፅሐፍ ውስጥ በማቀርባችው ምልከታወቼ አንዱ የትውልድ ምስክር ሆኜ እቀርባለሁ: :
እስከዚያው ግን ከደራሲው ጋር የነበረንን ወዳጅነት በስሱ፣ ስዕሉን ለማሳየት ሞክርያለሁ ::
በቀጣዩ ዝግጅቴ እስከምንገናኝ ቸር ይግጠመን