አጀንዳዬን አልቀይርም…!

0

ቲክቶከሩ ፍርድ ቤት ቀርቦ በፍርድ ቤት ፖሊስ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆበት የነበረ እና ፍርድቤቱም ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ፈቅዶለት የነበረ ቢሆንም በመሃል ግን በዛሬው ዕለት የኦሮሞ አባ ገዳዎች ነን ያሉ የምሥራቅ አሩሲ ኗሪ አባ ገዳዎች መኪና ሞልተው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የኦሮሙማ መንግሥታቸውን በገዳ ሥርዓት መሠረት ሽምግልና ጠይቀው ከፍርድ ቤት ቀጠሮ በፊት ዛሬ ምሽት ከፖሊስ ጣቢያ አማላጅ ሆነው፣ በዚያውም የገዳ ሥርዓት ማስታወቂያ ተሠርቶለት ተጠርጣሪው ከእስር እንዲወጣ መደረጉ ነው የተሰማው።

1 0
Read Time:3 Minute, 16 Second

ከመምህር ዘመድኩን በቀለ

“…ትናንት አርሲ መርቲ ጀጁ ወረዳ ከቦሌ ወደ አቦምሳ ሲጓዝ የነበረን የትራንስፖርት መኪና አስቁመው የኦሮሞ ወሀቢይ እስላሚስቶቹ ተሳፋሪዎቹን እና ረዳቱን ይዘው ሲሄዱ ሹፌሩን እዚያው ማረዳቸው ተነግሯል። ሌላም ሀንቀሎ ዋቤ ወረዳ ሃታት ቀበሌም ላይ አንድ ኦርቶዶክሳዊ መተራዱም ተሰምቷል። ጭፍጨፋው እንደቀጠለ ነው።

“…ይሄንን የኦርቶዶክሳውያን የእርድ እና የዘር ጭፍጨፋ አጀንዳ ለመቀልበስ፣ ለማስቀየስም ሲባል የኦሮሞ ብልግና ፓርቲ ቀድሞውኑ የነዳጅ ጭማሪውን አጀንዳ ለማስቀየስ እና ሕዝቡን በአጀንዳ ለማጇከብ ሲሉ ውኃ በማያነሣ ክስ ራቁታቸውን ከወጡ ቲክቶከሮች ጋር አጃምለው ያሰሩትን ካናዳዊውን የሰግጥ ፈምስ፣ ደድብ ባለቤት ቲክቶከር አዶናይን ዛሬ ምሽቱን ከእስር ቤት ፈትተው ለቀውታል። ያውም በጭለማ 😂

“…ቲክቶከሩ ፍርድ ቤት ቀርቦ በፍርድ ቤት ፖሊስ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆበት የነበረ እና ፍርድቤቱም ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ፈቅዶለት የነበረ ቢሆንም በመሃል ግን በዛሬው ዕለት የኦሮሞ አባ ገዳዎች ነን ያሉ የምሥራቅ አሩሲ ኗሪ አባ ገዳዎች መኪና ሞልተው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የኦሮሙማ መንግሥታቸውን በገዳ ሥርዓት መሠረት ሽምግልና ጠይቀው ከፍርድ ቤት ቀጠሮ በፊት ዛሬ ምሽት ከፖሊስ ጣቢያ አማላጅ ሆነው፣ በዚያውም የገዳ ሥርዓት ማስታወቂያ ተሠርቶለት ተጠርጣሪው ከእስር እንዲወጣ መደረጉ ነው የተሰማው።

“…አሁን ምሽቱን በቲክቶክ መንደር የሰግጥ መፈታት የፌስቡኩንም ሰፈር በሰበር ዜና እንዲጥለቀለቅ ተደርጓል። አዳሜና ሔዋኔ ከምሥራቅ አሩሲ ክርስቲያኖች ከሚታረዱበት ምድር የመጡና ከፍርድ ቤት በላይ ሆነው ለወጉ ያህል እንኳ የፍርድ ሂደቱን አክብረው ለማሳየት ትእግስት ያጣው ቡድን ማኖ ነክቶ ሲምበጫበጭ አክቲቪስቱና ቲክቶከሩ ሁላ ደግሞ “የገዳ ሥርዓት ፍቅር ነው” እያለ ነው። የትግሬ አክቲቪስትና የቲክቶከሩ አድናቂዎች ፌሽታ ላይ ናቸው። ሲጀመር ልጁን ያሰሩት ለነዳጅ ጭማሪው ማስቀየሻ አጀንዳ ብለው ነበር እናም ይፈቱታል የልጁ እስርም አሳማኝ አይደለም ብለን አስቀድመን የተናገርነው ነው ዛሬ ምሽት የተፈጸመው። ነውርን አስሮ ማጀገን ነበር የተፈለገው። አድርገውታል ልጁ ግን ከዚህ በኋላ አዲዮስ ከሽፏል።

“…በኋላኛው ዘመን የዘመኑ ፍጻሜም በደረሰ ጊዜ በነፃ ዝውውር የትግሬዎቹ አክቲቪስት ወደ መሆን የተሸጋገረው፣ መቀሌ ድረስ በመሄድም የተሸለመው የሀረርጌው መራታ ደሩ ዘሀረሩ እና ሌሎችም የኦሮሞ አክቲቪስቶች የተናገሩትን አስምሩበት። እንዲህ ነው ያሉት። “…ሕወሓቶች አዶናይን ልክ እንደ ሀጫሉ ሁንዴሳ ገድለው የተበታተነውን የትግሬ ፖለቲካ እና ፖለቲከኛ ወደ አንድነት ሊያመጡበት አቅደው ነበር። ብልፅግና ያ መረጃ ስለደረሰው ነው ልጁን በቶሎ ይዞ ያሰረው” በማለት ነበር ሲናገሩ የነበረው። እዚህ ጋር ያዙልኝ።

“…ስለዚህ ቲክቶከሩ ከሰማ ይመከር። እንደኔ እንደኔ ልጁ በዜግነት ካናዳዊ ነው። እኛ የማናውቀው ነገር ኖሮ ወደ ካናዳ ለመመለስ የማያስችለው እና ኢትዮጵያ የሚያስቀረው ጉዳይ ከሌለ በቀር ቶሎ ቢነካው መልካም ነው ባይ ነኝ። ያውም ከፍርድ ቤት ቀጠሮ ውጪ የፍርድ ቤትን መብትና ክብር ጥሰው፣ የሕግ የበላይነትን ደፍጥጠው ሲያበቁ ከምሥራቅ አሩሲ፣ ከሻሸመኔ በመጡ አባ ገዳዎች፣ በእነ ማይኮ ቲክቶከር እና በባልየው ማንትስ ቢሊየነር አማካኝነት አስቀድመው በማይኮ በኩል ሲዝቱበት የቆዩትን ቲክቶከር ዛሬ ደግሞ በአንደዜ ተለውጠው ሽማግሌም ሆነው ያስወጡትን ሰዎች ብዙም ባያምናቸው ጥሩ ነው ባይ ነኝ። ቲክቶሩ ከተቻለው በዜግነት ካናዳዊ ነውና በቶሎ ወደ እናት ሀገሩ ካናዳ ቢመለስ መልካም ነው ባይ ነኝ። ያለበለዚያ ሁለቱም ወያኔም ኦህዴድ ኦነግም ቁማር ነው የሚጫወቱበት። ወያኔ ሀውዜን ላይ ደርግ በጀቴ ሕዝቡን እንዲጨፈጭፍ አስደርጋ ትግሬን ከጎኗ እንዳሰለፈች፣ ኦህዴድም ወለጋ ላይ ዐማራን አርዶ፣ ፓርላማ ጠርቶ፣ ዐማሮችን አስለቅሶ፣ በወያኔ ላይ ሀገሩን ሁሉ አሰልፎ፣ እነሀጫሉን ሰውተው ፖለቲካ እንደሠሩት አዶናይንም ጭዳ እንዳያደርጉት እሰጋለሁ። ለሀጫሉ ያልራሩ ለዚህ ይራራሉ የሚል እምነት የለኝም። ምክር ነው። ምክሬ ይደብራል፣ ይጎመዝዛል፣ ነገር ግን ጨክኖ ምክሬን መዋጥ ፈውስ ይሰጣል።

“…በሌላ በኩል ሰሞኑን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም እና ብሔራዊ ባንክ እስከ ሚያዚያ 30 በግዳጅ እንዲተገበር ባወጡት action plan መሠረት ሁሉም ባንክ የሚጠቀሙ ደንበኞች ሒሳባቸውን በፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ካላዘመኑ ሒሳባቸውን መጠቀም እንዳይችሉ ጥብቅ መመሪያ አስተላልፏል። ባንኮችም ጥብቁን መመሪያ እየተገበሩት ይገኛሉ።

“…አሳሳቢው ነገር ለቴሌና ሳፋሪኮም የተሰጠው ጥብቅ ትእዛዝ ነው። ይኼውም መመሪያ የእያንዳንዱ ሰው ስልክ ቁጥር በፋይዳ እንዲተሳሰር እና በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልተሳሰረ አገልግሎቱ እንዲቋረጥ ማዘዙ ነው። በተለይ በተለይ በዚህ ደግሞ የዐማራ ፋኖ እና የፋኖ ደጋፊ የመረጃ ሰዎች ከባድ ችግር ይገጥማቸዋል ተብሎ ይሰጋል። ፋኖዎችም እንደ ዋትስአፕ እና መሠል የማኅበራዊ ሚዲያ አፖችን ለግኑኘት ካልተጠቀሙ በቀር ከባድ ይሆናል። ይኼም ቢሆን የኔትወርክ ችግር ሊኖር ስለሚችል ውጤታማ ላያደርጋቸው ይችላል። ስለሆነም ዘመዴ ምናልባት ይሄ መልእክት እንደ መረጃ ከጠቀማቻው መልእክቱን ብታጋራቸው እና ከወዲሁ ሌላ አማራጮችን እንዲያስቡ ቢደረግ መልካም ነው የሚል መረጃን ወፎቼ አድርሰውኛል። ይሄ መረጃ አስቀድሞ የደረሳቸው የጎጃም ፋኖዎችም መግለጫ አውጥተው አይቻለሁ። ምንአልባትም ከዚህ በኋላ ፋኖም ባንኮችን ሳይነካ መጠበቁ ቀርቶ ልክ እንደ ኦነግ ሸኔ ለዘረፋ እንዳይነሳሳ እሰጋለሁ። በመጨረሻም መልእክቴ አንድና አንድ ነው።

• እኔ በበኩሌ አጀንዳ አልቀይርም ‼

• በአሩሲ የኦርቶዶክሳውያን ጭፍጨፋ ይቁም‼

መምህር ዘመድኩን በቀለ ብዙ ተከታይ ያፈራ ተፅእኖ ፈጣሪ እና ብሮድካሰተር ነው። ከላይ የተገከፁት አሰተዉሎዎች የተወሰዱት በፀሐፊው ተዘጋጅቶ ከቀረበው ከቴሌግራም ቻነሉ ነው። The views expressed are his own.

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *