ምርጫ ቦርድ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ አላከብርም ብሏል” – ባልደራስ ፓርቲ

0
0 0
Read Time:51 Second

ምርጫቦርድለባልደራስየሰጠውምላሽምንድነው ?

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት እነ አቶ እስክንድር ነጋን በተመለከተ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እጩ እንዳይሆኑ ሰጥቶት የነበረውን ውሳኔ በመሻር እንዲመዘገቡ ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል።

በውሳኔው መሰረት የባልደራ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በዕጩነት ለማስመዝገብ እና እንደ ፍርዱ እንዲፈፀም ለምርጫ ቦርድ በደብዳቤ የተጠየቀም ቢሆንም ምርጫ ቦርድ ውሳኔ እንደማይፈፅም በደብዳቤ ምላሽ ሰጥቷል።

ይህን ተከትሎም የባልደራስ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል ሲል ፓርቲው በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

ምርጫ ቦርድ ለባልደራስ የሰጠው ምላሽ ምንድነው ?

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በህግ ጥላ ስር ያሉ የፓርቲው ዕጩዎች የሆኑት አባላት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 207000 ግንቦት 13 ባሳለፈው የፍርድ ውሳኔ መሰረት እንዲመዘገቡለትና ቦርዱ እስከ ግንቦት 19 ድረስ ተገቢውን ትዕዛዝ ለምርጫ ወረዳዎች አስተላልፎ እንደ ፍርዱ እንዲፈፀም ጥያቄ ማቅረቡን ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

የዕጩዎች ምዝገባ የካቲት 30 በመጠናቀቁ እና አንዳንድ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የሚኖረውን ስፍራ የሚወስን የሎተሪ ዕጣ በመውጣትና በዚሁ መሰረት የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ህትመትም ተጠናቆ ወደ ምርጫ ጣቢያ የመላኩ ተግባር በቅርብ ጊዜ የሚጀመር በመሆኑ እንደውሳኔው ለመፈፀም ቦርዱ የሚቸገር መሆኑን ገልጿል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *