0 0
Read Time:37 Second

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሀብታቸውን በማስመዝገብ የሀብት ምዝገባ ሰነዳቸውን ለፌዴራል ሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስረከቡ።

የፌዴራል ሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሙስናን ለመዋጋት ሰፋፊ ሥራዎችን እየሠራ ነው ያሉት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የሀብት ማስመዝገብ ሥራው ሙስናን ለመከላከል እና ለመዋጋት ትልቅ መሣሪያ ነው ብለዋል።

አክለውም ሙስናን የመዋጋት ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል በአዋጁ መሠረት ሁሉም የመንግሥት የሥራ ሓላፊዎች እና በየደረጃው የሕዝብን ሀብት የሚያስተዳድሩ ባለሞያዎች ከሥራ ባሕርያቸው አኳያ ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ይደረጋል ብለዋል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት የፌዴራል ሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሥራውን አጠናክሮ መቀጠል እንዲያስችለው ተጠሪነቱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሆን መደረጉን አፈ ጉባኤው ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል እና አገሪቱ ያላትን ሀብት በቁጠባ እና በተገቢው መንገድ ሥራ ላይ ለማዋል እንዲያስችል የሚመለከታቸው አካላት ሀብት የማስመዝገብ ሥራውን ማከናወን እንደሚገባቸው አቶ ታገሰ አሳስበዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *