በዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበራት በኩል የቀረቡ ጥያቄዎች

0
0 0
Read Time:47 Second

#የዩኒቨርሲቲ_መምህራን

መንግሥትን የደመወዝ ጭማሪ እና የዕርከን ዕድገት እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

• ለዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ እና ቴክኒካል ረዳቶች የተሰራውን አዲሱን የስራ ደረጃ ማሻሻያ JEG በተመለከተ ቅሬታ አላቸው።

• የመምህራን የቤት አበልን በተመለከተ በፍጥነት አሁን ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ ከግምት አስገብቶ ተሻሽሎ ተግባራዊ እንዲደረገ ጠይቀዋል።

• በመንግስት የተደረገው የደረጃ ማሻሻያ ረጅም ጊዜ በዩንቨርሲቲ ያስተማሩ መምህራንን ልምድ ያላገናዘበ በመሆኑና በመምህራን መካከል በቀጣይ ፍትሀዊ የደምወዝ ልዩነት እንዲኖር ስለማያስችል የደረጃ ማሻሻየው የመምህራንን ልምድ እና ማዕረግ ያገናዘበ እንዲሆን ጠይቀዋል።

• የረዳት ፕሮፌሰር የአካዳሚክ ማዕረግ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ የ3ኛ ዲግሪ መደረጉን በተመለከተ ያለን ቅሬታ አላቸው።

• የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳቶች ዝቅተኛው ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ የመጀመሪያ ዲግሪ መሆኑ ላይ አቤቱታ አላቸው።

• የቺፍ ቴክኒካል ረዳት II የትምህርት ደረጃን ፒ ኤችዲ ዲግሪ መሆኑም ላይ አቤቱታ አላቸው።

ጥያቄዎቻችን መልስ ይሰጣቸው እያሉ የሚገኙት መምህራኑ ይህ ካልሆነ እስከ ስራ የማቆም አድማ መምታት ድረስ ዕርምጃ እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ለሪፖርተር ጥያቄ እንዳለ እናውቃለን። ነገር ግን አሁን ላይ ለውጦች ለማምጣት ጥናት እየተካሄደ ነው። ከዚህ ባለፈ የምንለው ነገር የለም። የደመወዝ ጉዳይ የትምህርት ሚኒስቴር ብቻ አይደለም የሲቪል ሰርቪስ ጉዳይም ነው

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *