0 0
Read Time:5 Minute, 47 Second

ማይዝለው ሁለገብ የስፖርት ሰው- እዮብ ተሰማ
ትውልድና እድገቱ አዲስ አበባ ነው። በሳንፎርድ እንግሊዝ ትምህርት ቤት ተምሯል። በእግር ኳስ ስፖርት መነሻውየቀድሞው ዝነኛ ክለብ አየር መንገድና ጥቁር አንበሳ ወጣት ቡድኖች ነበሩ:: ከነዚህ ክለቦች ጋር ከልጅነቱ አንስቶየጠበቀ ቁርኝት ኖሮት ነው ያደገው። የብሔራዊ ቡድን ተጫዋች በነበረው ዝነኛው ገረመው ዘርጋ ከልጅነቱአንስቶ በሚገባ ተገርቶ አድጓል፡፡ ‹‹እግሮቹ ከመሮጥ የማይቦዝኑ ስኬታማና ሁለገቡ የስፖርት ሰው ነው›› ይሉታልእዮብ ተሰማን በቅርብ የሚያውቁት፡፡

እዮብና ማራቶን
በትልቅ ደረጃ ለሚሮጡ እውቅ አትሌቶች የማራቶን ውድድርን ማሸነፍ መቻል ጀግንነት ነው። የማራቶን ሩጫንተወዳድሮ አርባ ሁለት ኪሎ ሜትሮችን በብቃት ማጠናቀቅ መቻልም ለአንድ ተሳታፊ ትልቁ ስኬት ነው።በእርግጥ እንኳን ለአካል ብቃት፣ ለውጤት ለሚሮጡ አትሌቶችም ማራቶንን ማጠናቀቅ መቻል ቀላል ነገርአይደለም፡፡ ለዚህም ይመስላል የርቀቱ መክሊት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወይም ኬንያውያን አትሌቶች ከፊትበሚያጠናቅቁባቸው ውድድሮች የሌሎች በርካታ አገራት አትሌቶች መጨረሻ ሆነው ቢያጠናቅቁ እንኳንውድድሩን በመጨረሳቸው ብቻ ደስታቸው ወደር ሲያጣ የምናስተውለው።

ታላላቅ አትሌቶች በጉብዝናቸው ወራት ማራቶንን በማሸነፍ አገራቸውን እንደሚያስጠሩት ሁሉ በርቀቱ በርካታጊዜ ሮጦ በማጠናቀቅም የአገርን ስም ከፍ ማድረግ ይቻላል። እንደ ኢትዮጵያ ላሉ በርካታ የዓለም ከዋክብትአትሌቶች ሁሌም የማይጠፋባቸው አገራት ይህን ቀለል አድርገው ይመለከቱት ይሆናል። ግን ቀላል አይደለም።ኢትዮጵያ በበርካታ ከዋክብት አትሌቶቿ በማራቶን ስኬታማ የመሆኗን ያህል በርካታ ጊዜ ተወዳድሮበማጠናቀቅም የሚያስጠራት አላጣችም።
ባለፉት 40 ዓመታት ኑሮውን በአሜሪካን ሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ያደረገው ሁለገቡ የስፖርት ሰው እዮብ ተሰማለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው።

ይህ ሰው ኑሮውን ባህር ማዶ ካደረገ በኋላ በዩኒቨርስቲ ፣ በሰሜን አሜሪካየኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽንና የብራዚል መለስተኛ ፕሮፌሽናል ቡድኖች ውስጥ በአጠቃላይ ለ19 ዓመታትእግር ኳስን አጠንክሮ ተጫውቷል። ሁለገብ የስፖርት ሰው ሲባልም በምክኒያት እንደሆነ ከታሪኩ መረዳትይቻላል። ይህን ስያሜ የሚያሰጠው በልጅነትና በወጣትነት ዘመኑ የነበረው የእግር ኳስ ሕይወት ብቻ አይደለም።ከእግር ኳስ ታሪኩ በኋላ ወደ አትሌቲክስ ስፖርት ጎራ ብሎ ባለፉት 28 ዓመታት የሰራቸውና እየሰራ ያለው ታሪክአንድ የሚያስተምረን ነገር አለው፡፡

ታታሪነቱ፣ ከዓመት ዓመት አድካሚውን የማራቶን ሩጫ ለመወዳደር እድሜውገፍቶ እንኳን ደከመኝ ሰለቸኝ ብለው የማይዝሉት እግሮቹ እንዲሁም ስኬቱ ለብዙዎች ተነሳሽነትን የሚፈጥር፣ትምህርትም የሚሆን ነው።
ከሃያ ስምንት ዓመታት በፊት ስኬታማ ወደሆነበት ‹‹የማራቶን ሩጫ ቤተሰብ›› ጎራ ያለው እዮብ በስፖርቱከምንም ተነስቶ የጀገነበትን ብዙ ታሪክ ጽፏል። ከዜሮ ጀምሮ ዛሬ የስኬት ማማ ላይ ያስቀመጠው የታላቅ ሙያባለቤትም ሆኗል። በ1995 የመጀመሪያውን ማራቶን ውድድሩን በሎስ አንጅለስ ማራቶን በመሮጥ የሚወደውንየአርባ ሁለት ኪሎ ሜትር የሩጫ ታሪኩን አንድ ብሎ የጀመረው ብርቱው ሰው በየዓመቱ በዚህ ውድድር ከሦስትአስርት ዓመታት ላላነሰ ጊዜ ወጥ በሆነ አቋም እየተሳተፈ በስኬት ማጠናቀቅ ችሏል። ይህን ታሪክ በመስራትምየሚስተካከለውን ማግኘት አዳጋች ነው።
ከሚኖርባት ከተማ ሎስ አንጀለስ ማራቶን ባሻገር፣ እንደ ዝነኞቹ የቦስተን፣ ኒው ዮርክ፣ ሺካጎ፣ በርሊንና የጃፓንማራቶን ውድድሮች በመሳተፍም በርቀቱ በርካታ ጊዜ ሮጦ ማጠናቀቅ ችሏል።

በሃምሳ ዓመት እድሜው ሃምሳየማራቶን ውድድሮችን ሮጦ ማጠናቀቅ የቻለው ጠንካራው የስፖርት ሰው በአጠቃላይ ሰባ አራተኛ የማራቶንውድድሩን በቅርቡ ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ሎስ አንጀለስ ዙሪያ በሚገኝ ማራቶን ውድድር አድርጎ ለሚቀጥለውዓመት ቦስተን ውድድር ላይ እንዲወዳደር የሚያበቃውን መስፈርት አሟልቶ፣ በብቃትና በጥሩ ውጤት ፈጽሟልቢባል የተጋነነ ሊመስል ይችላል፡፡ ግን እሱ አድርጎታል፡፡ ይህ ሰው በማራቶን ብቻ የሮጠውን ርቀት ብንደምረው3108 ኪሎ ሜትር ሮጧል ማለት ነው።

‹‹የስፖርት ፍቅሬን፣ስሜቴን፣ጤንነቴንና የመንፈስ ጽናቴን ጠብቄ፣ አልበቃ ብሎኝ ነው እኩል ወደምወደውናእነሆ 28ኛ ዓመት ወዳስቆጠርኩበት የማራቶን ሩጫ ቤተሰብ ተሸጋግሬ እስከዛሬ ድረስ የቀጠልኩበት›› ይላልእዮብ በባህርማዶ ትልቅ ዝና ወዳተረፈበት የማራቶን ቤተሰብ ውድድር እንዴት እንደገባ ሲያስታውስ።

የማራቶን ውድድር እጅግ አድካሚና ትልቅ ጽናትን የሚሻ እንደመሆኑ የዓለማችን ታላላቅ አትሌቶች እንኳንበስፖርቱ በሚቆዩባቸው ዘመናት ሊሮጡ የሚችሉት ውድድር ብዛት የተወሰነ ነው። እዮብ ምናልባትም በዓለምበርቀቱ በርካታ ውድድሮችን በማድረግ ማጠናቀቅ የቻለ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ሰው ሊሆን ይችላል። ወደ ፊትምተጨማሪ ውድድሮችን የማድረግ አቅምና ተነሳሽነቱ አሁንም ድረስ አብሮት እንዳለ ሲታሰብ ደግሞ ይህን ሰውየተለየ ያደርገዋል። ይህም በርካቶች እሱን እየተመለከቱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን እንዲያዘወትሩ ብርታትናተነሳሽነት ሆኗቸዋል። የእዮብ ስኬትና ታሪክ ግን በማራቶን ብቻ የተወሰነ አይደለም። ሰማንያ ዘጠኝ የግማሽማራቶን ውድድሮችን ጨምሮ በበርካታ የአስርና አምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድሮችን አድርጎ ማጠናቀቅችሏል።

በነዚህ ሁሉ ውድድሮችም የኢትዮጵያ ስም ከፍ ብሎ እንዲጠራ ሲያደርግ ኖሯል፣ አሁንም እያደረገነው።
እዮብ ከታላቁ ድል ጀርባ
እዮብ በቅርቡ በዩጂን፣ ኦሬገን ለ18ኛ ጊዜ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶችከምንጊዜውም የላቀ ውጤት ሲያስመዘግቡ ከልኡካን ቡድኑ ጎን ቆሞ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከትየቀደመው የለም። ውድድሩ ዩጂን ከተማ ይካሄዳል ሲባል የዘወትር የኢትዮጵያ ኩራት የሆኑትን ብርቅዬአትሌቶች ቤቱ ቁጭ ብሎ በቴሌቪዥን መስኮት ብቻ ለመከታተል ልቦናው አልፈቀደም። 74ኛ ማራቶን ውድድሩንበጥሩ ውጤት ባጠናቀቀ ማግስት ውስጡ ያለው ከፍተኛ ስፖርታዊ ስሜት ገንፍሎ ወጣ።

የአገርና የወገን ፍቅርስሜቱ አላስችል ቢለው አረንጓዴ፣ቢጫና ቀይ ሰንደቅዓላማውን ታጥቆ፣ ቤተሰቡንና ሥራውን ትቶ፣ ለአንድሳምንት ያህል በከፍተኛ ወጪ በእንቁዎቹ አትሌቶች መንደር ኦሪገን ከትሟል። የኢትዮጵያ ኩራት የሆኑትንከዋክብት አትሌቶችን ሩቅ መንገድ ተጉዞ በባዶ እጁ ለመቀበልም አልፈለገም ነበር:: የሎስ አንጅለስ ማራቶንውድድርን ለ27 ተከታታይ ዓመታት በጤና፣ በትጋትና ለተለያዩ የኢትዮጵያ ማህበራዊና ሌሎች በጎ አድራጎትድርጅቶች “ተወካይ አምባሳደር ሯጭ” በመሆን ያፈራውን እውቅና በመጠቀም አንድ ነገር ለማድረግ ወሰነ።”ለምወዳቸው፣ለማደንቃቸውና ለማከብራቸው ወንድሞቼና እህቶቼ ለሆኑት የኢትዮጵያ ስፖርትልኡካን(ስፖርተኞች፣ አሰልጣኞች፣ ባለሙያዎችና አመራሮች በጠቅላላ) መተዋወቂያ ናሙና የሚሆን – 60 በልዩመልክ የተዘጋጁ መታሰቢያ ካናቴራዎች (ቲ-ሸርቶች) በሻንጣዬ ሰንቄ፣ በእህቴ ኮማንደር ደራርቱ ቱሉበተመቻቸልኝ መድረክ ላይ ለማበርከት በቅቻለሁ” ሲል እዮብ ቡድኑን እንዴት እንደተቀበለ ይናገራል።

ውድድሩ ለአንድ ሳምንት በቆየባቸው ቀናት በየእለቱ የኢትዮጵያን ልኡካን ቡድን በማግኘት፣ በግል ጀግኖቻችንንበመተዋወቅና ሙያዊ ምክር በመለገስ ያላሰለሰ ድጋፍና ፍቅሩን ሲገልጽ ሰንብቷል። ባካባቢው ከነበረውየኢትዮጵያ የዳያስፖራው ማህበረሰብና ደጋፊዎች ጋር በመሆንም ትልቅ የሞራል ድጋፍ አድርጓል። ‹‹ድምጹእስከሚዘጋ ድረስ በከፍተኛ ፍላጎት ሲጨፍርና ሲጮህ ነበር›› ይላሉ ውድድሩን በአካል ተገኝተው በመመልከትወደ አገር ቤት የተመለሱ የስፖርት ቤተሰቦች እዮብ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በኦሪገን ተአምር ሲሰሩ የነበረውንድባብ ሲያስታውሱ። ከድጋፉ ጎን ለጎን አልፎ አልፎ በአሜሪካውያን ተመልካቾችንና ታዛቢዎች ኢትዮጵያንናአትሌቶቹን በተመለከተ ይቀርቡ ለነበሩ ጥያቄዎች የተለያዩ ምላሾችና ማብራሪያዎችን በመስጠት በገጽታግንባታ ረገድ ሲያበረክት የነበረው አስተዋጽኦም ቀላል አልነበረም። ከሶስት አስርት ዓመታት በኋላ በአካል ያገኛትና”እህቴ” የሚላት እንቁዋ አትሌትና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉእንዲሁም በልኡካን ቡድኑ መሪ አቶ ተፈራ ሞላ አማካኝነትም እዮብ ጠርቀም ያለውንና አጠቃላይ ይዘት ያለውንየረጅም ጊዜ ሙያዊ ችሎታውንና ልምዱን ለቡድኑ ማካፈል ችሏል። ይህንን ሙያዊ ድጋፉን ወደ ፊትም በነጻለማበርከት ዝግጁ መሆኑን በመግለፅ፣ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በቅርቡ የሥራግንኙነት ለመፍጠርፍላጎቱን እንደገለጸላቸው ይናገራል። የልኡካን ቡድኑ በዩጂን በነበረው ቆይታ ባደረገው አስተዋጽኦ ግን የረካአይመስልም። ‹‹በውድድሩ ወቅት ለኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን ያደረኩት አስተዋጽኦና ድጋፍ እጅግ በጎላ መንገድነው ብዬ ባላምንም፤ እንደ መነሻና መተዋወቂያ ይሆናል ብዬ በማሰብ የበኩሌን ለማድረግ ሞክሬያለሁ፣በዚህምተደስቻለሁ›› ይላል።

እዮብ በስኬት ጎዳና
እኤአ በ2004 “በካሊፎርሊያ ግዛት እጅግ አነቃቂው ሯጭ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። ይህም ከሁለት አስርትዓመታት በላይ እንደ ሶኮኒ፣ ናይኪ፣ ኤሲክስ፣ ኬ ስዊስ፣ ስኬቸርስ፣ ሆካና ከሌሎችም ዓለም አቀፍ እውቅና ካላቸውታላላቅ ኩባንያዎች እውቅና አግኝቶና ድጋፍ ተደርጎለት በጋራ ለመስራት አስችሎታል። በደቡብ ካሊፎርኒያ ግዛትበሚካሄዱ በርካታ የጎዳና ላይ ውድድሮች ብዙዎች ተሳታፊ እንዲሆኑ የ”ሌጋሲ ራነርስ” መስራች የሆነው እዮብበትልልቅ መገናኛ ብዙሃን ትኩረት የሚሰጠው ሰው ነው። የሎስ አንጀለስ የስፖርትና አካል ብቃት መጽሄት ሰፊሽፋን የሰጠው ሲሆን፣ ኬኤንቢሲ ቻናል 4 ስፖርትስ፣ኬቲኤልኤፍ ቻናል 5 ቴሌቪዥን በእንግድነት ካቀረቡትመካከል ተጠቃሽ ናቸው። ከነዚህ በተጨማሪም ማህበረሰብ አቀፍ በሆኑ በሌሎች በርካታ የመገናኛ ብዙሃንፕሮግራሞች ላይም በተደጋጋሚ በክብር እንግድነት መቅረብ ችሏል።

እኤአ በ2014 የካሊፎርኒያ ግዛት ምክር ቤትእውቅና የተቸረው ሲሆን፣ የሎስ አንጀለስ ከተማ ምክር ቤት እንዲሁም ከንቲባው ኤሪክ ጋርሴቲ እዮብ ለሃያዓመታት በማህበረሰብ ስፖርት እንቅስቃሴ ውስጥ ላበረከተው አስተዋጽኦ እንዲሁም በነዚህ ዓመታት በሃምሳዓመት እድሜው ሃምሳ የማራቶን ውድድሮችን ማሳካት በመቻሉ እውቅና ሰጥተውታል።

እዮብና በጎ አድራጎት
እዮብ በማህበረሰብ ስፖርት ውስጥ ከሚያደርገው ሰፊ እንቅስቃሴ ጎን ለጎን ከበርካታ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋርየሩጫ አምባሳደር ሆኖ በመስራት የተለያዩ ድጋፎችን በማሰባሰብ አንቱታን አትርፏል። ከነዚህም መካከልኸርሽበርግ ፓንክሬቲክ ካንሰር ሶሳይቲ፣ ወርልድ ቪዥን፣ የልብ ህሙማን ማህበር፣ ፍሬገነት የህጻናት ትምህርትፋውንዴሽን እና በሎስ አንጅለስ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ድርጅት (ኢሲኤልኤ) ጋር በተያያዘ ከተለያዩ በጎአድራጎት ድርጅቶች ጋር ገቢ በማሰባሰብ ይሰራል።
እዮብ በሌላኛው የሙያ ገጽ
እዮብ የሎስ አንጀለስ የአካል ብቃት አማካሪ ቡድን (LA ENDURANCE SPORTS CONSULTING GROUP) መስራችም ነው። በዚህ ተቋምም ስር ከአካል ብቃትና ከስፖርት ጋር በተያያዘ ለማህበረሰብ ጠቃሚ የሆኑ በርካታአገልግሎቶችን ይሰጣል። የአትሌቲክስ አሰልጣኝና አማካሪ ሆኖም ይሰራል። በአካል ብቃትና በስፖርቱ ዓለምበየጊዜው እየተጋበዘ አነቃቂ ንግግሮችን ለአማርኛም ሆነ ለእንግሊዝኛ አድማጮች በማድረግ ይታወቃል።

ባለትዳርና የአራት ልጆች አባት የሆነው እዮብ፣ የተለያዩ አትሌቶች ማኔጀርና ተወካይ በመሆንም ይሰራል።በዚህም የተለያዩ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለይም በሎስ አንጀለስ ማራቶን እንዲወዳደሩ ሁኔታዎችንበማመቻቸት ይታወቃል። ከነዚህም መካከል ባለፈው መጋቢት በተካሄደው 37ኛው የሎስ አንጀለስ ዓመታዊየማራቶን ውድድር ላይ እንዲሳተፉ መንገዱን የጠረገላቸው ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ብርሃኑ በቀለበርጋ፣ግዛቸው ሃይሉ ነጋሽና በላይነሽ ሽፈራ ይገዙ ተጠቃሽ ናቸው።
አዲስ ዘመን ነሐሴ 15/2014

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *