“አሜሪካ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ትቆማለች ፤ የአፍሪካ ህብረትን (AU) ዲፕሎማሲያዊ ጥረትን ትደግፋለች ” – አንቶኒ ብሊንከን

0
0 0
Read Time:48 Second

አሜሪካ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ትቆማለች የአፍሪካ ህብረትን (AU) ዲፕሎማሲያዊ ጥረትን ትደግፋለች ” – አንቶኒ ብሊንከን

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሀገራቸው አሜሪካ #ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንደምትቆም እና በአፍሪካ ህብረት እየተመራ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት #እንደምትደግፍ ገልፀዋል።

ይህን የገለፁት ለሊት ባወጡት መግለጫ ነው።

ብሊንከን ፤ የአፍሪካ ህብረት እየተካሄደ ላለው ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ ለማበጀት የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት (TPLF) በተቻለ ፍጥነት ወደ ውይይት እንዲመጡ ለማድረግ እየሰራ ላለው ስራ ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም ሲባል ከህወሓት ጋር ” በየትኛውም ስፍራ፣ በማንኛውም ጊዜ ”  ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን እንደገለፀ ያስታወሱት ብሊንከን ለዚህ የመንግስት ዝግጁነት የሚሰጥ ምላሽን እናበረታታለን ብለዋል። ህወሓት (TPLF) ግጭት ለማቆም እና ችግሮችን በውይይት ለመፍታት ያወጣውን መግለጫ እናበረታታለን ሲሉም አክለዋል።

ዓለም አቀፍ አጋሮች የሰላም ሂደቱን ለማገዝ ዝግጁ ናቸውም ብለዋል።

ኤርትራ እና ሌሎችም ግጭቱን ማቀጣጠል ማቆም አለባቸውም ሲሉ ገልፀዋል።

አሜሪካ የኢትዮጵያን #አንድነት፣ #ሉዓላዊነት እና #የግዛት_አንድነት እንደምትደግፍ የገለፁት አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ወደ #ጠንካራ_አጋርነት መመለስ ትፈልጋለች ሲሉ ገልፀዋል።

የአዲስ ዓመት መንፈስን ታሳቢ በማድረግ የአገሪቱ መሪዎች አገሪቱ መከራዋ ወደሚያበቃበት እና ዘላቂ ሰላም ሊያስገኝ ወደሚያስችል መንገድ እንደሚሯት ጥሪ እናቀርባለንብለዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *