ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እንደሚቋጭ እና ሰላምም እንደሚሰፍን ተናገሩ።

0
0 0
Read Time:1 Minute, 0 Second

የኢፌዴሪ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እንደሚቋጭ እና ሰላምም እንደሚሰፍን ተናገሩ።

ይህንን የተናገሩት በቡራዩ ከተማ የተገነባ የልዩ ተሰጥኦ ማበልፅጊያ ኢንስቲትዩት በመረቁበት ወቅት ባሰሙት ንግግር ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ” በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ነገር ይቋጫል፤ ኢትዮጵያም ሰላም ትሆናለች ” ብለዋል።

” እንዲሁ እንደተዋጋን አንቀጥልም ያሉት ” ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በሰላም፣ በልማት የትግራይ ወንድሞቻችንን ለማልማት በጋራ የምንቆምበት ጊዜ ቅርብ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ በንግግራቸው ላይ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መቋጫ ስለሚያገኝበት እና ሰላም ስለሚሰፍንበት መንገድ በዝርዝር አልተናገሩም።

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከተጀመረ የፊታችን ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ/ም ሁለት ዓመት የሚደፍን ሲሆን ጦርነቱ በተለያየ ጊዜ የተለያየ ክስተት እያስተናገደ ዛሬ ላይ ደርሷል።

ይኸው ጦርነት የበርካታ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ ሲሆን ሚሊዮኖችን ከቀያቸው አፈናቅሏል፣ ለችግርም ጥሏል።

ጦርነቱ ባመጣው መዘዝ ባለፉት በርካታ ወራት የትግራይ ክልል ነዋሪዎች እና ከትግራይ ክልል አዋሳኝ በሆኑ የአማራ እና አፋር ክልል አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች መሰረታዊ አገልግሎት ለማግኘት አዳጋች ሆኖባቸዋል።

ጦርነቱ እንዲቋጭ የተለያዩ የሰላም ጥረቶች እየተደረጉ ሲሆን የፊታችን ሰኞም በአፍሪካ ህብረት መሪነት በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል በደቡብ አፍሪካ የሰላም ንግግር ይጀመራል ተብሎ ቀን ተቆርጧል። በዚሁ የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ መንግስት ቁርጠኛ ነኝ ሲል አሳውቋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https: https://www.facebook.com/TheEthiopianTribune
ቴሌግራም https://t.me/TheEthiopianTribune
ዩቲዩብ https://youtube.com/c/TheEthiopianTribune
ቲዊተር https://twitter.com/EthTribune
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *