ፓትሪያርክ ይሉዋል እነዲህ ነው። እን ደ ወላይተኛ ተናጋሪው ቅዱስ ፓትርያሪክ።

0
0 0
Read Time:2 Minute, 19 Second

ፕትርክና አይገባኝም ስላሉ ብቻ መንበራቸውን ጥለው እንዳይሄዱ በወታደር ይጠበቁ የነበረት ከወላይታ የተገኙት ወላይተኛ ተናጋሪው ቅዱስ ፓትርያሪክ


የቀደመው ስማቸው አባ መልአኩ ይባላሉ። ምንም እንኳን ውልደታቸው በጎንደር ጋዢን በምትባል ስፍራ ቢሆንም ረጅም ዕድሜያቸውን ያሳለፉት እና አብረው የኖሩት ማህበራዊ ስነልቦናቸው ያገኙት ወላይታ በሚባል ደቡባዊ ምድር ላይ ነው።

ከሀገሬው በላይ ወላይተኛ አቀላጥፈው ይናገራሉ። ከውልደት ስፍራቸው በቀር አኗኗር እና አዋዋላቸው ሙሉ በሙሉ ከአንድ የወላይታ ገበሬ የተለየ አልነበረም።

የመጽሐፍት ትርጓሜ በእዚሁ በወላይታ ምድር ባሉ ጉባኤ ቤቶች አጠኑ።ስርዓተ ገዳም ከተማሩ በኃላ በእዚያው ወላይታ በሚገኘው ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም መኖከሱ። የብህትህና ህይወታቸው በወላይታ ምድር ጀመሩ።

ከ1926-1968 ለ42 ዓመታት ወላይታ ላይ በወላይተኛ ቋንቋ ሐዋርያዊ አገልግሎት ፈጽመው ከ300,000 በላይ ኢ- አማንያንን እንዳስጠመቁ እና ከ65 በላይ አብያተክርስቲያናትን አሳንጸዋል። በእዛ ዘመን አስበኅዋል ወዳጄ?

የደርግ መምጣትን ተከትሎ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን 2ኛው ቅዱስ ፓትርያሪክ የነበሩት ብጽኡ አቡነ ቴዎፍሎስን ተገደሉ።

በመሆኑም ቅድስት ቤተክርስቲያን 3ኛው ቅዱስ ፓትርያሪክ ለመምረጥ 909 አከባቢያቸውን የሚወክሉ አባቶች በአዋጅ ሰበሰበች።

ከ565 ወረዳዎች ለማዕረገ ፕትርክና መንፈስ ቅዱስ የሚመርጠውን አባት ይገኝ ዘንድ ሁለት ሁለት ተወካይ ይላክ ዘንድ ታዘዘ።

ገና ማዕረግ ጵጵስናን ያልተቀበሉት በቁምስና ያሉት መኖክሴው የወላይታው አባት የሆኑት አባ መላእኩ ከወላይታ “ተወካይ ሆኜ አልሄድም” ብሎ እንቢ ማለትን ከጅምሩ ቢያሳውቁም በገዳሙ አባቶች ትዕዛዝ እና ቃለ ውግዘት የወላይታ አውራጃን ወክለው ተላኩ።

ገና ማዕረግ ጵጵስና ሳይቀበሉ በቁምስና ማዕረግ መሆናቸው ደግሞ ለዬት ያደርገዋል።

በስተመጨረሻም የመጨረሻው 5 ዕጩ ውስጥ ስማቸው ተካተተ። ከአንድ ቆሞስ እና ከሶስት ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ለ3ተኛው የፕትርክና የአገልግሎት ሥልጣን ለውድድር ተቀመጡ።

ከየወረዳው ለመጡት ለመራጩ ተወካዮችም ግን እንቢታቸውን እና ከውድድሩ እንዲያስወጧቸው እንዲህ ብለው ተናገሩ

<< “እኔ ባህታዊ ነኝ ..ጥዬው የመጣሁት ህዝብ አለኝ ፣ ኑሮዬ በጫካ ነው እና የከተማውን ህይወት ለምጄ መምራት አይቻለኝም ።የበቁ አባቶች አሉ እና እኔን በእዚህ ምርጫ ውስጥ አወዳድራችሁ መንፈስ ቅዱስን አታሳዝኑ፣ እኔን ከምርጫው ሰርዙኝ ” >>

ብለው ለጉባኤው በተደጋጋሚ እየጮኹ ቢነግሩም ሰሚ አጡ።

በስተመጨረሻም ከሊቃነ ጳጳሳት ጋር ተወዳድረው በአብላጫ ድምጽ መኖክሴው መናኝ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን 3ኛው ቅዱስ ፓትርያሪክ ሆነው ተመረጡ።

በ1968 ሐምሌ ወር ላይ መዓረገ ጽጽስና ተቀብለው ከወር በኃላ በጉባኤው ምርጫ መሰረት

<< “አባ ተክለሃይማኖት ሣልሳዊ የኢትዮጽያ ፓትርያሪክ”>>
ተብለው ተሾሙ።

ከተሾሙ በኃላም በብህትህና ወደ ወላይታ ተመልሰው በገዳማቸው በዓት ለመዝጋት መንበራቸው ጥለው ሊሸሹ በተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርጉም የደርግ ወታደሮች እየያዟቸው መለሱ።

በስተመጨረሻም መንበራቸውን ጥለው እንዳይሄዱ በመኖርያ ቤታቸው ጥበቃ ተመደበ። መውጫ መግቢያቸው ከደርግ ወታደሮች እውቅና ውጪ እንዳይሆን ተደረገ።

ወዳጄ…መንፈስቅዱስ ሲመርጥ እንዲህ ነው። ዳዊትን ከእረኝነት ንጉስ ያደረገ አምላክ፣ሳሙኤልን ከመካኒቷ ማህጸን አውጥቶ ነብይ ብሎ የሾመ ጌታ፣ሙሴን ከውሐ ላይ ታድጎ ነጻ አውጭ አድርጎ የቀባ እግዚአብሔር ….ምርጫው ኮታ ሳይሆን ጸጋ ነው።

ይህኝ አባት ለጸጋ ፕርትርክና የሚገቡ አባት መሆናቸውን ባገለገሉበት 12 የፕትርክና አገልግሎት ዓመታት ገለጡ።

ጫማን ለመንግስት ፕሮግራሞች ብቻ ይጫሙ እንደነበር ይነገራቸዋል።ከፆም ጸሎት በቀር ቅርባቸው የሚሆን ሰው አልነበረም።

ደምወዛቸውን ለነድያን እና ለወላይታ ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት መኖኮሳት ቀለብ በቋሚነት ይልኩ ነበር።

ለቁመተ ሥጋ ብቻ ተመጋቢ የሆኑ ይህኝ አባት በስተመጨረሻ በሥጋ ድካም ሲያርፉ የከበረች ሥጋቸው 25 ኪግ ብቻ እንደነበር ይታወቃል።

ይህኝን አባት ዛሬም ድረስ የወላይታ ኦርቶዶክሳውያን ያለስስት በዓለ ረፍታቸውን አስበው በገዳማቸው ይዘክራሉ።

የቅዱስነታቸው የከበረች በረከታቸው ትደርብን !!!

እግዚአብሔር ይመስገን !!!

Source: Kune Demelash kassaye -Arba Minch

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *