ህወሓት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ አልቀበልም አለ!!
” የቦርዱ ውሳኔ የሰላም ሂደቱ አደጋ ውስጥ የሚከት ነው ” – ህወሓት
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከቀናት በፊት ምርጫ ቦርድ ያሳለፈውን ውሳኔ እንደማይቀበለው ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።
የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ” አልቀበለውም ” ያለው ህወሓት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እወያይበታለሁ ብሏል።
የምርጫ ቦርድም ውሳኔውን እንደገና በማጤን የፕሪቶርያ ስምምነትና ሌሎች የፌደራል ተቋማት ያስተላለፉትን ውሳኔዎች መነሻ በማድረግ እንዲያስተካክል ጠይቋል።
ህወሓት የሰላም ስምምነቱ ባለቤት ናቸው ያላቸው የድርጅቱ አባላት፣ የትግራይ ህዝብና የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የቦርዱ ውሳኔ የሰላም ሂደቱ ኣደጋ ውስጥ የሚከት መሆኑ በመገንዘብ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
የፌደራል መንግስትም ” ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የሰጠውን ውሳኔ በተጀመሩት አወንታዊ የሰላም እና የመደጋገፍ ጥረቶች ላይ ሊያሳድረው የሚችል አላስፈላጊ ጫና እንዲሁም የፌደራል መንግስቱ ህጋዊ ውሳኔዎችን እና ስምምነቶችን #በሁሉም የመንግስት ተቋማት እና አካላት እንዲከበሩ የማድረግ ኃላፊቱን ግምት ውስጥ በማስገባት የቦርዱን ውሳኔ እንደገና ታይቶ ከህወሓት ህጋዊ ሰውነት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥያቄዎች ያሉትን ህጋዊና ፖለቲካዊ አማራጮች ተጠቅሞ ነገሮች ቅድመ-ጦርነት ወደ ነበሩበት ሁኔታ እንዲመለሱ በሚያደርግ ቀና አካሄድ እንዲፈቱ እንዲያድረግና የፕሪቶርያ ስምምነት በተሟላ መንገድ ተግባራዊ እንዲደረግ እና የተጀመረውን የሰላም ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንዲያደርግ ” ሲል ጥሪ አቅርቧል።
የህወሓት ሙሉ መግለጫ