ኦሮሚያ ባንክ 1.58 ቢሊዮን የተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን አሳወቀ።
ኦሮሚያ ባንክ ከታክስ በኃላ ሪከርድ ሆኖ ተመዝግቧል ያለዉን 1.58 ቢሊዮን የተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን አሳወቀ
ኦሮሚያ ባንክ ከታክስ በፊት የተገኘው ትርፍ ሌላ ሪከርድ መሆኑን የገለፀዉን 1.5 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ አሳክቻለሁ ብሏል።
የኦሮሚያ ባንክ ኢንቨስትመንት እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2023 ብር 153 ሚሊዮን ደርሷል ብሏል። ይህም ተጨማሪ ኢንቨስትመንቶችን በማድረጉ በድምሩ 17.1 ሚሊዮን ብር፣ ከኦሮሚያ ኢንሹራንስ 8.59 ሚሊዮን፣ ከፀሃይ ኢንዱስትሪ 4.83 ሚሊዮን፣ ከኤትስዊች 3.68 ሚሊዮን፣ ቀሪውን ገንዘብ ከቀሪዎቹ ሦስት ኩባንያዎች ማግኘት መቻሉን በዓመታዊ ሪፖርቱ ገልጿል።
እ.ኤ.አ. ከሰኔ 30 ቀን 2023 ጀምሮ የዓለም አቀፍ የባንክ ሥራ አጠቃላይ የውጭ ምንዛሪ 371 ሚሊዮን ዶላር ያስገኘ ሲሆን ይህም የእቅዱን 102.1 በመቶ ውጤት ያሳያል። የኦሮሚያ ባንክም የውጭ ምንዛሪ ሃብት ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ33 በመቶ እድገት አሳይቷል ያለ ሲሆን በኢትዮጵያ የባንክ ኢንደስትሪ ውስጥ ከፍተኛ እድገት መሆኑን ለካፒታል አሳዉቋል።
ባንኩ በበጀት አመቱ መጨረሻ 65.4 ቢሊየን ብር ሀብት መያዙን አሳዉቆ ካፒታሉ በበጀት አመቱ መጨረሻ ወደ ብር 5.4 ቢሊየን አድጓል ብሏል ።
ገቢው ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር በ43 በመቶ (ብር 2.45 ቢሊዮን) በማደግ 8.3 ቢሊዮን ብር ደርሷል ያሉት የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተፈሪ መኮንን “የአመቱ አጠቃላይ ወጪ ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር 47 በመቶ እድገት በማስመዝገብ ብር 6.3 ቢሊዮን ደርሷል”። የባንኩ ያልተጣራ ትርፍ ብር 2 ቢሊዮን መድረሱንም በሪፖርቱ ገልጿል።
Source: (ካፒታል : ህዳር 30፤2016 ዓ.ም.)