ጀኔራል መስፍን ገብረቃል ” ዜና እረፍት !!


እትብታቸው የተቀበረው ከዘርአይ ደረስ፣ ከነአብርሐ ደቦጭ፣
ከነ ሞገስ አሰግዶም ፣
የትውል አገር ባሕረ ነጋሽ (ኤርትራ ) ነው ።
ሙሉ ሰማቸው
ሜ/ ጀኔራል መስፍን ገብረቃል
ይባላሉ ። ሐገራቸዉን በዉትድርና ሞያ ለማገልገ በእንግሊዝ
Royal Military Academy Sandhurst በ1957 ተልከው
ወታደራዊ ትምህርታቸውን
ጨርሠዉ በጦር መኮነንት ተመርቀዋል ።
በምስራቅና በሰሜን ጦር ግንባር በአዛዥነት እንዲሁም የመከላከያ የዘመቻ ዋና መምሪያ ኃላፊ ፣ የምድር ጦር ምክትል አዛዥ
በመሆን አገልግለዋል ።
በመጨረሻም የጦር ኃይሎች የፓለቲካ መምሪያ ሃላፊና የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሆነው እስከ ደርግ ፍፃሜ ድረስ ሠርተዋል ።
የትምህርት ዝግጅታው
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በህግ የመጀመሪያ ዲግሪ ።
በእንግሊዝ ወታደራዊ አካዳሚ በሳድህረስት በካምበርሊ ስታድ ኮለጅ ከፍተኛ ወታደራዊ ትምህርት ተከታትለዋል ።
ግንቦት 19 ቀን 1983
ከቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ ዲንቃ ጋር በመሆን ከሻዕቢያ፣ እንዲሁም ከወያኔና ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጋር ሊካሄድ በታቀደው ድርድር ለመሳተፍ የመንግስት ልዑካን ከነበሩት አንዱ በመሆን እንግሊዝ አገር ለንደን ገቡ ።
ድርድሩም ሳይቋጭ በአሜሪካን የተመራው ሽምግልና ኤርትራን አስገንጥሎ ወያኔን ኢትዮጵያ ላይ አንግሶ ተደመደመ ።
እሳቸውም በስደት እንግሊዝ ለንደን ቀሩ ።
ለንደን በነበሩበት ጊዜም በአለም አቀፍ ግንኙነት በለንደን ከኪንግስ ኮሌጅ የማስትሬት ቀጥሎም በዶክትሬት ተመርቀዋል ።
ኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ስልጣን በነበሩበት ጊዜም በተለያዩ መንግስታዊ ስብሠባዎች ላይ አገኛቸው ስለነበረ በአካል አውቃቸዋለሁ ።
ከብዙ አመት በሗላ አንድ ቀን (SOAS University of London) ቤተመፃህት ውስጥ ተገናኜን ።
ዛሬ በህይወት የለም።
ከዮሐንስ ጴጥሮስ ጋር ሆኜ ሳገኛቸው የተሠማኝን ደስታ አሁን መግለፅ አልችልም ።
እንደ ባህላችን በአክብሮት ሠላምታ አቅርበን ሻይ ቡና እንድንል ጠይቀን ተማሪዎች ክበብ ውስጥ ወስደን ጋበዝናቸው ።
ጄኔራል መስፍን ስለአሳለፉት መከረኛ ሕይወት እያጫወቱን በረጅም ትዝታ አብረናቸው ቆየን ። እኔም በትንሹ እራሴን አስተዋውቄ በቅርብ እንደማውቃቸዉ ገለፅኩላቸው ።
ነገር ግን በፍፁም ሊያስታውሡኝ አልቻሉም ። ዮሐንስ ጴጥሮስ በበኩሉ በጨዋታችን ምሐል ጣልቃ እየገባ አንዳንድ ምቾት የማይሠጡ ጥያቄዎች እያነሳ አስቸገራቸው ።
በመጨረሻም ሊሠናበቱን ሲነሡ ለዶክትሬት መመረቂያ የፃፉትን ፅሁፍ እንዳነበው እንደሚሠጡኝ ቃል ገብተውልኝ ተሠነባበትን ።
ከዚያን ቀን ጀምሮ SOAS University ቀሩ መሠል ላገኛቸው አልቻልኩም ።
የቅርብ ወዳጃቸውን የሆኑትን ኮሎኔር ምንዳዬን አልፎ አልፎ
ሳገኛቸው በተደጋጋሚ ሰለ
ሜ/ ጀኔራል መስፍን ገብረቃል ጤንነት እጠይቃቸው ነበር ። እንዲያገናኙኝም አጥብቄ ለምኛቸው ነበር ። ነገር ግን ጀኔራል መስፍን ገብረቃል የደህነት ሰጋት ስላለባቸው ማንንም ሰው ማግኜት እንደማይፈልጉ እቅጩን ነገሩኝ።
በምስልና በድምፅ ቀርጨ ለታሪክ ላቆየው የነበረው የሠራዊቱ ታሪክና የድርድሩ ፍፃሜ ከሳቸው አንደበት ሳልሠማው ጊዜ እያመለጠኝ ተቸገርኩ ።
አንድ ቀን ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጌወርጊስ ጋር ተገናኝተን ጀኔራል መስፍን ገብረቃልን እንዲያገናኙኝና ቃለመጠይቅ ማድረግ እንደምፈልግ
አጫወትኳቸው ። የሚችሉትን ሁሉ ጥረት እንደሚያደርጉ ቃል ገብተውልኝ ነበር ።
ደግሜ ሳገኛቸው ቃለ ምልልስ ለማድረግ ፍቃደኛ እንዳልሆኑ ነገሩኝ ። እናም የድርድሩን ጉዳይ የደቡብ ሱዳንን ሚስጥር እንደያዙት በ88 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን ስሠማ አንድ የታሪክ መፅሀፍ የተቃጠለ ያህል ተሠማኝ።
ነፍስ ይማር !ጄኔራል ።
በደርግ ዘመን ብቻ 40 ሺህ የደቡብ ሱዳን ሠራዊት የሰለጠነው በኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ በህይወት የሌሉት የደቡብ ሱዳን ንቅናቄ መሪ ኮሎኔል ጆን ጋራንግ ፣ ሳልቫኬር ምክትላቸውና ሬክ ማቻር ሌሎችም መኖሪያቸው ኢትዮጵያ ነበረች፡፡
በቅርብ ሆነው ጉዳዩን ሲከታተሉ የነበሩት ሜ/ጀኔራል መስፍን ገብረቃል እንደነበሩ ሠምቻለሁ ።
ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳን ሠላም አግኝታ በተረጋጋ ሁኔታ እንድትኖር ጦርነቱ ከተካሄደ በኋላም ሰፊ የሽምግልና ሥራ ሰርታለች፡፡ ያለመሰልቸት ሁለቱንም ወገኖች አቀራርባባ ሠላምና እርቅ እንዲፈጠር የበኩሏን ትልቅ ድርሻ እንድትወጣ መሐንዲሡ
ሜ/ጀኔራል መስፍን ገብረቃል እንደነበሩ በነበረን አጭር ቆይታ በአንደበታቸው ነገረውኛል ።
ሜ/ጀኔራል መስፍን ገብረቃል በተወለዱ በ88 አመታቸው ማክሠኞ ።August 12 ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል ።
ስርአተ ቀብራቸውም በኖሩበት የስደት አገር ለንደን ውስጥ እንደሚፈፀም ሠምቻለሁ ።
ለቤተሰቦቻቸው ለጓደኞቻቸውና ለቀድሞ መከላከያ ሠራዊት አባሎች
መፅናናትን እመኛለሁ ።
ይህንን ፎቶግራፍ
ስብሠባላይ ለመጨረሻ ጊዜ አብሪያቸው የተነሳሁት ነው ።
አለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ለንደን)