0 0
Read Time:2 Minute, 10 Second

==>>>ዜና እረፍተ ሕይዎት<<<==

የልዑል ራስ አሥራተ ካሣ ኃይሉ ባለቤት ፤ ልዕልት ዙርያሽወርቅ ገብረእግዚአብሔር እረፍት፤

በመላው የላስታና በጌምድር ተወላጅ ከሆኑት ከጃንጥራር የትውልድ ሐረጋቸው የሚመዘዘው እቴጌ መነን አስፋው መጀመሪያ ጋብቻ የልጅ ልጅ የሆኑት ፤ እጅግ በጣም ሲበዛ ተወዳጅና ከፍተኛ ዝና የነበራቸው የዳግማዊ ምንሊክ የአጎት ልጅ የራስ ዳርጌ ልጅ ራስ ኃይሉ ፤ የልዑል ራስ ካሣ ኃይሉ የልጅ ልጅ የሆኑት የራስ አሥራተ ካሣ ባለቤት ልዕልት ዙርያሽወርቅ በእንግሊዝ ሀገር በለንደን ከተማ ውስጥ ማረፋቸው ታውቀ።

ልዕልት ዙርያሽወርቅ በሕገ ቤተ ክርስቲያንና በክፍተኛ ንጉሣዊያን ቤተሰብ ማዕረግ ልዑል ራስ አሥራተ ካሣን አግብተው ልጆች ወልደው በተድላና በደስታ ሲኖሩ፤ ንጉሠ ነገሥቱ ትምህርት ቤት ከፍተው ከከብት እረኝነት አንስተው በወታደራዊ ሙያ ያሰለጠኗቸው ካህዲያን ወታደሮች ድንገት ተነሳስተው ባደረሱት የዘውድ መፈንቅለ መንግሥት ምክንያት እራሱን ደርግ ብሎ የሰየመው ቡድን ያለፍርድ ከገደላቸው የንጉሠ ነገሥቱ ከፍተኛ ባለሥጣናትና መኴንንቶች መካከል አንዱ የልዕልት ዙሪያሽወርቅ ባለቤት ልዑል ራስ አሥራተ ካሣ ናቸው።

ልዑል ራስ አሥራተ ካሣ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ፈቃድ በከፍተኛ የዘወዳዊ ልዑልነት ማዕረግ በሀገራችን ኢትዮጵያ በሁሉም አቅጣጫ በሚባል ደረጃ ሀገራቸውን በኃላፊነት ካገለገሉት እውቅ ንጉሣውያን ቤተሰብ መካከል በግንባር ቀደምነት የሚጠቀሱ የንጉሠ ነገሥቱ ልዩ ቀራቢና አማካሪም በመሆን አገልግለዋል።

ልዕልት የዙርያሽወርቅም ደርግ ለአሥራ አራት ዓመታት ያለፍርድና ያለዳኝነት በግፍ ካሠራቸው የንጉሣውያን ቤተሰብ መካከል አንዷ ሲሆኑ፤ በምህረት ከእሥር ከተፈቱ በኋላ ወደ እንግሊዝ ሀገር መጥተው ፤ በንግሊዝ ንግሥት እውቅና ልዩ እንክብካቤ እንዲደርግላቸው ተፈቅዶ የተሟላ የቅርብ ክትትል እየተደረገላቸው ለአለፈው ሠላሳ ሦስት ዓመታ በእንግሊዝ ሀገር በለንደን ከተማ ኖረዋል።

ልዕልት ዙርያሽወርቅ ከልዑል ራስ አሥራተ ካሣ ወንድችም ሴቶችም ልጆች የወልዱ ሲሆን በተለይም በወል ታዋቂ የሆኑት ወንድ ልጆቻቸው ልጅ አስፋውወሰን አሥራተ ካሣ በጀርመን ሀገር የሚኖሩ የታወቁ ምሁር በዓለም አቀፍ የታሪክና የምጣኔ ሐብት አማካሪ ሲሆኑ በኢትዮጵያ ማህበራዊ፣ ፓለቲካዊ ትንታኔዎች ላይ የጎላ ተሳትፎ በማድረግ ይታውቃሉ ።

ታናሽ ወንድማቸው ልጅ ሙሉጌታ አሥራተ ካሣ በእንግሊዝ ሀገር በልዩ ልዩ ሕዝባዊና መንግሥታዊ በከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት ተቀጥረው የሠሩ ከመሆናቸውም በላይ፤ በአየር ላንድ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። በእንግሊዝ ሀገር የኢትዮጵያ ኢንባሲ የሕዝብ ግኑኝነት ኃላፊ በመን በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

ልጅ ሙሉጌታ አሥራተ ካሣ የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ፀጉር ወደ ኢትዮጵያ በማስመለስ ደረጃ ንቁ ተሳትፎ ያደረጉና በእግሊዝ ሀገር በለንደን ከተማ በሚገኘው የጦር ሙዜም ውስጥ የንጉሡ የእራስ ፀጉር አመላለስ የርክክብ ስነ-ሥርዓቱን በአግባቡ የመሩ ናቸው።

ልዕልት ዙርያሽወርቅ እራሳቸውን ለፈጣሪ ያስገዙ በጾም በጸሎት ተውስነው የሚኖሩ፤ ሀገራቸው ኢትዮጵያንና ሃይማኖታቸውን ሕዝባቸውን ኢትዮጵያውያንን የሚያፈቅሩ፤ እጅግ ሲበዛ ትሁት ሩህሩህና ደግ ልዕልት ነበሩ።

ልዕልት ዙርያሽወርቅ እንግሊዝ ሀገር ከሚደረግላቸው ድጋፍ በተጫማሪ በልጃቸው በልጅ ሙሉጌታ አሥራተ ካሣ ልዩ የቅርብ ክትትል ከፍተኛ እንክብካቤ ሲደረግላቸ የኖሩ፤ የልጅ ልጆቻቸውም ድጋፍ ሳይለያቸው በዚህ ምድር ላይ ወደ ዘጠና የሚጠጋ ዘመን ኑረው ዛሬ አርብ መስከረም ስምንት ቀን ሁለት ሺህ አሥራ ሦሥት ዓመተ ምሕረት በዘመነ ማቴዎስ መዋዕለ ዘመናቸው ተጠናቋል እረፍተ ሕይዎታቸው ተፈጽሟል።

አምላካችን የልዕልት ዙርያሽወርቅን ነፍስ በደጋጎች ቀደምት አባቶቻችን አብርሃም ይሕሣቅና ያዕቆብ ባረፉበት የጽድቅ ቦታ ያሣርፍ ዘንድ ጽሎታችን ነው እንዲሁም ሐዘናቸው ሐዘናችን ለሆነው ለውድ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ወገን ዘመዶቻቸው ኢትዮጵያውያን ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን።

ትውጻፈ መንገሻ መልኬ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *