አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ጋር ተወያዩ፡፡

በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ጋር እደተወያዩ በትዊተር ገፃቸው አሳወቁ።

ውይይቱ የነበረው ስደተኞችን ከመጠበቅ ፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ለስደተኞች እየተሰጠ ስለሚገኘው የኮቪድ 19 ምላሽን በተመለከተ መሆኑን በመልዕክታቸው ገልፀዋል።

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ፥ ኢትዮጵያ የስደተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ እና ለመከላከል ለረጂም ጊዜ የሚዘልቅ ዝግጁነት እንዳላት ለፊሊፖ ግራንዴ ነግረዋቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.