የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ከተወከሉበት አገር ወደ አዲስ አበባ ለግምገማ ሁሉንም ጠርቶ አስገብቷል።

0
0 0
Read Time:1 Minute, 35 Second


አምባሳደሮቹ የተጠሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየዓመቱ በሚያዘጋጀው የአምባሳደሮቹ የዲፕሎማሲ ተግባራትን ግምገማና የቀጣይ ዓመት አጠቃላይ የውጭ ዲፕሎማሲ የትኩረት ጉዳዮች ላይ እንዲሳተፉ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።

ቃል አቀባዩ ባለፈው ዓርብ ነሐሴ 15 ቀን 2012 ዓ.ም. በሰጡት ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት፣ ወደ አገር እንዲመለሱ ከተጠሩት አምባሳደሮች ጋር ከሰኞ ነሐሴ 18 ቀን ጀምሮ በቢሾፍቱ ውይይት ይካሄዳል።

የዘንድሮው ዓመታዊ ስብሰባ ‹‹ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኳችን ለዘላቂ ሰላም፣ ለጋራ ተጠቃሚነትና ለአገራዊ ብልጽግናችን›› በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ የተናገሩት አምባሳደር ዲና፣ የአምባሳደሮቹ ስብሰባው ለ15 ቀናት እንደሚቆይ ገልጸዋል።

በስብሰባውም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የሚሲዮኖቹ ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እንደሚካሄድ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የ2013 በጀት ዓመት የትኩረት ዕቅዶች፣ የቀጣይ አምስትና የአሥር ዓመት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ መሪ ዕቅዶች ላይ ውይይት እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

በተጨማሪም በተሻሻለው የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲና በተለያዩ አገራዊ ፖሊሲዎች ላይ ለአምባሳደሮቹ ሥልጠናና ውይይት እንደሚካሄድም አመልክተዋል።

በመጨረሻም ስብሰባው የአገሪቱ የበላይ አመራሮች በሚሰጡት መመርያ እንደሚጠናቀቅ አምባሳደር ዲና ጠቁመዋል። በውጭ ግንኙነት ዘርፍ ባለፈው ሳምንት ከተከናወኑ አንኳር ጉዳዮች መካከል አንዱ፣ በጂቡቲ የሚገኙ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያዊያንን የአገሪቱ መንግሥት እንዳያስወጣ ለማግባባት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ቡድን ተልኮ ከጂቡቲ መንግሥት አመራሮች ጋር መምከሩን ቃል አቀባዩ አመልክተዋል።

ወደ ጂቡቲ የተላከው የዲፕሎማሲ ቡድን የተመራው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ እንደሆነ የተጠቆሙት ቃል አቀባዩ፣ ሚኒስትር ዲኤታዋ ከጂቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ከአገሪቱ የውስጥ ደኅንነት ኃላፊ፣ ከፖሊስ ኮሚሽነሩ፣ በጂቡቲ የዓለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት ተወካይና የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን ገልጸዋል።

የውይይታቸው ትኩረትም በጂቡቲ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ባሉበት ሆነው ድጋፍ የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻች እንዲሁም የጂቡቲ መንግሥት በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አያያዝ መብታቸውን በጠበቀ መልኩ ሊሆን እንደሚገባው መምከራቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያና ጂቡቲ መካከል ያለው የኢኮኖሚ ግንኙነት እንዲጠናከር ከጂቡቲ ንግድ ምክር ቤት ኃላፊዎች ጋርም ውይይት ማካሄዳቸውን አምባሳደር ዲና ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ወደ አገራቸው ለመመለስ ላመለከቱ በቤሩት ለሚገኙ 180 ኢትዮጵያዊያን፣ ቤሩት በሚገኘው የኢፌዲሪ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት አማካይነት የሰነድ ማዘጋጅት ሥራ መሠራቱን ተናግረዋል።

በተመሳሳይም በየመን የሚገኙ 1,200 ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ ከሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በትብብር እየተሠራ መሆኑን፣ እንዲሁም በሳዑዲ ዓረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ደኅንነት ለማስጠበቅ ከሳዑዲ ንጉሥ ጋር ውይይት መደረጉን ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *