ዞኑ ይህን ያሳወቀው ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል ነው።

የዞን ም/አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ደጀኔ ለሬድዮ ጣቢያው ፥ ” ትናንት ሌሊት 8 ሰዓት ሲሆን ነፋስ መውጫ ማረሚያ ቤትና ሌሎች ሁለት ፖሊስ ጣቢያዎች እስረኛ ለማስፈታት ከሞከሩት ዘራፊ ካሏቸው ታጣቂዎች መካከል 16ቱ ሲገደሉ 20 ተማርከዋል ” ሲሉ ተናግረዋል።

ከመንግስት በኩል ሶስት የፀጥታ አካላት መቁሰላቸውን ጠቁመዋል።

አቶ ጥላሁን ፤ ” ዘራፊ ” ያሏቸው አካላት ከተለያዩ አጎራባች ዞኖች የተሰባሰቡ ነበሩ ብለዋል።

ከማረሚያ ቤት ወጥተው ከነበሩት ታራሚዎች መካከል 65ቱ በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳና በደቡብ ጎንደር ዞን ጋይንት ወረዳ በተውጣጡ ጥምር የፀጥታ አካላት ቅንጅት በያሉበት ተይዘው መመለሳቸውንም አቶ ጥላሁን አመልክተዋል።

ዛሬ የባህር ዳር – ወልዲያ መስመር ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ እንደነበር እና ታጣቂዎቹ በሶስት ተለያዩ መኪናዎች የመጡ እንደነበሩ፤ ተሸከርካሪዎቹም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነዋሪዎች እንደገለፁ የሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.