0 0
Read Time:30 Second

ከደቡብ አፍሪካው የሰላም ስምምነት መልስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በአዲስ አበባ የሰላም ሂደቱ፣ ውጤት እና አንድምታው ላይ ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ ላይ የሁለቱ ምክርቤት አፈጉባኤዎች፣ ርዕሰ መስተዳድሮች እና ሚንስትሮች ተገኝተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬዲዋን ሁሴን በውይይቱ የተደረሰውን ስምምነት በተመለከተ አጠቃላይ ገለፃ መደረጉን ተናግረዋል።

የሰላም ስምምነቱ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ያስጠበቀና የሀገር ሉዓላዊነትን ያከበረ ነው ብለዋል።

የሰላም ስምምነቱ የባከኑ ጊዚያትን የሚክስና የተጉዱ አካባቢዎችን በመልሶ ግንባታ ለማስተካከል ትኩረት የሚሰጥ መሆኑን አምባሳደር ሬድዋን በውይይቱ ላይ መነሳቱን ገልጸዋል ።

በጦርነቱ የተጎዳችው ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን በመሆናቸው የሰላም ስምምነቱ ጥቅሙ የሁሉም ነው ብለዋል።

የስምምነቱ አተገባበር ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባልም ብለዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *