አቶ ጃዋር የቪዲዮ ኮንፈረንስ ተዘጋጅቶለት ባለቤቱንና ልጁን አግኝቶ መነጋራቸውንም ፖሊስ ማረጋገጡን የፍርድቤቱ ዳኛ ተናግሩ፡፡

0
0 0
Read Time:1 Minute, 16 Second

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርምራ ቢሮ ለፍርድ ቤት በላከው ደብዳቤ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ ሐምዛ አዳነና አቶ ሸምሰዲን ጠሀ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸው ነፃ መሆናቸው መረጋገጡን አስታውቋል፡፡

አቶ ጃዋር የቪዲዮ ኮንፈረንስ ተዘጋጅቶለት ባለቤቱንና ልጁን አግኝቶ መነጋራቸውንም ፖሊስ ማረጋገጡን የፍርድቤቱ ዳኛ ተናግሩ፡፡ ሕክምናን በሚመለከት ግን በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሠረት እንደማንኛውም ተጠርጣሪ በፌዴራል ፖሊስ ሪፈራል ሐኪም ቤት እንዲታከም ተጠይቆ ‹‹በራሴ ሐኪም ካልሆነ አልታከምም›› በማለት ፈቃደኛ አለመሆኑንም የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ በደብዳቤ ማሳወቁን ፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡

አቶ ጃዋር እንደገለጸው፣ ነሐሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም. መታመሙን ለፍርድ ቤት ማሳወቁንና በዕለቱም ሲመለስ ሕመሙ ፀንቶበት ሲያስመልሰው ማደሩን ተናግሯል፡፡ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ ‹‹አላመመውም›› የሚል መግለጫ እንደተሰጠበት ጠቁሞ ‹‹አዝናለሁ›› ብሏል፡፡

እዚህ አገር የእሱን ያህል ጠላት ያለው እንደሌለና ቤቱ በፌዴራል ፖሊስ እየተጠበቀ መሆኑን የተናገረው አቶ ጃዋር፣ ጠላቱ መንግሥት ሳይሆን በመንግሥት ውስጥ ያሉ ሰዎች መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡ ‹‹መድኃኒት ብወስድ ልመረዝና ልገደል ስለምችል እኔ በማላውቀው ሐኪም መታከም አልፈልግም፤›› ብሏል፡፡ ምግብ ሲበላ ስለሚያስመልሰው መመገብ ማቆሙን አስታውቆ፣ ‹‹አዕምሮዬን ብስት እንኳን በማላውቀው ሐኪም መነካት አልፈልግም፤›› በማለት የሚናገረው ለሪከርድ እንዲያዝለት መሆኑንም ገልጿል፡፡

አቶ ጃዋር፣ አቶ በቀለ ገርባና አቶ ሐምዛን ጨምሮ ለ14 ተጠርጣሪዎች የቆሙት ጠበቆችም ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡ አቤቱታ፣ ፍርድ ቤቱ ሰጥቶት በነበረው ትዕዛዝ መሠረት ደንበኞቻቸውን ለማግኘት በተለይ አቶ ጃዋርና አቶ በቀለን ጨምሮ አራት ተጠርጣሪዎች ታስረው በሚገኙበት የቀድሞ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በተደጋጋሚ ቢመላለሱም፣ በሚገናኙበት ቦታ ላይ ተገጥሞ የነበረው ካሜራ አለመነሳቱን ተናግረዋል፡፡ ካሜራው እንደተነሳ ከፖሊሶች ተደውሎላቸው ተመልሰው የሄዱ ቢሆንም፣ ተጠርጣሪዎቹን ሊያገናኟቸው እንዳልቻሉ ጠቁመው ‹‹የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አልተከበረም›› ብለዋል፡፡ ፖሊስ ሲጠየቅ ከሥልጣኑ ውጭ መሆኑን እየገለጹና በሌላ አካል ትዕዛዝ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እየተጣሰ ባለበት ሁኔታ ‹‹ተባብረን በቅንነት ካልሠራን በዚህ ሁኔታ ወደፊት መራመድ አንችልም፤›› ብለዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *