ኦታ ቤንጋ፦ በሃገረ አሜሪካ እንደ ብርቅዬ አውሬ ና የዱር አራዊት ለመታየት ታፍኖ የተውሰደው ብላቴን።

0
0 0
Read Time:1 Minute, 5 Second

ኦታ ቤንጋ በ 1904 እ.ኤ.አ. ከ አሁኗ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪብሊክ ከምትባለው ተጠልፎ እንደ ዱር አራዊት በሃገረ አሜሪካ “እንደ ብርቅዬ አውሬ” ለመታየት ወደ አሜሪካ ተጠርዞ ተወሰደ ፡፡

ኦታ ቤንጋ


ኦታ ቤንጋ ማን ነበር?

እ.ኤ.አ. ማርች 1904 በዚያን ጊዜ ቤልጂየም ኮንጎ ነበር ፡፡ የእሱ ዕድሜ አይታወቅም ፣ ምናልባት 12 ወይም 13 ሊሆን ይችላል

በዚያ ዓመት መጨረሻ ላይ በእስታንት ሉዊስ ወርልድ በተደረገው የዓለም የዱር አራዊት ትርኢት ላይ ከሌሎች ስምንት አፍሪቃዊያን ወጣት ወንዶች ጋር እንደ ዱር አወሬ ለመታየት በኒው ኦርሊንስ በመርከብ ተወሰደ ትርኢቱ በቂ አልባሳት ወይም መጠለያ ሳይኖርበት እስከ ክረምቱ ወራት ድረስ ቀጠለ።

እጅግ በጣም ብዙ ሰዎችን ለመሳብ በመስከረም ወር 1906 በኒው ዮርክ ብሮንክስ መካነ ትዕይንት ለ 20 ቀናት ታየ።

በክርስቲያን ሚኒስትሮች ቁጣ የዚህን ሰው እንደ አውሬ በግርግም ታስሮ ማስጎብኘት ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ። ነጻም ወጣ። በአሜሪካዊው ሬቭረንድ ጄምስ ጎርዶን ሥር በሚተዳደረው ወደ ኒው ዮርክ ሃዋርድ የጥቁሮች እና አናሳዎች ጥገኝንት በሚስጠው ማዕክል እንደ ጥገኛ ሰብ ተዛወረ ፡፡

እ.ኤ.አ. ጃንዋሪ 1910 በቨርጂኒያ ለጥቁር ተማሪዎች በሊንክበርግ ሥነ-መለኮታዊ መማሪያ ኮሌጅ መኖር ጀመረ።

እዚያም አብረውት ይሚኖሩትን ተማሪዋች አደን ማደንን እና ዓሳ ማጥመድን አስተማራቸው እንዲሁም አፍሪቃ አግርቤት በነበረበት ዘመን ውስጥ ስለፈጸማቸው ጀብዱና ታሪኮች ያወጋቸው ነበር።

ከግዜም በኋላ ወደ ቀዬ መንደሩ ወደ ውድ አገሩ ለመኖር በነበረው መጓጓት እና ፍላጎት በጠና ታሞ እና ተረብሾ ሲኖር በመጋቢት ወር 1916 ራሱን በደበቀበት በጠብመንጃ እራሱን አጥፋ ፡፡ ዕድሜው 25 ዓመት እንደሆነ ይታሰብ ነበር።

Source: Spectacle: The Astonishing Life of Ota Benga

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *