በታላቋ ብሪታኒያ ያለውን የኢትዮጵያ ኤምባሲን ቄሮዎች ደጃፉን ዘግተውታል።
አርቲስት ሹክሪ ጀማል “ቄሮ በሎንዶን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላለፉት አምስት ቀናት ሌት ተቀን ሠላማዊ ሠልፍ እያደረገ ነው።

Read Time:30 Second
አርቲስት ሹክሪ ጀማል “ቄሮ በሎንዶን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላለፉት ሶሰት ቀናት ሌት ተቀን ሠላማዊ ሠልፍ እያደረገ ነው።” ቄሮዎች ኤምባሲውን ማንም እንዳይገባ እንዳይወጣ አስዘግተንዋል እያሉ ይገኛሉ። የ ኤምባሲውን የሚሽን ወኪል ኢትዮጵያን ትሪቢውን ደውሎ ሲጠይቅ ኤምባሲው ስራውን እንደወትሮው እየሰራ ነው ነገርግን በኤምባሲወ ፊትለፊት የቆሙትን ሰላምዊ ሰልፈኞች ጉዳይ ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መመሪያ እየጠበቅን ነው። መመሪያው እንደደረስን በ ኤምባሲያችን ድህረ ገጽ የ ኤምባሲውን መመሪ እንገልጻልን በማለት ቅዳሜ ኦገስት 22 2020 የ ኤምባሲው ወኪል በቴክስት አሰውቀውናል።
በሌላ በኩል ዕለት ዐርብ የቄሮዎችን ወኪል ስለዚህ ጉዳይ ስንጠይቃቸው የኤምባሲው ወኪሎች ሊያነጋግሩን አይፈልጉም ብለዋልና የሰልፉ መሪ አርቲስት ሹክሪ ጀማል። ሙሉ ቃለ ምልልሱን በምስል ይዘን ቀርበናል ያድምጡ።