የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ሻንጋይ ለአንድ ሳምንት እንዳይበር ታገደ!

0
0 0
Read Time:49 Second

ወደ ሻንጋይ ለአንድ ሳምንት እንዳይበር ታገደ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ሻንጋይ የሚያደርገው በረራ ከነሃሴ 25 ጀምሮ ለአንድ ሳምንት እንዳይበር ታገደ። የቻይና ሲቪል አቪዬሽን አስተዳደር በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጓዢዎች ላይ ኮሮና ቫይረስ ማግኘቱን ተከትሎ እገዳው ተፈፃሚ እንዲሆን የተደረገ ሲሆን ባለፉት ሁለት ሳምንት ውስጥ በሲቪል አቪዬሽን ከታገዱ አለም አቀፍ በረራዎች አንዱ ሆኗል።

ET684 በተሰኘው በረራ ላይ የተሳፈሩ ስድስት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሳፋሪዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ፑንዶንግ አየር መንገድ ሲደርሱ መረጋገጡን የቻይና ሲቪል አቪዬሽን አስተዳደር አስታውቋል። እንደ አስተዳደሩ ፖሊሲ ከሆነ በማንኛውም አየር መንገድ ወደቻይና የሚገቡ ተሳፋሪዎች ለሶስት ሳምንታት በተከታታይ ሲመረመሩ ኔጋቲቭ ውጤት ካሳዩ የተሳፈሩበት አየር መንገድ በረራውን በሳምንት ሁለቴ ማድረግ ይችላል። በተቃራኒው ደግሞ አምስት ተሳፋሪዎች ፖዘቲቭ ሆነው ከተገኙ ለሁለት ሳምንት፣ አስር ተሳፋሪዎች ከያዛቸው ደግሞ ለአራት ሳምንት ከበረራ ይታገዳሉ።

የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሲባል ፖሊሲው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ10 በላይ በረራዎች ታግደዋል። ከታገዱት በረራዎች ውስጥ ከአቡዳቢ ወደ ሻንጋይ የሚበረው የኢቲሃድ አየር መንገድ ለሁለት ሳምንት፣ ከኮሎምቦ ወደ ሻንጋይ የሚበረው የስሪላንካ አየር መንገድ ለአራት ሳምንት እና ከማኒላ ወደ ሻንጋይ የሚበረው የቻይና የምስራቅ አየር መንገድ ለሁለት ሳምንት መታገዳቸው ሊጠቀስ ይችላል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *