ኢትዮጵያ አዲስ የብር ምስሎችን ለማተም 3.7 ቢሊዮን ብር (101 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር) አውጥታለች ተባለ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ወይዘሮ ይናገር ደሴ ባቀረቡት መግለጫ እንዳስታወቁት አዲስ የተዋወቁት የገንዘብ ኖቶች አገሪቱ መዝባሪዎችና የተቀናጁና የተደራጁ ውንጀለኞች ብርን በማከማቸትን ፣ አስመሳይ የብር ምስሎችን በማተም ፣ ሙስናን በማስፋፋትና እና ሌሎችን ብልሹ የውንጀልና የማጭበርበር ደባዎች ለመግታት እና ለማስቆም ይረዳሉ ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ማንኛውም ኩባንያ ወይም ግለሰብ ጥሬ ገንዘብ እስከ 1.5 ሚሊዮን ብር (41,000 ዶላር) ብቻ ማቆየት እንዲችል አቅጣጫዎችን አስተላልፋለች ፡፡ ከባንኮች የሚወጣው የገንዘብ ገንዘብ እንዲሁ ከ 100,000 ብር በላይ (2,737 ዶላር) መብለጥ የለበትም የሚል መተዳደሪያ ደንቦችንመ ስትተገብር ሰንብታለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ እንደተናገሩት መንግስታቸው ከ2018 ጀምሮ የደቀቀውን ኢኮኖሚ ለመታደግ በርካታ እርምጃዎችን ወስዷል ብለዋል ፡፡
“የወርስነው መንግስታዊ አስተዳደር የአገሪቱ ለሲቪል ሰርቫንት የድመኦዝ ክፍያ ለመፈፀም በቂ ገንዘብ የሌለው ባዶ ካዝና ነበር” ያሉት ሚኒስትሩ ሀገሪቱ ከፍተኛ የበጀት ጉድለት እና ከዘላቂ የዕዳ ደረጃ በላይ መሆኗንም አክለዋል ፡፡
ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደ ገለጹት እርሳቸው በሚመሩት መንግስት ጥረት የሃገሪቱን ሉዓላዊ የዕዳ ብዛት ከ35% ወደ 25% ዝቅ እንዳስደርጉት ተናግረዋል ፡፡