ከፍተኛ የህወሃት ጁንታ አመራሮች ሲደመሰሱ 9 ደግሞ በቁጥጥር ስር ዋሉ

0
0 0
Read Time:1 Minute, 48 Second

የሰሜን ዕዝን በ45 ደቂቃ ውስጥ መብረቃዊ ጥቃት በመፈጸም ከጥቅም ውጭ አድርገነዋል ያለውን የጁንታው አፈቀላጤ ሴኩቱሬን ጨምሮ 4 ከፍተኛ የህወሃት ጁንታ አመራሮች ሲደመሰሱ 9 ደግሞ በቁጥጥር ስር ዋሉ

የሰሜን ዕዝን በ45 ደቂቃ ውስጥ መብረቃዊ ጥቃት በመፈጸም ከጥቅም ውጭ አድርገነዋል ብሎ የገለፀው የጁንታው አፈቀላጤ ሴኩቱሬ ጌታቸውን ጨምሮ 4 ከፍተኛ የጁንታው ቡድን አመራሮች ከነአጃቢዎቻቸውና ጠባቂዎቻቸው ተደመሰሱ፤ ሌሎች 9 የጁንታው ከፍተኛ አመራሮችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የመከላከያ ሰራዊት ሃይል ስምሪት መምሪያ ሃላፊ ብርጋዴል ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ እንደገለፁት ሴኩቱሬ ጌታቸውና ዘርአይ አስገዶምን ጨምሮ በርካቶች ሲደመሰሱ ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ እና ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔና ሌሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በዚህም መሰረት፣

 1. የጁንታው ቃል አቀባይ ሴኩቱሬ ጌታቸው፣
 2. ዘርአይ አስገዶም የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅና የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበረ፣
 3. አበበ አስገዶም የድምጸ ወያኔ ሃላፊ የነበረ፣
 4. ዳንኤል አሰፋ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበረ ከሹፌሮቻቸውና ከጥበቃዎቻቸው ጋር በጀግናው የመከላከያ ሰራዊት፣ በፌዴራል የጸጥታ ተቋማትና በትግራይ ህዝብና በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በተደረገ የተቀናጀ ዘመቻ መደምሰሳቸውን ብርጋዴል ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ተናግረዋል።

ከተደመሰሱት ውስጥ ሴኩቱሬ ጌታቸው ከዚህ ቀደም በጁንታው መገናኛ ብዙሃን በኩል ጁንታው የመከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ መብረቃዊ ጥቃት ፈፅሟል ብሎ ማረጋገጡ ይታወሳል።

ከተደመሰሱት በተጨማሪም 9 የጁንታው ቁልፍ አባላት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን እነሱም፣

 1. ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ የቀድሞ የክልሉ አፈጉባኤ የነበረች፣
 2. ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ የቀድሞ የትግራይ ክልል ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የነበረ፣
 3. አቶ ተክለወይኒ አሰፋ የማረት ስራ አስፈጻሚ የነበረ፣
 4. አቶ ገብረመድህን ተወልደ የክልሉ ንግድ ቢሮ ሃላፊ የነበረ፣
 5. አቶ ወልደጊዮርጊስ ደስታ የክልሉ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የነበረ፣
 6. አምባሳደር አባዲ ዘሙ በሱዳን የኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር የነበረና የጁንታውን ፖለቲካ ክንፍ የተቀላቀለ፣
 7. አቶ ቴዎድሮስ ሃጎስ የመለስ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንትና የኢፈርት ቦርድ ሃላፊ የነበረ፣
 8. ወይዘሮ ምህረት ተክላይ የክልሉ ምክር ቤት ህግ አማካሪ የነበረች እንዲሁም
 9. አቶ ብርሃነ አደም መሃመድ የክልሉ የንብረትና ግዢ ስራ ሂደት ሃላፊ የነበረ ሁሉም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የህወሃት ጁንታ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር የዋሉት በጫካና ዋሻ ለዋሻ ሲንቀሳቀሱ በተደረገ ጠንካራ አሰሳ መሆኑንም ብርጋዴል ጀኔራሉ ገልጸዋል።

የአገር መከላከያ ሰራዊት እነዚህ የጁንታው ቁልፍ የጥፋት ቡድን አባላት እንዲደመሰሱና በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ያላሰለሰ ድጋፍ ላደረገው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ምስጋናውን አቅርቧል።

ሰራዊቱ ወንጀለኞቹን አድኖ ለመያዝ ቃል በገባው መሰረት ግዳጁን እየተወጣ መሆኑን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት የጀመረውን ቀሪ የጁንታውን ርዝራዦችን አድኖ ለመያዝና በህግ ተጠያቂ ለማድረግ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ አረጋግጠዋል።

ህዝቡ እያደረገ ያለውን ድጋፍና ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አስተላልፈዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *