የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የመተከል ዞን በፌዴራል የፀጥታ መዋቅር ሥር መሆን አለበት አለ

0
0 0
Read Time:1 Minute, 27 Second


የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር)
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በመተከል ዞን እየደረሰ ያለው የሰብዓዊ መብት ቀውስ፣ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መንግሥት ሕግ የማስከበር አቅም በላይ በመሆኑ፣ የዞን አስተዳደሩን በጊዜያዊነት በፌዴራል የፀጥታ መዋቅር ሥር በማድረግ ሁኔታውን ማረጋጋት እንደሚገባ አሳሰበ፡፡

የኢሰመኮ ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ በመተከልና በአካባቢው ያለው የሰላምና ደኅንነት ችግር ከአሳሳቢ በላይ ሆኗል፡፡ አሁን ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ በሥጋት ላይ ያሉትንም የሚታደግ ፈጣን የሆነ የፀጥታ መዋቅር ሊኖር ይገባል ያሉት ኮሚሽነሩ፣ ይኼንን ለማድረግ ከክልሉ አቅም በላይ ሆኖ በመገኘቱ፣ ጠንካራ የሆነ የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ ገብነት እንደሚጠይቅ ተናግረዋል፡፡

በተለይ ታኅሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. ከሌሊቱ አሥር ሰዓት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ የታጠቁ ኃይሎች፣ በነዋሪዎች ላይ በለኮሱት እሳትና ተኩስ በርካቶች ከመሞታቸውም በተጨማሪ፣ በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውንና የተሰበሰበና በማሳ ላይ ያለ እህል መቃጠሉን የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ በዚህም ምክንያት ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል፣ ተሰደዋል፣ እንዲሁም ተበታትነዋል ብለዋል፡፡

በክልሉ የነዋሪዎችን ደኅንነት ከማረጋገጥ በተጨማሪ ፈጣን የሆነ የሕክምናና የሰብዓዊ ዕርዳታ ማድረግ እንደሚገባ ያሳስቡት ዳንኤል (ዶ/ር)፣ ኮሚሽኑ ግን ቦታው ድረስ ገብቶ የማጣራት ተግባር ለማከናወን የአካባቢው የፀጥታ ችግር እንቅፋት ሆኖበታል ብለዋል፡፡ ጥቃት የተፈጸመበት በኩጂ ቀበሌ ከዋናው ወረዳ 90 ኪሎ ሜትር እንደሚርቅና አካባቢውም መንገድ የሌለው በመሆኑ፣ እንኳንስ ድጋፍ ቀርቶ መረጃውም የሚደርሰው ጥቃቱ ከደረሰ በኋላ ዘግይቶ እንደሆነና ይህም ችግሩን ውስብስብ እንዳደረገው ገልጸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዓርብ ታኅሳስ 16 ቀን 2013 ዓ.ም. በኮንሶ ዞን በተደጋጋሚ ስላገረሸው ግጭትና የሰብዓዊ መብት ቀውስ መግለጫ አውጥቷል፡፡ በደቡብ ክልልና የኮንሶ ዞን ከኅዳር 1 እስከ 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ እንደገና ባገረሹ ተከታታይ ግጭቶች የደረሰው አሰቃቂ ግድያ፣ የአካል ጉዳት፣ መፈናቀልና የንብረት ውድመት መድረሱን አስታውቋል፡፡ 66 ያህል ሰዎች መገደላቸውንና 132,142 ሰዎች ደግሞ መፈናቀላቸውን ገልጿል፡፡ የአካባቢው ሰብዓዊ ቀውስ ዘላቂ ዕልባት ባለማግኘቱ እየተባባሰ ሄዷል ብሏል፡፡ ስለሆነም ለተፈናቃዮች በአፋጣኝ አስፈላጊውን ድጋፍ ከማቅረብ ባሻገር፣ የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት ሕዝቡን በማሳተፍ ዘላቂ ሰላም የሚያሰፍን መፍትሔ ሊሰጡ ይገባል ሲል ኮሚሽኑ በመግለጫው አሳስቧል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *