በኢትዮጵያ ኢምባሲዎች የሚታዩ ዕፀፆች፣ ብሄር ተኮርና የቡድን የተረኝነት አካኤድ ምክንያቶችና መፍትሄዎች

0
0 0
Read Time:13 Minute, 1 Second

የኢምባሲው ጁንታዎች ሽኝት፣ የተረኞች ትንቅንቅ ፣ የውስጥ እዋቂ
ታዛቢው ዶሴ


ከውስጥ አዋቂ

መግቢያ
ሰሞኑን በታላቅዋ ብሪታንያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ የሚታየውን ትንቅንቅ አስመልክቶ ፤ የተፈጠሩትን እሰጥ

አገባዎችና አስተያየቶች በኢትዮጵያ ትሪቢውን በሚባል በይነ መረብ የቀረበውን ውይይት በማስረገጥ የማውቀውን ያህል የውስጥ አዋቂ መረጃዎቸን ለኑዋሪውና ለመግለጫ ሰጭዎች ለማስረዳት ይህችን አጠር ያለች ፅሁፍ ከትቢያለሁ።
ወደ አምባሳደሮች በውጭ ሃገራት የሚያከናውኑትን ተግባራት ከመዘርዘራችን በፊት ዓለም አምናና ዘንድሮ የአምባሳደሮች/የእንደራሴዎች/ና የዲፕሎማቶችን ተግባራትና ውስጠ ወይራ ማንነት እንዴት እንደሚያስቀምጠው እንመልከት:
ከ17 ኛው ምዕተ ዓመት በፊት ቤንጃሚን ፍራክሊን የተባለ ፀሃፍት ቀደምት የሆነውን የአምባሳደሮች ተግባር ሲገልፅ” ቀን ተሌት እንቅልፍ ሳይተኙ፣ ሳይበገሩ፣ሳይገለባበጡ፣ረጋ ባለ፤ ትዕግስት በተሞላበት ፣ሳይታለሉ፣ በነገር ቢሸነቁሩትም ተቋቁመው፣ እውሸትና ማታለልን በመፀየፈ የሃገራቸውን ጉዳይና ጥቅም በሌሎች ሃገሮች የምያስጠብቁና የሚያስፈፅሙ ባለምያወች ብሎ ያስቀምጣቸዋል ፡
“The qualities of a diplomat are] sleepless tact, unmovable calmness, and a patience that no folly, no provocation, no blunders may shake.” Benjamin Franklin
ከላይ ከተጠቀሰው የመልካም ዘመን የአምባሳደሮች ተግባር በተቃርኖ ከ17ኛው ምህተ ዓመት በኋላ ኤነሪ ዎተን የተባለ ፀሃፊና ዲፕሌማት የዘመኑን የአምባሳደሮች ትልዕኮ ሲገልፅ “ የዘመኑ አምባሳደሮች ለመንግስታቸው ሃቀኛና ታማኝ በመሆን የሃገራቸውን መንግስት የፓለቲካ አጀንዳ አስፈፃሚ ለመሆን ቃል
በመግባት የሚመደቡ ሲሆን፤ እንዲሁም በተወከሉበት ሃገራት የሃገራቸውን ተጨባጭ እውነተኛውን ገፅታክማቅረብ ተቆጥበው ውሸት ውሸቷን በተገዥነት ስሜትና ግራ እያጋቡ ቀለብ የሚሰፈርላቸው” ብሎ
ያስቀምጣቸዋል።

Henry Wotton, the 17th-century writer anddiplomat, once observed that ፡ ”An ambassador ‘is an honest man sent abroad to lie and intrigue for the benefit of his country’”
ይህን ካልኩ በኋላ የአምባሳደሮች ተግባራት እንደሚከተለው አጠር ብሎ ይታተታል ፤ እምባሳደሮች የሃገራቸው ፕሬዝዳንት ወይም ሃገራቸው በጠቅላይ ሙኒስቴር የሚመራ ከሆነ የሃገራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩን ወክለው በወተወከሉበት ሃገር የሃገራቸውን ተጨባጭ ሁኔታ፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣የማህበራዊና መላ እንቅስቃሴዎች ከመንግስታቸው መሪዎች ጋር በመመካከር የሚያስረድ፣የሚያብራሩ ናቸው፡፡

የተወከሉበት ሃገራት መንግስታት አጣዳፊ መልስ የሚሹ ጥያቄዎች ካነሱ ቀርበው መግለጫ የሚሰጡ፡፡ እንዲሁም የሃገራቸውን የኢኮኖሚ፤ማህበራዊ፤ፖለቲካዊ ቁመና ለማጠነከር የሚተጉ፤ የሃገርን ገፀታ ከፍ ከፍ እንዲል የሚጥሩና የሃገርን ጥቅም በተወከሉበት ሃገራት የሚያስጠብቁ በሙያው የተካኑ ሙያተኞች ናቸው፡ ፡ ለተለያዩ ሃገራት አምባሳደሮች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በተወከሉበት ሃገራት እይተዘዋወሩ የሚያስረዱ ናቸው።

ከዚህ ባሻገር በተወከለበት ሃገራት ንዋሪ የሆኑ የሃገራቸው ተወልጅ ዜጎችና ስደተኞችን ጥቅም የሚያሰጠብቁና ደህንነታቸውን የሚከታተሉ መሆን እንዳለባቸው የሙያው ዝርዝር ተግባራቸው በዙህ መልክ ሊቀመጥ ይችላል።
በሌላ አገላለፅ ደግሞ ከላይ የተዘረዘረው ግልጽ ተግባራዊ የስራ ዝርዝር እንዳለ ሆኖ ፕሮፌሰር ዴቩድ ዳን የተባሉ የበርሚንግሃም ዮኒቭርሱቲ የዲፖሎማቲክ ዘርፉ ተመራማሪ ” ዲፓሎማሲ ቃሉ ራሱ እንደሚያመለክተው በሁለት ሃገሮች በአምባሳደሮቻቸው/በዱፕሎማቶቻቸው/ በኩል የማይገለፁና የማገለፁ
ሚስጥራዊ ስራዎች የሚከወኑበት ፤ በአንድ ወረቀት በፊትና ጀርባ ላይ በግልፅ የሚነበቡና የማይነበቡ ድብቅ ክንውኖችንና ትልዕኮዎች ተነድፈው በሁለትዬሽ ሃገራት የሚከወኑ ስራዎች የሚያስፈፅም የሙያ ዘርፍ ነው ብለው አስቀምጠውታል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ሁለት ዓይነት የአምባሳዳርነት ስልጣን የሹመት እርከኖች እንዳሉ ማህበረሰብ ማወቅ የግድ ይለዋል እነሱም እንደኛው ሹመት ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ አምባሳደሮች በኢኮኖሚውና በፓለቲካው እንቅስቃሴ በዓለም ላይ አንቱ የታባሉና ተፅእኖ ፈጣሪ ናቸው በሚባሉ ሃያልን ሃገራትና ታላላቅ አለም እቅፍ እንዱሁም የአለም መንግስታት ድርጅቶች ባሉበት አገሮች የሚመደቡት ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ተብለው ይሾማለ። ባለሙሉ ስልጣን ተብለው የሚሾሙ አምባሳደሮች የአገራቸውን ርዕሰ ብሄርና ጠቅላይ ሚኒስተር ተግባራት ተሸክመው የሚንቀሳቀሱ በመሆኑ ከርዕሰ ብሄሮችና ጠቅላይ ሚኒስትሮች መማከር ሳያስፈልጋቸው ወይም ማማከር የግድ ባለሆኑባቸው ገዳዮች መወሰን ይችላሉ። ነገር ግን በራሳቸው
ተነሳሽነት መወሰን የማይችሉ ያለ ቅጥያ አምባሳደር ተብለው ይጠራሉ። ይህን ነጥብ ያነሳሁት በኢትዮጵያ ትሪቢዮን ውይይት ከሚተላለፉ ቃለ ምልልሶች ተወያዮች ይህ መረጃ ሊኖራቸውና ሊያውቁ ይገባል በሚል ነው።


‘By its very nature, diplomacy involves secret communications between states, and between envoys and their governments,’ says David Dunn, professor of international politics at the University of Birmingham. ‘Indeed the word itself — diplomacy — means a paper folded in two to keep it confidential. It is the embassy’s job to rep – resent the home government abroad but also, crucially, to provide candid analysis of
the state of politics and leadership in the receiving country.”


ሌላው ኢትይጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ /Diaspora/ የሚባል ከኢምባሲ አገልግሎት የሚፈልግ፤የሃገሩን ጉዳይ ጠያቂ፤ እውቀት አሻጋሪ ተብሎ የሚታሰብ ማህበረሰብ አለ፡፡ ይህን ማህበረስብ የሚያሰባስብ የዲያስፖራ ተወካይ ከዲያስፖራው ተመርጦ በቅጥር ኢምባሲ ውስጥ ተመድቦ የሚያግለግል ባለሙያ አለ፡ ፡ መልካም የዲያስፖራ አሰባሳቢዎች እንዳሉ ሁሉ ሊትዮጵያዊውና ትውልደ ኢትዮጵያዊው ጠበቃ ከመቆም ይልቅ የመንግስት መራጆች፤ ቀፈታቸውን የዘረገፉ አልጠግብ ባይ ዝሆኖች፤ ቀበሮወች ፤ አፋጆወች፤ እንደ ጁንታው ተሞዳምዶው ባለሃብት የሆኑና መንግስት በተለወጠ ቁጥር እንደስስት እየተገለባበጡ መኖር የሚሹ እንዳሉ ልታወቅ ይገባል ፡፡ ወገን የነዚህ ሰለባ እንዳይሆን ሊጠነቀቅ ይገባል እንላለን፡፡


በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያጋጠመኝን የስራ አቀጣጠር መስፈርታቸውና አካሄድና በተመለከተ: በኢትዮጵያ ታሪቪውን ከተነሱት መከራከራያ ነጥቦች የዲፕሎማቶች አቅምን አስመልክቶና በጉቦ ዲፕሉማቶች ይመደባሉ የሚለውን የውይይት ሃስብ የኢትዮጵያ ትሪቡን /በይነ መረብ/ የሚዲያ እዘጋጅ ይሁን ባለቤት ደጋግሞ ጥያቄውን ቢያነሳውም ፣ በውይይቱ የተሳተፉት ለሙያው እንግዳ፤ ተጨባጩን የሃገራችን ሁኔታ ባለማውቃቸው ይመስለኛል በሃሳቡ ላይ መልስ የሚሰጥ አልተገኝም።
ይህን ተከትሎ የኔን ገጠመኝና በተለይ በታላቅዋ ብሪታንያ ያየሁትን ከዚህ ጭብጥ ሃሳብ ጋር አንተርሸ የታዝብኳቸውን ላክፍላችሁ።

እኔ የዚህ አጠር ያለ ፅሁፍ ከታቢ እስከማውቀው ድረስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሚመደቡ ወይም የሚቀጠሩ ለወደፉት ዲፕሎማት ወይም እምባሳደር ይሆናሉ ተብሎ የሚታሰብ በመሆኑ ከተቻለ በአለም እቀፍ ግንኙነት ና ፓለቲካል ሳይንስ (Political Science and international relations), በውጭ(በእንግሊዝኛ) ቋንቋወችና ስነ-ፅሁፍ( English Languages and Literature)ና በሕግ (Law)
ተመራቂወች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስርያ ቤት ቢቀላቀሉ ይመረጣል የሚል ሚዛን የሚደፋ መመዘኛ እንዳለ አውቃለሁ። ይህን አስታኮ ያጋጠመኝ በእርሻ ሙያ ተመራቂ የሆኑ ዲፕሎማቴች አጋጥመውኛል። ከዚህ ላይ ዲፕሎማት መሆን አይችሉም ማለቴ ሳይሆን ፣ ይህ ለምን ሆነ የሚለውን ጥያቄ መመለሱ ላይ ነው ዋናው ነጥብ ። ይህ የሆነው በነበረው ስርዓት የብሄር ብሄረሰቦችን በዚህ የሙያ መስክ በማመጣጠን ተሳትፎ እንዲኖራቸው የሚለው እሰራር የነበረው ስርዓት መመሪያ ስለሚያስገድድ ፣ የትምህርት ዕድል ያለአገኙትን ዳህጣን ብሔረሰቦች ለሙያው የሚመጥን የትምህርት ዝግጅት ይኖራቸዋል ተብሎ ስለማይታሰብ ቢያንስ በተገኘው ሙያ የተመረቁትን ሁሉ በዲፕሎማሲው ስራ ማሳተፉ ግድ ሆኖ ይሆናል የሚል ጭምጭምታ ያለ ይመስለኛል እላለሁ። ይህ አካሄድ ግን ጉዳቱን ከአለም አቀፍ መመዘኛዎች እንፃር
ጉዳቱና ጫናው ሊታይ የግድ የሚል ይሆናል።


ወደኔ የውጭ ጉዳይ መስሩያ ቤት የቅጥር ገጠመኝ ልምጣ። እኔ ትምህርቴን ካጠናቀቅኩ በኋላ ስራ የጅመርኩት በኢንዱስትሪ ሚኒስትር የህዝብ ግንኙነት ክፍል የነበረ ቢሆንም አብዛኛውን በአዲስ አበባ በሚገኙ በሚንስትሩ መስሪያ ቤት ስር በሚገኙ ፋብሪካዎች አገልገያልሁ።


ከዚያም ኢሕአድግ ወደስልጣን እንደመጣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር መስሪያ ቤት ከየመስራያ ቤቶች ባለሙያወችን ሲያሰባስብ በአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ በማህበራዊ ሳይንስ (Sociology) ሁለተኛ ድግሪየን እየተማርኩ እንዳለ ውጭ ጉዳይን እንድቀላቀል ጥሪ ይቀርብልኛል። የተማርኩት ትምህርት ለሙያው ቅርበት ስላለውና የምመኘውም ሙያ ስለነበረ እሽታየን ገልጨ የፅሁፉን ፈተናና ቃለ-መጠይቅ ለማድረግ ተዘጋጀሁ።
እንግዲህ አንባቢ ሊያውቀው የሚገባው ይህ የሆነው እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር 1988 ዓ ም. ይመስለኛል ። የሚያገባውን ዝግጅት አድርጌ ወደ ሃያ ከሚሆኑ ተጋባዥች ወደ ቃል ፈተና ገባን። የፅሁፍ ፈታናው በየወንበሩ ተሰራጨ። ከዚያም ጀምሩ ተባልን ፣ የፁሁፍ ፈተናውን ካጠናቀቃችሁ በኋላ ፉት ለፊት (Face
to face) ቃለ መጠይቅ ይኖራችኋልም ተባልን።

የቃል ፈተናው ከሙያው ጋር በጣም የራቀ ከመሆኑ ባሻገር የፓለቲካ አቋማችን ለመፈተሽ ነበር። ጥያቄዎችም የሚከታሉት ነበሩ

  1. Give your detail viewስ about the essence of “UNITY AND DIVERSitY” and state those countries that adhere this principle in their constitutions?
2. What is your view about article 39 of “The Rights of Nation and Nationalists to the extent of secessions” stated in Ethiopian Constitution?

3. What the phrase mean “Pet Aversion “?
እነዚህን ጥያቄዎች ሳነብ ወሽመጤ ተበጠሰ “ ለምን መጣሁ፣ ይህን አልደግፍም ልበል፣” እያልኩ ሳወጣ ሳወርድ፣ አንዳንዶቹ ሌጣውን ወረቀት እየሰጡ ሲወጡ እኔ ግን በመስሪያ ቤቱ የማገልገል የታመቀ ፍላጎት ስለነበረኝ የባጡን የቋጡን ፣ እደግፋለሁ ሳልል ሞነጫጭሬ ወጣሁ። ነገር ግን እኛ የሞነጫጨርነው ሳንቀጠር፣ ባዶ ወረቀት እየወረወሩ የወጡት የትምህርት ቤት ጓደኞቻችንን ተቀጠሩ፣ አምባሳደር ደረጃ ድረስ ደረሱ።
ይህን ጉዳይ ያነሳሁት በደርግ ጉዜ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተስፋየ ዲንቃ በነበሩበት ጊዜ ከነበሩት ልምድ ያላቸው ዲፕሎማት(Career diplomat) በስተቀር በውጭ ጉዳይ የሚቀጠሩት ፣ በብሄር ፣ብሄረሰብ ተዋፅኦ፣ በጋብቻ ትስስር ፣ በፓለቲካ አመለካከት ቀናይነት ወዘተ እንደሆነ ለመግለፅ በሚል ነው ይህን ገጠመኝ የከተብኩት፡፡ በኢትዮጵያ ትሪቢዩን በየነ መረብ የተነሳውን ሃሳብ እንደምጋራው የደቦ ፍርጃውን ለመጋራት አይዳዳኝም፡፡ የሌሎች የሰራሁባቸውን የህግ አርቃቂና ተርጓሚ የኢሕአዴግ የመንግስት መዋቅሮች ጉዳ ጉዶች ስጠይቅ አቀርባለሀ።ከዚያም የኢትዮጵያ የኢሕአዴግ መንግሥት ተብየው ቁመና ሲያንገፈግፈኝ ያገኘሁትን እድል አግኝቼ ወደ ታልቅዋ ብርታንያ እንግሊዝ ተገፍቸ ዘለቅኩ።የመጀመሪያው ዓላማየ ይህን ገነጣጣይና ለኢትዮጵያ ሕዝብ የማይበጅ መንግስት ለመታገል ነበር አመጣጤ። ይህን ዓላማየና ራዕየን ለማሳካት ያደርኩት ወደ እትዮጵያ ኮሚኒቲ ብቅ ጥልቅ እያልኩ ኢትዮጵያ ዊውንና
ትውልደ ኢትዮጵያዊውን ግንዛቤ እንዲጨብጥ ማድረግ ነበር።እንድ ጊዜ እድሉን አግኝቼ በኢሕአዴግ መንግስት ያለውን አፈና፣ሙስና ከማስገንዘብ አልፎ በተለይ ከ1997 ዓ.ም. አገራዊ ምርጫ በተከሰተው ግድያ ጋር ተያይዞ “ግድያው ተመጣጣኝ ነው አይደለም?” የሚል የጅሎች ውይይት በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የኦሮሞው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በተሳተፉበት ሲካሄድ የህግም ትምህርት ስለቀሰምኩ፣ የአባቶቻችን ትብዕል፣ ዘየና ህጋዊ ትርጓሜ ” ወገኖቸ በሕግ ፊት አንድ እንቀላል የሰረቀና አንድ በሬ የሰረቀ እኩል ወንጅለኞች ናቸው” ይልቅስ “አንድ ልጅ ለአንድ እናት ሚልዮን እንደመሆኑ በእናት ቁስል እትቀልዱ፣ይልቅስ የሰው ልጅ ትገሏል ወይስ አልተገደለም” ብላችሁ የሕግን መሰረታዊ ፅንሰ ሃሳብ ተገንዝባችሁ ተከራከሩ” ብየ ስናገር ፣ ቤቱ በጭብጨባ ተናጠ። መድረክም ተስጦኝ፣በኢትዮጵያ
ፓርላማ የፓርላማው ልዩ ረዳትና የኢትዮጵያ ፓርላማ ረዳት አስተዳዳሪ “ ነበርኩ ብየ ጉዱን ዘረገፍከት። በዚያን ጊዜ የለንደንን ፓለቲካ ይዘውረት የነበሩት አቶ ጎሞራውና ተቀጥያው ወንድሙ መኮንን ነበሩና ከአቶ ገሞራው ጋር ኮሚኒቲ የኢሶልና የአማርኛ ቋንቋ እናስተምር ስለነበር በጋራ ለመታገል ተግባቦት ላይ ገባን ፤
ስልካችን ተለዋውጥን። ብዙ ሳይቆይ አካሄዳችው ስላላማረኝ ትግሉን ተረጋግቸ ለመቀጠል ሞከርኩ። ነገር ግን ከነወንድሙ መኮነንና አቶ ጎሞራው ጋር መጓዝ ስላልቻልኩ ስሜን “ A to Tezera Asegu Special Assistant of Dawit Yohannes, though he is born in Ethiopia ,he is half Eritrean “ ብለው ስሜን አጠልሽተው፣ እኔም ከትግሉ ልያሸሹኝ ሞከሩ።
ከዚያ በቆራጥነት ያመራሁት “ክወልቃይት፣ ጠገዴና ሰቲት ሁመራን” ወደ ትግራይ መካለል የሚደረገውን ትግል የሚጋራ ዲያስፓራ ባለመኖሩ ፣ ፉት ለፊት ለመጋፈጥ ወደ ኢምባሲ ስዘልቅ “ ይህ ኢምባሲ እባቶቻችን በከፈሉት ግብር የተገዛ በመሆኑ ማን ይሁን ማን የተለየ የፓለቲካ አቋም ቢኖረውም ፣ ሊስተናገድበት መብቱ” ነው በሚል ንግግሬ ይሁንታን አግኝቶ መመላለስ፣ በስብሰባዎች መጋበዝና ለሃገሬና ለህዝቤ መጮህ፣
ጀመርኩ፣በተቃዋሚ ነን ባዮች ቅንጅት፣ግንቦት ሰባት ያላገኘሀትን መድረክ አግኝቼ፣እንደሌሎቹ ፈርቸ ሳይሆን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ትግሌን “ውስጡን ለቄስ “ ብየ ጀመርኩ ።
እንግዲህ ይሄን እደረኩ፣ ይሄን ተናገርኩ፣ተጋፈጥኩ ለሚለው ከነበሩት ጥቂት ሰንኮች ባላመልጥም ይህን ጉዳይ ለታዳሚው፣ ለሕዝቡና ለህሊናየ ትቸው በኢትዮጵያ ትሪቢውን ከተደረገው ውይይት አንፃር የኢትዮጵያ ኢምባሲ በታለቅዋ ብሪታንያ ይታዩ የነበረ ጥንካራ ጎኖችና ዕፀፆች ለማተት እሞክራለሁ።

ከለውጡ በፊት የነበረው የኢምባሲዎች ቁመና

ከላይ ስለ አምባሳደሮች አለም እቀፋዊ ተልዕኮዎች አስመልክቶ ከተዘረዘረው ፅንሰ ሃስብ እንፃር ሲታይ በአለም ዙሪያ ያሉ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች አምባሳደሮች በተቃርኖ አብዛኛዎቹ የየብሄራቸው ፓርቲ አባላት ናቸው። ስለዚህ ለሃገረ ኢትዮጵያ ዘብ ከመቆም ይልቅ የኢሕአዴግ ፓርቲ ጋሻ ጃግሬዎች ነበሩ። ከዚያም ዝቅ ሱሉ ለየብሄራችው ጋሻና መከታ በመሆን የየራሳቸውን ብሄር ተወላጆች በየኢምቢሲያቸው
ይኮለኩላሉ።

እንድ ነገር መታወቅ ያለበት የኢምባሲው አምባሳደሮች ሆነ ዲፕሎማቶች የሌላ ብሄር አባል በተለይ የአማራ ተወልጅ ከሆኑ በዐይነ ቁራኛ የሚከታተላቸው የበላይ የሆነው ፓርቲ ከእኛ ሃገር እንፃር የህውሃት አባላት ስለሚመደብ ራሳቸውን ሆነው አይቀሳቀሱም። ካፈነገጡ በግምገማ ወይ የመቆያ ጉዚያቸው አምስት አመታት አጥሮ ሳይጨርሱ ወደ ሃገር ቤት ሽንጣቸውን ጠቅልለው ለመመለስ ይገደዳሉ።

ሌላው በገዥው መደብ እንደ አጋር፣ ተለጣፊነታቸው አየል ያለውና ለክፉ አይሰጡንም ተብለው የሚታዩ ፓርቲዎች በኢምባሰው፣ በአምባሳደሩ፣ በዲፕሎማቶች ያላቸው ቦታ ከፍ ያለ ይሆናል።

ከዚህ እንፃር ባለፉት 27 ዓመታት የኢትዮጵያ ኢምባሲ ተጠቃሚዎች፣ ጋሻ ጃግሮዎች፣ቤተኞች፣አለን አለን ባዮች በደረጃ ሲቀመጡ በአንደኛ ደርጃ ዲፕሎማቶች በብዛት ጡረተኛ የህዋት ሃባላት የሚጨፍሩበት፣
ቀጥሎ ሱማሌዎች፣ ደቡቦች ከዚያ አማራ ያልሆኑ ቅይጥ እማራ ተብየዎች፣ ከዚያ ደፋር በየጊዜው የሚኮረኮሙ ለኢትዮጵያና አማራ ከመናገር የማይቦዝኑ ተብለው ይቀመጣሉ፡፡ ቡችሎታ ሁሉን የሚያስከነዱና ሊኢምባሲው ራስ ምታት የሆኑ አማሮች በውራነት የሚቀመጡ ሲሆን ኦሮሞች ካላቸው የፖለቲካ አቋም የተነሳ ኢምባሲው ውስጥ እንደዛሬ ሳይሆን ኢምባሲው የሲኦል ቤት ነበር ።

ከዚህ ላይ አንድ የሚያስደምመው ጉዳይ “እንዳይሸሽ በመጠን ጎትተው፣ ጠቅልሎ ውስጣውስጡን እንዳያውቅ በብልሃት ግፋው “ በሚለው የተንኮል ስልታቸው ይመለሳል ጥይቄ አለኝ ብሎ የሚመጣውን አማራ በዚህ መልክ ያስደናግቱታል፡፡ አማራው በዲፕሎማሲው የተፈጥሮ ዕውቀት ስላለው፣ እንደሚባለው ቢኢምባሲው አካባቢ የአቅም ውስንነት ስላለ አማሮች በበጎ ፍቃደኝነት ዲፕሎማቶችን ሰለሚያግዙ
በየገቡበት እየተከታተሉ እገዛ እንዲያደርግላቸው ይወተውቱታል። ከዚህ ባሻገር የአማራ ዲፕሎማቶች ሆነ አምባሳደሮች እንጀራ ሆኖባቸው እንጂ የሚደርስባቸው ግምገማ በገዥው መደብ የከፋ ስለሆነ ምን ቢሰሩ አይመሰገኑም፣ በዐይነ ቁራኛ ነው የሚታዩት፣ በአጠቃላይ ብዙዎቹ ደስታ ክላያቸው የራቀ፣ በራሳቸው እንዳይተማመኑ የተደረጉ ፣ ተፅእኖ የበዛባቸው ናቸው።

ሌላው በተቃዋሚ ጎራ የተሰለፉት እንደ ቅንጅት ፣ግንቦት ሰባት ያሉ ቡድኖች የዛሬውን አያድርገውና በነፍስ የሚፈላለጉ፣ እንደ አይጥና ድመት እርስ በእርሳቸው አድፍጠው እንዱ እንዱን ለመያዝ ፣ሌላው ለማምለጥ እየተጠባበቁ የሚኖሩ ነበሩ። ተቃዋሚዎች የኢንባሲውን ደጃፍ እንዳይረግጡ፣ ሃገራቸውን እንዳይጎበኙ ማዕቀብ እንዲጣልባቸው የኢምባሲ ተጠማኝ ፤ ተቀጣሪ ዘበኞች ይህን ፀያፍ ስራ ይደረጉ ነበር፡፡ በማንኛውም ማህበራዊ ግንኙነት ዘር እንዳይሉ፤ ክተግፕናኘም በድላና ቦክስ የሚዣለጡ ነብሩ።

ለውጥ መጧል በሚባልበት ወቅት እሁን የሚታየው የኢምባሲዎች ቁመና ምን ይመስላል? ለሚለው

እንግዲህ በኢትዮጵያ ትሪቢውን ሚዲያ /በይነ መረብ/ ለውይይት ቀርቦ አወያዩና ምላሽ ሰጭወች ተረኝነት በታላቅዋ ብሪታንያ ኢምባሲ ይታያል የሚል ፅንሰ ሃሳብ ቀርቦ በአንድ ምላሽ ሰጭ ምልሁ የሆነ ምላሽ ሰጥተዋል ። እርሳቸውም ሲናገሩ “አንዱ ልጅ ፣ ሌላውን የእንጀራ ልጅ” አድርጎ ማየት ወንጀል ከመሆኑ ባሻገር እምባሳደሩንም ሳይቀር ጥያቄ ውስጥ ያስገባል ብለዋል።

የሃሳባቸ ቅቡልነት አጠያያቂ አይደለም። ነገር ግን ምክንያቱን አንጥሮ ማውጣቱ የግድ ይላል። እንደሚታወቀው “ከበሬ በረት በግ አብሮ አያድርም” እንዲሉ እንደዚህ ቀደሙ የነበረውን የተለመደ ክስተትተከትሎ መሄዱ የኢምባሲውን የ27 ታሪክ ለሚያውቅ አይገርምም።

የሚገርመው ግን እነ ግንቦቴዎች/ የአሁኑ አዜማ ነን ባዮች/ ወደ ሁለተኛ የኢትዮጵያዊያን ቤታቸው በምን ሆነ ምን ወደ ኢምባሲ መግባታቸው ባይከፋም ሌሎችን እየፈረጅ ለማሸሸት መሞከራቸው የሚያፀይፍና
የማናለብኝነት አካሄድ ነው።

ማንኛውም ኢትዩጵያዊ ሰሳማዊ የሆነ የፓለቲካ ልዮነት ይዞ፤ ተቀራርቦና በሚያግባቡ ጉዳዮች ተቀራርቦ መነጋገሩ የለውጡ አንዱ እካል በመሆኑ ሉበረታታ ይገባል እንጂ በስመ ኢምባሲ ይሳተፍ ነበር ብሎ እየፈረጁና እያሸማቀቁ ማራቁ ህጋዊ አይደለም። ያለፈውን በነሱ ይደርስ የነበረን አድሏዉ ድርጊት በስመ ቂም በቀል ከአባራሪዎቻቸው ፣ ከከሳሾቻቸው ጋር ሁነው መፈፀማቸው የበታችነት ስሜት የተጠናወታቸው መሆኑን የሚያሳይ ነው።

ከዚህ ላይ ከዚህ በፊት አባሮሽ ይጫወቱ የነበሩ ባላንጣዎቻቸው ጋር አሲረው፤ የኢምባሲው የዲያስፓራ ክፍል ተጠሪዎች ችግሩን የጋራ መድረክ ፈጥረው ከመፍታት ይልቅ ድንጋይ ተሸክመው ና ተጎብሰው ይቅርታ በመጠየቅ ከዚህ በፊት በአጋርነት አብረው የሰሩትን ወንድሞቻቸውን የሌለ ገመና በመለደፍ “ እኔ ከተመቸኝ ፣ ለእንቺ መላ በይ” በሚል በኖሩበት ትበዕል ተጠምደውና ለማይርባ ደሞዝ ብለው እያጣሉና አሳልፈው እይሰጡ ከመጣው ጋር ማሽቃበጥ አግባብ አይደለም ።

ለአምሳደሮች ሆነ ለዲፕሎማቶች እውነታውን በማፍረጥረጥ መላ እንዲፈጠርና ችግሮች እንዲፈቱ ጥረት ማድረግ የግድ ይላቸው ነበር። እሳት እያቀበሉ የራስን መናኛ እንጀራ መጋገር ትዝብት ነው ትርፉ።

በአምባሳደሮችም ሆነ አዲስ በሚመደቡ እንግዳ ዲፕሎማቶች ብቻ መረጃ እስከሌላቸው ድረስና ድፍሮ ጉዳዩን እፍረጥርጦ የሚናገር የሚመለከተው ክፍል እስከሌለ ድረስ ፣ሁሉን በእንግዶች መለደፍ አግባብ አይደለም “ምን ተዳቸው” ፣ ስራቸው የሚመጣውን ማስተናገድ ነው።

ነገር ግን ዲፕሎማቶቹ እያወቁ “ይራሳቸውን ብሄር እያሰባሰቡ ክሆነ ይህ እየተሄደበት ያለው የዘቀጠ ከለውጥ ጋር የሚቃረን አደገኛ አካሄድ ኋላ ቀር ከመሆኑ ባሻገር እንደተባለው ትልቅ ወንጀልና የትም እንደማያድረስ ተገንዝበው የእርምት እርምጃ ሉወስዱና የሚኤዱበት ውርስ ዕፀፃቸው ሊነገራቸው የግድ ይላል። ይህ ዘር ተኮር ፣ የቡድን፣ የደቦ ለመልካም ስራ እንጅ ለተንኮል ስለማይበጅ፣ በተረኝነት ወንድምን ለማሽመድመድ መታተሩ ከኢትዮጵያ ባህል ጋር ስለማይሄድ ለአንዴና ለመጨረሻ መላ ሊበጅለት የግድ ይላል ።

ሌላው የቤተክርስቲያን ጉዳይን በተመለከተ በዐፄው ዘመን ሆነ ቀደም ባለው የኢትዮጵያ የመንግስት ሥርዓት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ና መንግስት መሳ ለመሳ ትጋግዘው ሃገርን ያስተዳድሩ ነበር። ነገር ግን አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታና በኢትዮጵያ የዕምነቶች መበራከት የተነሳ ይህ እካሄድ ተግ ያለ ይመስላል፡፡
ነገር ግን የብህላዊ ውርስ ተፅህኖው ስላለ አንዳዴም እየተደጋገፉ ቢሄድ አይጎዳም።

በእንግሊዝ ሃገር በምትገኘው ቅድስት ማሪያም የተከሰተው የመከፋፈል ሂደት መነሻው ለመግለፅ መዳዳቱ እስቸጋሪ ስለሆነ ይህ ሰንክ አምላክ መላ ይበለው እያልኩ በተደረገው ውይይት ግን በተረኝት ኢምባሲውን
እጁን ለመጠምዘዝ የሚደረግ የወገተኝነት አካሄድ ይታያል።

ትናንት የህውሃት ኢምባሲ ቤተክርስቲያናቺንን ግብቶ ያምሳል ይል የነበረው የአንድ ብሄርና የእነ ግንቦት ሰባት የአሁኑ እዜማ ቡድን መናገሻውን ኢምባሴ አድርጎ እጁን ለማስረዘምና ጉልበቱን እስከ ሲኖድስ ዘልቆ ለማፈርጠም መሞከር የጀመረው ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ስለመሆኑ መረጃ አለ።

ኤምባሲዎች በዕምንት ጉዳዬች በተለይ በቀኖናውና በእስተዳደር በኩል እንዳይገቡ ህግ የሚከለክላቸው መሆኑን ያውቃሉ። ነገር ግን የመገላገል፣የማስታረቅና የአማኞችን ደህንነትና ሰላም የመጠበቅ ሃገራዊ ሃላፊነት ስላለባቸው መረጃዎችንና ታሪካዊ ተግዳሮቶችን ከማስተላለፍ አልፎ ለአንዱ ወግነው ለመሄድ መሞከሩ
ክፍፍለና መወነጃጀሉ እየሰፋ ስልሚሄድ ለአካኤዳቸው ልጓም ሊያበጁ ይገባል።

የሰራተኛ ቅጥርና ስንብትን በተመለከተ በተቻለ መጠን ሆደ ስፊ ሆኖ ስተቶችን እያረሙ መጓዙ መልካም ቢሆንም በተቅጣሪና ቀጣሪ መካከል የተፈጠረውን ውል፣ ከነበረው የፓለቲካ ወገንተኝነት፣ከለውጡ ፍላጎትና አሁን ያለው የፓለቲካ እንድምታ ጋር ተያይዞ መንግሥት ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደሩ ባላቸው ምጥን ራስ ተነሳሽነት ከደርሳቸው መርጃ አንፃር የመወሰን መብት ስላላቸው በዚህ ጉዳይ ላይ ጠልቆ ለመተችት የሚያስቸግር ይሆናል

ማጠቃለያ
ማጠቃለያየን የማደርገው በሚዲያ(በበይነ መረቡ) በኢትዮጵያ ቲሪቪውን የታዘብኩትን ጠንካራና ኮስማና አካሄድ በማስመላከት ነው።

የኢትዮጵያ ትሪቢውን ይህን ውስጥ ለውስጥ የሚብላላ ፤ ስር የሰደደ ፤ የነበረና ተደጋግሞ እየተከወነ ያለ የኢምባሲ ዘር ተኮር አፀያፊ የታሪክ ቅብብሎሽ እንዲሁም የተረኝነት አካሄድ ለህዝብ ውይይት ማቅረቡ፣ መላ እንዲባል ድልድይ ሆኖ መነሳቱ ሊመሰገን ይገባል።

ትናንት ተገፍተናል የሚሉ ግንቦቴዎች እሁን እዜማ የሚባል ጠረን ያላቸው ቡድኖችና የአንድ ዘር ግልብጥ ስብስቦች በዕውቀታቸው ሳይሆን የተረኝነትን ስሜት አግበው ኢምባሲውን “ጀግና የወለደው” በሚል ስሜት መውረርና ሌላውን አስተዋፅኦ ያደረጉትን ኢትዮጵያዊያን ና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለማሸሽት መሞከር ክሰለጠነው ዓለም ጋር የማይመጣፕን የዘቀጠ እካኤድ መሆኑን ለማስተማር መሞከሩ እሰየው ሊይሰኘው ይገባል።

ያየሀትን የሚዲያው (የበይነ መረቡ) ድክመት ሲዳሰስ ቃለ መጠይቅ የቀረበላቸው ግለሰቦች ስለ ኢትዮጵያ ኢምባሲ የረጅም ጊዜ መልካም ስራዎችና ዕፀፆች ጥልቅ ዕውቀት የሌላቸው፣ ተገፍተው በሄዱት የኢምባሲው ባለውለታዎችና ይበቃቸዋል ተብሎ” እንደ እሮጌ አቁማዳ” በተወረወሩ ዜጎች ምትክ፣ የዲያስፓራ ኢምባሲ ተቀጣሪዎችን ዕድሜ ይስረዝማሉ ተብለው በሸፍጥ የተመለመሉትን አሰባስቦ እርባና የሌለው ቃለ-መጠይቅ ማድረግ የእንቶ ፈንቶ አካኤድ ነው ፡፡ የኢምባሲ ምልምል ቃል-መጠይቅ ምላሾች ጠንከር ባሉት የኦሮሞና ግንቦቴዎች ተገፍተው ስለወጡ ፤ ኢምባሲ ባሉ በፍራቻ ተረኛ ተባራሪ እንሆናለን ብለው ባሰቡና ከስራ በተሰናበቱት አካላት የተቀነባበረ ዝግጅት የሚመስል ሽታ አለው።

ሌላው የግለሰቦች መባረር ተረኛ ነን በሚሉ ከተፈፀመ፣ ስህተት ተሰርቶ ከሆነ ፍርድን ህዝብ እንዲሰጥ በማድረግ ፤ ከሰው ህሊና በላይ የሆኑትን ምክንያቶች ለሚመለከተው ና ለግለሰቡ ተትቶ ውይይቱ ማህበረሰብ ተኮር ቢሆን ይበጃል እንላለን።

ከዚህ በተጨማሪ በደቦ ፍረጃና በይባላል የኢምባሲው ዲፕሎማቶች “የሶስት ወር ደሞዝ እየለቀቁ ነው” በየአለማቱ በዲፕሎማትነት የሚመደቡት ብሎ በበይነ መረብ መልቀቁ የአቅም ማነስ፤የዘመድ አሰራር፤ ያለ ችሎታ ብሔር ተኮር የማመጣጥንና ሌሎች ችግሮች በግልፅ ቢታዩም ፤ ማስረጃ በእጅ እስክሌ ድረስ ተጠያቂ ስለሚያደርግዎ ፤ ሚስጥሩን ከውስጥ አዋቂ ነው ያገኙት ተብለው ጣጣ እንዳይገቡ ያስቡበት እላልሁ፡፡

አዘጋጁ ወይም የበይነ መረቡ የኢትዮጵያ ትሪቢዩን ባለቤት እውነታውን ለማውጣት የሄዱበት ዕርቀት የሚበረታታ ሆኖ የሚፈልጉትን ምላሽ በግለሰብ ጉዳይ ላይ ተጠያቂዎችን መጥመደ ፤ እውቀት ተኮርና ልምድ አዘል መልስ የሚመልስላቸው አጥተው እራሳቸው መላሽ፣ እራሳቸው ጠያቂ ለመሆን መዳዳታቸው፣ የድግግሞሽ መበራከት የሚያሳብቅ ተልዕኮ ዝግጅቱ በአጠቃላይ እንዳለው ያሳያል። ለወደፊቱ የጋዜጠኝነትን ካባ ተላብሰው ቢመጡ ትልቅ ስራ ይሰራሉ ተብሎ ይታሰባል።

ሰላሙን ፣አንድነቱን፣ ያምጣልን።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።
ተዘራ አሰጉ
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *