ሳማንታ ፖወር በኢትዮጵያ ማንን አገኙ ?

0
0 0
Read Time:45 Second

ሳምንታ ፓወር ሱዳን እንደነበሩ ቢታወቅም በይፋ በሚዲያ ሳይገለፅ፣ በመንግስትም የተባለ ነገር ሳይኖር እንዲሁም እሳቸው ሆነ ተቋማቸው UASID ያሉት ነገር ሳይሆር ዛሬ አዲስ አበባ ሆነው መግለጫ ሰጥተዋል።

ትላንት ነው ኢትዮጵያ የገቡት።

ፓወር በኢትዮጵያ ቆያታቸው ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተዋል።

እሳቸው እንዳሳወቁት ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና ከሰላም ሚኒስትር ሙፈርያት ካሚል ጋር ተገናኝተው ተወይያተዋል።

ሳማንታ ፓወር ዛሬ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ለማግኘት እና ለመወያየት ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከከተማ ውጭ እንደሆኑ እንደተነገራቸው ገልፀዋል።

ሳማንት አሁን ላይ ቆይታቸውን ያጠናቀቁ ይመስላል አብረዋቸው ያሉ ባልደረቦቻቸው እንደገለፁት ዛሬ ለሊት ወደአሜሪካ ይበራሉ።

ሳማንታ ፓወር የተለያዩ አሉባልታዎች ሊወሩ እንደሚችል ያነሱ ሲሆን የተሳሳቱ መረጃዎች በሚሰራጭበት ጊዜ መወያያት ብቸኛው መፍትሄ ነው ብለዋል።

ሳማንታ ፓወር ከአሜሪካ በተነሱበት ወቅት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይን ጨምሮ ከሌሎችም ባለስልጣናት ጋር እንደሚነጋገሩ አስበው ነበር የመጡት።

የጉብኝታቸው ዋነኛ አላማ በትግራይ ክልል ረሃብን ለመከላከል የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነት ከፍ እንዲል ለማድረግ በመንግስት ላይ ጫና ለማሳደር ነበር።

የመረጃ ባለቤት ፦ ጋዜጠኛ ኬኒዲ አባተ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *