ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ለተፈቱት አመራሮች ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ “እንኳን ለቤታችሁ አበቃችሁ” በማለት መልካም ምኞቷን ገልፃለች።

0
0 0
Read Time:44 Second

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በባልደራስ ዋና ፅ/ቤት በመገኘት ታህሳስ 29/2014 ዓ.ም ከእስር ለተፈቱት አቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ወ/ሮ ቀለብ ስዮም እና ወ/ሮ አስካለ ደምሌ” እንኳን ደስ ያላችሁ ፤ እንኳን ለቤታችሁ አበቃችሁ” በማለት መልካም ምኞቷን ገልፃለች።

አትሌቷ ከእስር ለተፈቱት አመራሮች መጭው ጊዜአቸው የተቃና እንዲሆን እና ኢትዮጵያም ሰላሟ፣ አንድነቷ እና ክብሯ እንዲመለስ ያላትን  ምኞት ገልፃለች።

የባልደራስ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ በበኩላቸው ኮማንሰር አትሎህ ደራርቱ የፓርቲው ፅ/ቤት ድረስ ቃሏን አክብራ በመልካም መንፈስ በመገኘት ይህንን እውቅና በመስጠቷ ከልብ አመስግነዋል።

በተጨማሪም “በቀጣይ በኢትዮጰያ ሰላምና ልማት ይሁን። ሲል መልካም ምኞቱን ገልፀዋል።

ሌሎች ከእስር የተፈቱ የፓርቲው አመራሮች አትሌቷ ቃሏን አክብራ በባልደራስ ዋና ፅ/ቤት በመገኘት “የእንኳን ደስ ያላችሁ”መልዕክት በማስተላለፏ የተሰማቸውን ደስታ መግለፃቸውን ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፥ ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ከእስር የተፈቱት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ከፍተኛ አመራር አቶ በቀለ ገርባን ” እንኳን ለቤትዎት አበቃዎት !! ” በማለት መልካም ምኞቷን ገልፃለች።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *