በኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ሙከራ መደረጉን ኢንሳ አስታወቀ፡፡

0
0 0
Read Time:30 Second

በኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ከ3 ሺህ 400 በላይ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጄንሲ ኢንሳ አስታውቋል፡፡

የኤጄንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ ባለፉት ጊዜያት በባንኮች፣ በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት፣ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ በክልል ቢሮዎች፣ የትምህርት ተቋማት፣ የሚዲያ ተቋማትና መሰል ተቋማት የሳይበር ጥቃት ኢላማ ተደርገው እንደነበር ገልጸዋል።

ከሰሞኑ በዋልታ የፌስቡክ ገጽ ላይ የደረሰዉ ጥቃት ያነሱት ዳይሬክተሩ “በሚዲያ ተቋሙ የፌስቡክ ገጽ ላይ የደረሰው ጥቃት ገጹን ከሚቆጣጠሩ ባለሙያዎች ጋር የተያያዘ መሆኑንም አሳውቀዋል፡፡

የዋልታ የፌስቡክ ገጽ ዋና ተቆጣጣሪ በሀገር ውስጥ አለመሆኑ ከጥቃቱ ጋር እንደሚያያዝ ያነሱት ሀላፊው፤ አክለውም የሚዲያዉን የፌስቡክ አካዉንት እንዲያንቀሳቅሱ ሃላፊነት በወሰዱ አካላት ስህተት መሆኑን ገልፀዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *