የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድቤት ባለፉት ስድስት ወራት ከ57ሺ በላይ መዝገቦች ላይ ወሳኔ መስጠቱን አስታወቀ፡፡

0
0 0
Read Time:43 Second

የአዲስ አበባ ከተማ ፈርድ ቤት በስድስት ወራት ውስጥ ለ57 ሺ 179 መዝገቦች ውሳኔ መሰጠቱን አስታውቋል፡፡

የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ተስፋዬ መለሰ የፍርድ ቤቶችን የስድስት ወራት ሪፖርት ለከተማው ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት ዋነኛ ግቦች ተደርገው ተሠርቷል።

ውሳኔ ካገኙት መዝገቦች ውስጥ 53 ሺ 374 ጉዳዮች በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ውሳኔ ያገኙ ሲሆን 3 ሺ 175 መዝገቦች ከተቀመጠው ስታንዳርድ በላይ ጊዜ መውሰዳቸውን ገልጸዋል።

በ2014 ግማሽ ዓመት በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ተሰጥቶባቸው ይግባኝ ከቀረበባቸው አንድ ሺ 163 ጉዳዮች ውስጥ 960 መዝገቦች ውሳኔ ማግኘታቸውን ገልጸው፤ 647 ጉዳዮች የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በማጽናት ሲወሰን 313 መዝገቦች የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ መሻሩን አስታውቀዋል።

በይግባኝ ሰሚ ችሎት ውሳኔ አግኝተው የሰበር አቤቱታ ከቀረበባቸው 343 ጉዳዮች ውስጥ ውሳኔ ካረፈባቸው 278 ጉዳዮች 1877 መዝገቦች ውሳኔ እንዲጸና ተደርጓል ያሉት አቶ ተስፋዬ፤ የ91 መዝገቦች ውሳኔ ተሰጥቷል። የፍርድ ቤቱ አጠቃላይ የውጤታማነት አማካይ አፈጻጸም 67. 3 መሆኑንም አስታውቀዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *