የኢትዮጵያ የሃገራዊ የውይይት መድረክ ግምገማ

0
0 0
Read Time:3 Minute, 50 Second

መግቢያ

ሃገራዊ የውይይት /National Dialogue/ መድረክ በተለያዩሃገራት ተከናውኗል ነገር ግን ውጤታማ የሆነው እፍኝበማይሞሉ አገራት ነው።

ለምሳሌ ያህል በሩዋንዳ “በሁቱና ቱትሲ” የዘር ጭፍጨፋ ፣በሳውዝ አፍሪካ” አፓርታይድ አገዛዝንና ኤንሲ/ANC/” ፣ ላይቤሪያ ፣ በኬኒያው የምርጫ ወቅት የተነሳው ግጭትወ.ዘ.ተ. የተከወኑ አገራዊ ምክክሮች /Public Dialogues/በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው።

ከላይ ከጠቀስኳቸው የምክክር መድረኮች የተዋጣለትና በስኬት የተጠናቀቀው የሩዋንዳው “ቱትሲና ኡቱ” ድርድር ነበር።

የተቀሩት ግን የሚጠበቅባቸውን የድርድር ስርአትና አካኤድ ስላልተከተሉ ውጤታማ አልሆኑም።

የተፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል፣ ማፈናቀል ወ.ዘ.ተ.እውነታዎች ነጥረው ስለ ወጡ ፣ በሁለት ጎራ በተቃዋሚነት የሚናረቱት/የሚዋጉት/ ቡድኖች እጅ ለእጅ ስለተጨባበጡዕርቅና ስምምነት ይመጣል ለማለት በታሪክ እንዳየነውያስቸግራል።

ወደ ኢትዮጵያ ሃገራዊ ድርድር/Nation Dialogue/ና ዕርቅ/National reconciliation/ ዝግጅት ስንመጣ ወደ ሃገራዊ ምክክር መድረክ ከመገባቱ በፊት መሟላት ያለባቸውየሚከተሉት ቅድመ ሁኔታወች ሊጠበቁ የግድ ይላል። እነሱም፣1) ትክክለኛ ሃገርና ህዝብ የተግባባባቸውና ስምምነት የደረሰባቸውን ታሪኮች አንጥሮ ማውጣትና ህዝብን ማስተማር የመጀመሪያውና ዋናው ወደ ሃገራዊ ምክክር የማግቢያ ዳዴ ማያ ስልት ነው ፣ 

በየመድረኩ የሚደሰኮሩ ሰው ሰራሽ /Fabricated/ ታሪኮች ሊገመገሙ፣ሊተቹና ታርመው ትክክለኛው የኢትዮጵያ ታሪክ ሊዘገብና ትውልዱ ሊማረውና ሊያውቀው የግድ ይላል።

የተመዘገቡና ያልተመዘገቡ የኢትዮጵያ ታሪኮች በታሪክ ሙሁራን፣ በአረጋዊያንና በተመራማሪዎች ለክርክር ቀርበው ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ታሪክ ማህበረሰቡ ሊያውቀው የግድ ይላል።

ፈረንጆች እኛን አፋጅተው እነሱ ሃገረ ኢትዮጵያን እንደ ልባቸው ሊንቀባረሩባትና የተፋጥሮ ሃብታችን ሊመዘብሩ የከተቡልን ታሪኮችን ወደ ጎን ልንላቸው ይገባል።2) ሕዝብ የጨፈጨፉ፣ እንዲጨፈጨፍ መ መሪያ የሰጡ ፣ያፈናቀሉ፣ ያንኮላሹ ፣ የደፈሩ ወ.ዘ.ተ. ማን ይሆን ማንወንጀል ፈፅመዋል የሚባሉ ሁሉ ህግ ፊት ቀርበውአግባብነት ያለውን ቅጣት ሊያገኙ የግድ ይላል፣

3) ያለአግባብ የተበደሉ ቡድኖችና ግለሰቦች የደረሰባቸውን ወንጀል፣ በደል፣ መፈናቀል፣ የአካል ጉዳት ፣ የአዕምሮ መጎዳት ለመጠገንና ለማስረሳት የካሳ /Reparations/ ክፍያ ሊመቻችላቸው የገባል፣

በጉልበት ፣ በብልጠት፣ በግለኝነት፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማግኘት፣ ከሌላው ህብረተሰብ በተለየ መልኩ ለማደግና የግል ዕድገትን የመጨቆኛ መሳሪያ ለማድረግ ታስቦባት (Intentionally) ተቆርሰው የተወሰድ መሬቶች ለነባርና በታሪክ ባለቤት ለሆኑ ህዝቦች ሊመለሱ ይገባል፣

 4) ሕዝብን እንደ ህዝብ የሚያቃቅሩ፣ ለሃገር አንድነት ሰንክና ሰላም የሚነሱ የሕገ መንግስት አንቀፆች ፣ ሕጎች ፣ ደንቦች ፣ መመሪያወች ወ.ዘ.ተ. በህግ ሊሻሩና ማሻሻል ያለባቸው ሊሻሻሉ ይገባል፣

 5) ሕዝብን በጋራ አግባብተው ሊያቆሙ የሚያስችሉ ምልክቶች ለምሳሌ:6.1. ባንዴራ ፣ ሃውልቶች ወ.ዘ.ተ. በህዝብ ተግባቦት ሊቆሙና ሊሰየሙ የግድ የሚል ሲሆን እንደ “አኖሌ ሃውልት” ያሉ ያለተፈጠረ ታሪክ እየዘከሩ በህዝብ መካከል ቂም እየጫሩ ለግጭት የሚገፉናምክንያት የሚሆኑ መሰል ምልክቶች ሊወገዱ ይገባል6.2. ዋና ከተማወች ለምሳሌ እንደ አዲስ አበባና ድሬደዋ ያሉ /Metropolitan cities/ የመላ ሃገር ህዝቦች መናህሪያ ፣ የተለያዩ ሃገራት ኢምባሲዎች መቀመጫ፣ የውጭ ሃገር ድርጅቶች መናህሪያ ፣ የለጋሽ ሃገራት ቢሮዎች በመሆናቸው ለአንድ የሕዝብ አካል /ብሄር/ ለመስጠት ወይም ጥቅም ማስጠበቂያ ለማድረግ መሞከር ለሕዝብ እልቂት / Jonocide/ና ግጭት ምክንያት ስለሚሆኑ እነዚህ ዋና ዋና ከተሞች የመላው ህብረተሰብ መኖሪያ መሆናቸውን በሕግ ማወጅ የግድ ይላል፣

 

6.3.) በዋና ከተሞች ደንብና ስርአት የሚያስጠብቁ ፓሊሶች ፣ ትራፊኮች ፣ ደንብ አስከባሪዎችበመንግስት የስራ ሃላፊነት የሚሰሩ የስራ ሃላፊዎች ወ.ዘ.ተ. የተለያዮ የሃገሪቱን ህዝቦች /ብሄሮች/ የሚወክሉና አማረኛ ተናጋሪ ቢሆኑ ይመረጣል፣።

7) መንግስት ለችግሮች መባባስ ያሳየው ዳተኝነትናግጭቶችን ለመፍታት ያለው አቅመ ደካማነት ሊፈተሽ የግድ ይላል።

8) ተቃዋሚ ከሆኑ ቡድኖች ከሕወሃት ፣ ኦነግና ኦነግ ሸኔ ጋር ለመማከር መሞከሩ ባይከፋም የሚያቀርቡት ቅድመ ሁኔታዎች ለሃገር  ደህንነት ፣ ሉአላዊነት፣ ሰላምና አብሮነት ፀር ስለሆኑና መሪዎቹም በሰሩት ወንጀል በሕግ የሚፈልጉ በመሆኑ በማን ተወክለውና በአንፃራዊነት የሰላምና የአንድነት መንፈስ ካላቸው ተከታዮቻቸው ጋር በገደምዳሜው የኢትዮጵያንና የሕዝቦቿ የጋራ ጥቅም አሳልፎ ባለ መስጠት ሊከወን የሚቻልበትን አካሄድ መቀየስ የተሻለ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል።

ማጠቃለያ

አገራዉ የምክክር መድረክ ከላይ የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታወችን አሟልቶ ከተከናወነ እውነተኛ እርቅ /Reconciliation/ ዕውን ይሆናልተብሎ ይታሰባል።

መንግስት ይህ የህዝብ መመካከሪያ መድረክ /National Dialogue/ ጉባኤ ሲቋቋም እጁ ሊገባ አይገባም፣

የመማክርት ጉባሄ መማክርታን / Public Covneres/ ሲመረጡበግለልተኛ ወገን መሆን ይገባዋል።

መንግስት ለድርድር የቀረቡትን ቡድኖችና ግለሰቦችን ለማባበልና የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም ሲል ለተቃራኒ ቡድኖች ስልጣን በማካፈል ችግሩን ለማብረድ ከሞከረ “ ከድጡ ወደ ማጡ” እንደሚሆንበት ከሌሎች ሃገሮች ልምድ አንፃር የታየ በመሆኑ ይህ ዓይነቱ አካሄድ መታሰብም ሆነ መሞከር የለበትም።

በመጨረሻም መድረኩ አሳታፊ /Inclusive/ , ግልፅ / Transparence/ የተሞላበት፣ ግልፅ አጀንዳ ያለው ፣ ስርዓት ያለው አካሄድ የተላበሰ / ከታልቃ ገብነት የራቀ፣ የተመረጡት የመማክርት ጉባኤ አባላቱ ትፅህኖ በሌለበት መልኩ ያለ መንግስት ጣልቃ ገብነት ሊሰየሙ ይገባል።

ተዘራ አሰጉ- ከምድረ እንግሊዝ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *