አዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ዝርዘር ጉዳዮች
– የህንፃው መሰረት ድንጋይ የተቀመጠው በሰኔ 20 ቀን 2007 ዓ/ም በወቅቱ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣን በነበሩት በሚኒስትር ማዕረግ የፖሊሲ ጥናት እና ምርምር አማካሪ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ በረከት ስምኦን ነው።
– ግንባታውን ለማካሄድ ረጅም ጊዜ ጥናት የተደረገ ሲሆን ቦታውን ለማግኘት እራሱን የቻለ ጊዜ ወስዷል ፤ 18,308 ሜትር ስኩዌር መሬት ለህንፃው ከተሰጠ በኃላ በርካቶች የተሳተፉበት የዲዛይን ውድድር ተካሂዶ አሁን ያለው ተመራጭ ሊሆን ችሏል።
– የህንፃውን ዲዛይ እና ግንባታ ተቋም ለመለየት 7 ዓመታት ወስዷል።
– ህንፃው እጅግ ዘመናዊ የሆነ እና በኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ያልተለመደ አሰራርን አካቶ ነው የተሰራው።
– የህንፃው ግንባታ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (AAiT) ተቆጣጣሪነት በቻይና መንግስት ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አማካኝነት ነው የተካሄደው።
– 4 የምድር ውስጥ እና 49 ከምድር በላይ በድምሩ ባለ 53 ወለል ከፍታ ያለው ርዝመቱ 209.15 ሜትር የሆነ ታወር ሲሆን ሁለት ባለ 11 እና ባለ 13 ወለሎች ግዙፍ ህንፃዎችን አካቷል። በድምሩ ከ165 ሺህ ካሬሜትር በላይ ስፋት ላይ የተገነባ ነው።
– ባለ 11 ወለሉ ህንፃ ለኮንፈረንስ ነው፤ በአንድ ጊዜ 2500 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ የስብሰባ አዳራሽ ፣ 300 ሰዎችን የሚይዙ እና 200 ሰዎች የሚይዙ 5 መለስተኛ የስብሰባ አዳራሾች አሉት (ሁሉም እርስ በእርሳቸው መገናኘት ይችላሉ) ፤ የሰራተኞች መመገቢያ እንዲሁም የባንክ ቅርንጫፍ አሉት።
– ባለ13 ወለሉ ህንፃ ለንግድ ስራ ማዕከልነት የሚያገለግል ነው። 5 ክፍሎች ያሉት እጅግ ዘመናዊ የሲኒማ አዳራሽ ፣ የንግድ ማዕከላት፣ ጂምናዚየም ፣ የውበት መጠበቂያ ስፓ፣ የልጆች መዝናኛ ማዕከል ጌም ዞን ፣ ሬስቶራንቶች ፣ ፉድ ኮርት አካቷል።
– የዋናው ህንፃ አንደኛ ፎቅ ቋሚ የአውደርእይ ማሳያ ነው፣ ከ2ኛ እስከ 46ኛ ፎቅ የባንኩ የዋና መስሪያ ቤት ሰራተኞችን ቢሮ ይይዛል። 47ኛ እና 48ኛ ፎቆች የካፍቴሪያ እና የመዝናኛ ቦታዎች ናቸው።
– 24 አሳንሰሮች፣ 26 ስኬሌተሮች አሉት። 4ቱ የምድር ውስጥ ወለሎች 1500 መኪና መያዝ የሚችል ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ መካኒካል ፓርኪንግ ጨምሮ የያዘ ፣ ሌሎች ልዩ ልዩ አገልግሎት የያዙ ክፍሎች የያዘ ነው።
– ሙሉ ህንፃው ዘመናዊ የእሳት መከላከያ እና የ CCTV ካሜራዎች ፣የሚዲያ ፋሲሊቲ፣ በረጅሙ ህንፃ 3 የአደጋ ጊዜ መቆያ ሪፊውጂ ወለሎች አሉት። ዘመናዊ የደህንነት መጠበቂያ ሲስተም የተገነቡለት ነው።
– ውሃ እና መብራት በቁጠባ ለመጠቀም IBM የተሰኘ ልዩ ቴክኖሎጂ ተገጥሞለታል።
– ህንፃው በአዲስ አበባ ረጅሙ ህንፃ በምስራቅ አፍሪካ እና በመላው አፍሪካ ሰማይ ጠቀስ ህፃዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው።
– ግንባታው 303.5 ሚሊዮን ዶላር ፈጅቷል።
– የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ/ም በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናት በተገኙበት ተመርቋል።