” ሀገር እንደ ልብስ አትበጣጠስም ” – ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ

0
0 0
Read Time:52 Second


የ2014 ዓ/ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የመክፈቻ ጸሎት መርሐ ግብር በአዲስ አበባ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተካሂዷል።

በዚሁ መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ስለ #ሰላም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ብፁዕነታቸው ፥ ” በአሁን ጊዜ በቤተክርስቲያናችን በኩል ያለው ከሚመጣው መከራ የተነሳ ምዕመናን ከመሞታቸው ፣ ካህናት ሰማዕት ከመሆናቸው የተነሳ ቤተክርስቲያኒቱ መከረኛ ሆናለች ፤ ድሮም መከረኛ ናት በእርግጥ የሰማዕታት ቤት ናት ፤ ስለዚህም ተግተን ልንፀልይ ሰላምንም ልናስገኝ ይገባል ” ብለዋል።

” ሁሉ የተጣላበት ዘመን ነው ” ያሉት ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ” በሰዎች ዘንድ ፣ በሁሉ ዘንድ ሰላም የለም ” ሲሉ ገልፀዋል።

” አንድ አካል ፣ አንድ ህዝብ ፣ አንድ ህብረ አባል፣ አንድ ህብረ ሀገር የሆነች ኢትዮጵያ በአሁን ጊዜ እርስ በእርሱ መጣላት ፣ መጋጨት ፣ መጋደል እየታየ ነው ” ብለዋል።

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ” ይህችን ታላቅ ሀገር ኢትዮጵያን ለመከፋፈል የሚሞክሩ የተወገዙ ይሁኑ ፤ ለምንድነው ይሄ የሚሆነው ? ሀገር አትከፈልም፣ ሀገር እንደ ልብስ አትበጣጠስም ፥ ይህኔ ሁሉ ያርቅልን ዘንድ እግዚአብሔር አምላካችን በጥበቡ በቅዱስ ፍቃዱ ያርቅልን ” ሲሉ መልዕክታቸውን አስታላልፈዋልን።

ዛሬ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በነበረው የመክፈቻ ጸሎት መርሐ ግብር ላይ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፣ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተገኝተው ነበር።

ፎቶ ፦ EOTC TV
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *