የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ የደመወዝ እርከን አወጣ!!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ መደቦች ምዘና፣ ደረጃዎች ምደባና የደመወዝ እርከን ደንብ ማውጣቱ ተሰምቷል።የከተማ አስተዳደሩ አዲስ ባወጣው በደንብ መሰረት
✔የደረጃ አንድ የደመወዝ መነሻ 1,100 ብር ሲሆን፣ የዚህ ደረጃ ጣሪያ 2,079 ብር ነው፡፡
✔ የመጨረሻው ደረጃ የደመወዝ መነሻ 20 ሺህ 468 ሲሆን፣ ጣሪያ ደግሞ 26 ሺህ 959 ብር ነው፡፡
በእያንዳንዱ ደረጃ ዘጠኝ የደመወዝ እርከኖች ያሉ ሲሆን፣ የደመወዝ ጭማሪን በሚመለከት ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ የሥራ አፈጻጸም ምዘና ውጤቱ መካከለኛ ወይም ከመካከለኛ በላይ ሆኖ ከተገኘና ደመወዙ ጣሪያ ላይ ካልደረሰ በደመወዝ እርከኑ የተፈቀደውን የእርከን ጭማሪ በየሁለት ዓመቱ ያገኛል፡፡
በአዲሱ ደንብ የተወሰነው የደመወዝ እርከን በሥራ ላይ ሲውል ወይም የደመወዝ እርከኑ ሲቀየር የአንድ የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ፣ለያዘው የሥራ መደብ ከተወሰነው የመነሻ ደመወዝ በታች ከሆነ ወደ መነሻው ደመወዝ ከፍ እንዲል ይደረጋል፡፡በደንቡ ላይ እንደተገለጸው ከሥራ መደቡ የደመወዝ ጣሪያ ጋር እኩል ወይም ከዚያ በላይ የሆነ የመንግሥት ሠራተኛው የደመወዝ ጭማሪ አይደረግለትም፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ያወጣው ደንብ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የሚስፈጽመው ሲሆን፣ በደንቡ ቢሮው የተለያዩ ሥልጣንና ኃላፊነቶች ተሰጥተውታል፡፡ከኃፊነትና ሥልጣኖቹ መካከልየሥራ መደቦችን ምዘናና የደረጃ ምደባ በደንቡ መሠረት የማከናወን እና አፈፃፀሙን የመከታተል፣የሥራ መደብ መጠሪያዎችን ወጥ የማድረግናለሥራ መደቦች የመለያ ኮድ የመስጠት፣የሥራ መደቦች የደረጃ ምደባ ቅሬታዎችን አጣርቶ ምላሽ የመስጠት የሚሉት ይገኙበታል፡፡
[ዋዜማ ራዲዮ]