የማይክ ሐመር ስለ ኢትዮጵያ ቆይታቸው ምን አሉ ?

0
0 0
Read Time:53 Second

አሜሪካ የኢትዮጵያን #ሉዓላዊነቷን እና #የግዛት_አንድነቷን_በማክበር ኢትዮጵያን ለመደገፍ ያላትን ፍላጎት እንደሚያረጋገጡ የሀገራቸውን አቋም ገልፀዋል።

በአሜሪካ ህዝብ ለጋስነት ሀገሪቱ ለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ ድጋፍ እያደረገች መሆኑን አመልክተዋል።

ሰላምን በማረጋገጥ በኩል የጋራ ፍላጎቶችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ከመንግስት ጋር የመነጋገር እድሉን ማግኘታቸውን እንደሚያደንቁ ገልፀዋል።

ሀመር በኢትዮጵያ ቆይታቸው ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ልማት እቅዶች ይበልጥ እንዳወቁና እንደተማሩ አሳውቀዋል።

በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ስር ባለ ዲፕሎማሲ፣ በናይል ወንዝ ዳር የሚኖሩትን ሁሉ የሚያገለግል ስምምነት ላይ መድረስ ይቻላል ብለዋል።

ሀመር በኢትዮጵያ ለሁለት ሳምንት የሚጠጋ ጊዜ የቆዩ ሲሆን ቆይታቸው አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ረጅም የግንኙነት ታሪክ እና በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ለአፍሪካ ህብረት የምታደርገውን ጥረት የሚያንፀባርቅ መሆኑን በአ/አ የአሜሪካ ኤምባሲ ገልጿል።

ሀመር በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከእነማን ጋር ተገናኙ ?

– ከፕ/ት ሳህለወርቅ ዘውዴ

– ከም/ጠ/ሚ እና ውጭ ጉዳይ ሚ/ር አቶ ደመቀ መኮንን

– ከኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሌንሳ ቢየን

– ከተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች

– ከተመድ መርማሪዎች (በአ/አ)

– ከAU የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦባሳንጆ

– ከመንግስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች

– ወደ ትግራይ ተጉዘው ክልሉን እያስተዳደሩ ካሉት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እና ሌሎች የህወሓት አመራሮች ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *