የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለንግሰ‍ት ኤልዛቤት ዳግማዊት ስርዓተ ቀብር ወደ ለንደን ደርሰዋል።

0
0 0
Read Time:45 Second

የሀገራችን ኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፤ የጎረቤታችን ኬንያ፣ ሶማሊያ ፣ ሱዳን መሪዎች ለንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ስርዓተ ቀብር ወደ ዩናይትድ ኪንግደም መድረሳቸው ተሰምቷል።

ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ በንግስቷ ህልፈት በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ሀዘናቸውን ለመግለፅ ለንደን የገቡ ሲሆን ለንግሥቲቱ በተዘጋጀ የሀዘን መግለጫ መዝገብ ላይም ሀዘናቸውን ገልፀዋል።

የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ፤ በትላንትናው እለት ለንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ስርዓተ ቀብር ወደ ለንደን በረዋል። ፕሬዜዳንቱ በስርዓተ ቀብሩ ላይ ከታደሙ በኃላ ወደ ኒውዮርክ በማቅናት 77ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደሚታደሙና ከዓለም መሪዎች ጋር እንደሚቀለቀሉ ገልፀዋል።

በንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ህልፈት #ኬንያ የ3 ቀን ብሄራዊ ሀዘን አውጃ እንደነበር ይታወሳል። በንግስቷ ሞት በኬንያ ሀዘን መታወጁ በቅኝ ግዛት ወቅት ከተፈፀሙ ግፎች ጋር በተያያዘ በርካቶች ሲቃወሙ ነበር።

በሌላ በኩል የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ለንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ድርዓተ ቀብር ዛሬ ለንደን ገብተዋል። ለንግሥቲቱ በተዘጋጀ የሀዘን መግለጫ መዝገብ ላይም ሀዘናቸውን እንደገለፁ ተሰምቷል።

የሱዳን ጦር አዛዥ እና የሃገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃንም ወደ ለንደን አቅንተዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *