የሱዳን የሉዓላዊ ም/ቤት ሊቀመንበር ፤ ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ባህር ዳር የጣና ፎረም እየተካፈሉ ይገኛሉ።

Read Time:44 Second
ባህር ዳር የጣና ፎረም መካሄድ ጀምሯል።
10ኛው የ ” ጣና ፎረም ” ጉባኤ በአፍሪካ የሰላም ፣ ጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክ ይነግራል እስከ ጥምቅት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
በ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራው ሥብሰባ የሶማሊያ ጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ እና የሱዳን የሉዓላዊ ም/ቤት ሊቀመንበር ፤ ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን እና ሌሎችም እየተካፈሉ ይገኛሉ።
ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ ” በአፍሪካውያን ለአፍሪካውያን የሚጠቅሙ መፍትሔዎች የሚወጡበት ውጤታማ የውይይት ጊዜ እንደሚሆንልን እምነቴ ነው ” ብለዋል።
የጣና ፎረም አፍሪካውያን መሪዎችን እና ባለ ድርሻ አካላትን በአሕጉራዊ የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በማወያየት ዘላቂ መፍትሔዎችን ለመቀየስ አልሞ ሚካሄድ ውይይት መሆኑን ጠቅላዩ ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ፤ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን የሽግግር መንግስት ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ከሆኑት ሌተናል ጀነራል አል ቡርሃን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል ፤ ከዚህ በተጨማሪ ዓባይ ወንዝ ላይ በመገንባት ላይ ያለውን ግዙፍ የድልድይ ግንባታ ስራ ጎብኝተዋል።
- Ethiopia’s Road to Recovery: Balancing Civil Conflict, Debt, and Reform
- ያ ካፋው ሚካኤል የካቲት 12 የአዲስአበባ ነዋሪዎች በግፍ የተጨፈጨፉበት ቀን !
- Ethiopia bondholders say IMF report ‘artificially’ creates solvency issue
- Tulu Kapi Gold Project, Ethiopia
- African Leaders Converge in Ethiopia for the 38th AU Summit