ዶ/ር ደብረፅዮን ለሠላም ድርድር ድርጅታቸው ዝግጁ መሆኑን አስታወቁ።
Read Time:37 Second
ህወሓት በደቡብ አፍሪካ በሚደረገው የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን ትላንት ምሽት አሳውቋል።
ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ርጠኞች ነን ሲልም ገልጿል።
ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ለአፍሪካ ህብረት ሊቀንበር በፃፉት ደብደቤ ፤ ለሰላም ሂደቱ ይረዳል ያሉትን ” ግጭት ማቆም ” ዋናው የድርድሩ የአጀንዳው አካል ተደርጎ ስለመያዙ ጠይቀዋል።
” ተደራዳሪዎቻችን ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመላክ ዝግጁ ነን ” ሲሉም አሳውቀዋል።
” ግብዣው ቀደም ብሎ ያልተማከርንበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ቢሰጠን ” ሲሉ በፃፉት ደብዳቤ ጠይቀዋል።
እነዚህም ፦
– በሰላም ውይይቱ ተጨማሪ ተዋናይን እንደ ተሳታፊዎች፣ ታዛቢዎች ወይም ዋስትና ሰጪዎች የሚጋበዙ ይኖሩ እንደሆነ፤
– ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምን አይነት ሚናዎችን ሊሰጥ እንደታሰበ ፤
– ለተደራዳሪ ቡድኑ የሎጅስቲክስ ፤ #የጉዞ እና የደህንነት ዝግጅቶችን በተመለከተ እንዲብራራላቸው ዶ/ር ደብረፅዮን ለፋኪ በላኩት ደብዳቤ ጠይቀዋል።
ዛሬ ጥዋት የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት በደቡብ አፍሪካ የሚደረገውን የሰላም ንግግር ግብዣ መቀበሉን ማሳወቁ ይታወቃል።